ፔፕ ጋርዲዮላ በአሁኑ ሰዓት የጣሊያን እግር ኳስ ፌዴሬሽን (FIGC) የብሔራዊ ቡድኑ ቁጥር አንድ አሰልጣኝ እንዲሆን ከፍተኛ ፍላጎት አለው ።

የጣሊያን ብሔራዊ ቡድን ከዓለም ዋንጫ ማጣሪያ መሰናበቱን ተከትሎ ጄናሮ ጋቱሶ ከሃላፊነታቸው መልቀቃቸው ይታወሳል።
ይህንን ተከትሎ አዲስ የተሾሙት የጣሊያን ቴክኒካል ዳይሬክተር ፓኦሎ ማልዲኒ  የጣሊያንን እግር ኳስ ከመሰረቱ ለመለወጥ እና አዲስ አብዮት ለመፍጠር ጓርዲዮላን ለማምጣት ከፍተኛ ፍላጎት አሳይተዋል።

በጓርዲዮላና በጣሊያን መካከል ስላለው ወቅታዊ ሁኔታ ዋና ዋናዎቹ መረጃዎች ከጠቆሙት መካካል የጣሊያኑ ጋዜጣ [La Gazzetta dello Sport] እንደዘገበው፣ ፓኦሎ ማልዲኒ እና ስትራቴጂካዊ አማካሪው ሊዮናርዶ የቀድሞዎቹን የጣሊያን አሰልጣኞች (አንቶኒዮ ኮንቴና ሮቤርቶ ማንቺኒ) ከመቅጠር ይልቅ ለፔፕ ጋርዲዮላ ቅድሚያ ሰጥተዋል።ማልዲኒ  ከጋርዲዮላ ጋር መነጋገሩንና ፍላጎቱን ለመጠየቅ መቃረቡን የሚዲያ ዘገባዎች ያመለክታሉ።  ፔፕ ጋርዲዮላ ባለፈው ግንቦት ወር ማንቸስተር ሲቲን ከለቀቀ በኋላ በአሁኑ ሰዓት እረፍት ላይ ይገኛል።እሱ ራሱ ከዚህ ቀደም የብሔራዊ ቡድን የማሰልጠን ፍላጎት እንዳለው ደጋግሞ ገልጿል።

በተጨማሪም በተጫዋችነት ዘመኑ በጣሊያኑ ብሬሻ (Brescia) እና ሮማ ክለቦች በመጫወቱ ከሀገሪቱ ጋር ጥብቅ የፍቅር ትስስር አለው። ይሁንና ዋናው ጋሬጣ የገንዘብ ጉዳይ ነው ለዚህ ዝውውር ትልቁ እንቅፋት የጓርዲዮላ የደመወዝ ክፍያ ነው።

የጣሊያን እግር ኳስ ፌዴሬሽን ይህንን የገንዘብ መጠን ብቻውን መሸፈን ስለሚከብደው፣ ትልልቅ ስፖንሰሮች የጋርዲዮላን ደሞዝ ሙሉ በሙሉ ለመሸፈን ፍላጎት እያሳዩ መሆኑ ተነግሯል።

ጣሊያን በታሪኳ የውጭ ሀገር አሰልጣኝ የመቅጠር ልምድ የላትም፤ ነገር ግን ለሶስት ተከታታይ የዓለም ዋንጫዎች ማለፍ ባለመቻሏ ይህንን ታሪክ ሰብራ ጋርዲዮላን ለመቅጠር እየጣረች ነው።

የጣሊያን ብሔራዊ ቡድን (Azzurri) አዲሱ ዋና አሰልጣኝ ለመሆን ከጋርዲዮላ በመቀጠል በአሁኑ ሰዓት አንድሪያ ፒርሎ (Andrea Pirlo) ግንባር ቀደም እጩ (Pole Position) ሆኖ እየመራ ይገኛል።

የጣሊያን እግር ኳስ ፌዴሬሽን (FIGC) ፕሬዝዳንት ጆቫኒ ማላጎ፣ አዲሱ ቴክኒካል ዳይሬክተር ፓኦሎ ማልዲኒና አማካሪው ሊዮናርዶ ባደረጉት አስቸኳይ ስብሰባ 4 ዋና ዋና አሰልጣኞችን ያካተተ አጭር ዝርዝር (Shortlist) ይፋ አድርገዋል። ውሳኔው በሚቀጥለው ሳምንት በይፋ የሚታወቅ ሲሆን፣ የዕጩዎቹ ወቅታዊ ሁኔታ የሚከተለው ነው፦

1. አንድሪያ ፒርሎ (Andrea Pirlo) — ቁጥር አንድ እጩ

ወቅታዊ ሁኔታ፦ በጣሊያን ሚዲያዎች (እንደ La Gazzetta dello Sport) ዘገባ መሰረት ፒርሎ አሁን ላይ የፌዴሬሽኑ ዋነኛ ምርጫ ሆኗል።

