የሀገር ውስጥ የእግር ኳስ ዜናዎች

IMG_20260802_094241_522

Ethiopia Football Local News

የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር የ2019 ዓ.ም ጠቅላላ ጉባኤና የስታዲዮም ግንባታ

ጉባኤዉ ላይ የስፖርት ማህበሩ አባላት፣ የሥራ አመራር ቦርድ አባላት፣ የስፖርት ማህበሩ ከፍተኛ ሥራ ኃላፊዎች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

‎በቅርቡ የማህበሩን ህልዉና ለማስቀጠል የተቋቋመዉ ጊዜያዊ ቦርድ ባለፋት አምስት ወራት ያከናወናቸዉን ተግባራት ለጠቅላላ ጉባኤዉ አባላት ይፋ አድርጓል።

‎ጊዚያዊ ቦርዱ ላለፋት ወራት በዋናነት የክለቡን የፋይናንስ ህልዉና ለማስቀጠል በስፋት ሲሰራ መቆየቱን የገለፁት የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር ሊቀመንበር አቶ ነሲቡ ጫኮ፣ የክለቡን የፋይናንስ ስርአት ለማስተካከል ከተለያዩ አጋር ድርጅቶች ጋር ስምምነት መፈፀሙን ገልፀዋል።

CBE Ethiopian Premier League

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አምስተኛ ሳምንት ተጠባቂ የነበረው የባህር ዳር ከተማና ፋሲል ከነማ ጨዋታ 2 ለ 2 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቅቋል።በባህር ዳር ኢንተርናሽናል ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ

ፋሲል ከነማ በጄሮም ፊሊፕ እና ታምራት ኢያሱ ግቦች 2 ለ 0 ቢመራም፣ በጨዋታው መጠናቀቂያ ደቂቃዎች ላይ አንተነህ ተፈራ አከታትሎ ያስቆጠራቸው ሁለት ግቦች ባህርዳር ነጥብ ተጋርቶ እንዲወጣ አስችለዋል።

የሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ በታላቁ ጉጉት የሚጠብቀው “የጣና ደርቢ” ጨዋታ

ዛሬ ቅዳሜ ጥቅምት 21 ቀን 2019 ዓ.ም. (October 31, 2026) የሚደረጉት የሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ (CBE Ethiopian Premier League 2026/27) የአምስተኛ ሳምንት ጨዋታዎች

ኢትዮጵያ ቡና ከ አዳማ ከተማ

ሰዓት፦ ከቀኑ 09:00 ሰዓት

ስታዲየም፦ አዲስ አበባ ስታዲየም

ወቅታዊ ሁኔታ፦

ኢትዮጵያ ቡና፦ ባለፉት ሁለት ጨዋታዎች ሽንፈት ያስተናገደ ሲሆን በ3 ነጥብ በደረጃ ሰንጠረዡ 13ኛ ላይ ይገኛል።

አዳማ ከተማ፦ በአንጻሩ ባለፉት ሦስት ጨዋታዎች ድል ባያገኝም በ5 ነጥብ 8ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። ሁለቱም ክለቦች ወደ አሸናፊነት ለመመለስ የሚያደርጉት ተጠባቂ ጨዋታ ነው።

ፋሲል ከነማ ከ ባህር ዳር ከተማ (የጣና ደርቢ)

ሰዓት፦ ከቀኑ 09:00 ሰዓት

ስታዲየም፦ ባህር ዳር ኢንተርናሽናል ስታዲየም

ይህ ጨዋታ በታላቁ “የጣና ደርቢ” (የአማራ ደርቢ) ስያሜ የሚታወቅ እጅግ ተጠባቂ የሳምንቱ መርሃ ግብር ነው። ፋሲል ከነማዎች ከመጀመሪያ ሳምንታት መደናቀፍ ወጥተው ውጤታቸውን ለማስተካከል የሚጫወቱበት ሲሆን ባህር ዳር ከተማ በአንጻሩ በሊጉ ጥሩ አጀማመር ካላቸው ክለቦች አንዱ ነው።

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የአራተኛ ሳምንት
ጨዋታዎች ዛሬ ቀጥሎ ይውላል

የ2026/27 (የ2019 ዓ.ም.) የሲቢኢ (CBE) የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የአራተኛ ሳምንት ጨዋታዎች በአሁኑ ወቅት በመካሄድ ላይ ይገኛሉ።

የዚህ ሳምንት (4ኛ ሳምንት) እስካሁን የተመዘገቡ ውጤቶች እና ቀጣይ መርሐ-ግብሮች እንደሚከተለው ቀርበዋል፦

የሳምንቱ የተደረጉ ጨዋታዎች ውጤት

ሀዲያ ሆሳዕና 1 – 0 ፋሲል ከነማ (ቅዳሜ ጥቅምት 14/2