ለምን ተመረጠ? ማልዲኒ እና ሊዮናርዶ አዲስ እና ወጣት አሰልጣኝ ወደ ቡድኑ በማምጣት አዲስ የታክቲክ አብዮት መፍጠር ይፈልጋል። ፒርሎ የ2006 ዓለም ዋንጫ ባለቤትና የጣሊያን እግር ኳስ ምልክት በመሆኑ ቡድኑን መልሶ ለመገንባት ተመራጭ ሆኗል። ሆኖም የአሰልጣኝነት ልምዱ አነስተኛ መሆኑ በሀገሪቱ ተንታኞች ዘንድ «አደገኛ ውርርድ»(Gamble) በሚል ትልቅ ክርክር አስነስቷል።
2.ኛ ሮቤርቶ ማንቺኒ (Roberto Mancini)

ወቅታዊ ሁኔታ፦ የቀድሞው የጣሊያን አሰልጣኝ በሁለተኛ ደረጃ ላይ በጠንካራነቱ እየተጠቀሰ ይገኛል።

ለምን ተመረጠ? ማንቺኒ ከፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት ማላጎ ጋር በጣም ጥብቅና የቆየ ወዳጅነት አላቸው። ከዚህም በላይ አብዛኛዎቹ የአሁኑ የጣሊያን ብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾች ማንቺኒ በድጋሚ ተመልሶ ቡድኑን እንዲረከብ በይፋ ፍላጎታቸውን ገልጸዋል።

3ኛ. አንቶኒዮ ኮንቴ (Antonio Conte)

ወቅታዊ ሁኔታ፦ ሌላኛው የቆየ ታሪካዊ ስኬት ያለው የቀድሞ አሰልጣኝ።

ለምን ተመረጠ? ኮንቴ ቡድንን በፍጥነት የመገንባትና የማሸነፍ ስነ-ልቦና የመፍጠር ከፍተኛ ብቃት አለው። ነገር ግን ማልዲኒ እና ሊዮናርዶ ከኮንቴ ይልቅ ለፒርሎ እና ለማንቺኒ ቅድሚያ በመስጠታቸው አሁን ላይ ስሙ በመጠኑ ወደ ኋላ እቀረ ይገኛልፈገግ ብሏል።

4ኛ. ፔፕ ጓርዲዮላ (Pep Guardiola) — የህልም ምርጫ

ወቅታዊ ሁኔታ፦ የማልዲኒ ትልቁ ህልም ጓርዲዮላን ማምጣት ቢሆንም፣ የፊናንስ ጉዳዮች (የደሞዝ ጥያቄው) እና አሰልጣኙ በአሁኑ ሰዓት እረፍት መፈለጉ ዝውውሩን በጣም አስቸጋሪ አድርጎታል።

በአጠቃላይ፣ ጣሊያንን በይፋ የመረከብ ከፍተኛ ዕድል ያለው አንድሪያ ፒርሎ ሲሆን፣ እሱ ካልተስማማ ደግሞ ሮቤርቶ ማንቺኒ በድጋሚ የመመለስ ሰፊ ዕድል አለው።

Facebooktwitterlinkedinyoutubetumblrinstagramflickrfoursquaremail
Facebooktwitterredditpinterestlinkedintumblrmail

By admin

Hello, dear. I am Wosenseged Mersha Demissie. Author, Journalist, and Sociological Criticism. He has worked in several media in Ethiopia and foreign media also. I have come to my country, Ethiopia, from abroad, and for the past eight years, I have been giving political analysis and writing in magazines, newspapers, and televisions on all the free press in Ethiopia. I have six books that I wrote and published during my stay abroad and after I came back to my country and are on the market. Above all, I feel spiritual satisfaction for coming from a developed country and working in a country where there is no freedom of the press. I have sacrificed a lot in this profession. Imprisonment, abuse—I was crushed economically. I have been living separately from my family for many years, but I am happy and proud of my career to be a voice for the voiceless people of Ethiopia, whom I love and respect by working in the press without payment. After leaving my country and returning to my country, Growing up in Arat Kilo, YMCA, I was exposed to various sports. I know many sports. I have worked as a referee, player, and tournament organizer. As a result, I have worked as a sports editor on radio, television, and newspapers for many years. I have worked alongside other media outlets for more than 20 years by preparing and publishing my own sports newspaper called San George.I have traveled to many countries, including Europe, the Far East, Asia, Oceania, and Africa, and have been present at many competitions, including athletics.This is because I have this love for sports. I have reopened this media outlet for sports. In addition to this, I have worked for the past 30 years. May God protect Ethiopia and its people and give peace and love to our world. Thank you anyway. Wosenseged Mersha Demissie Author, Journalist, Sociological Criticism

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *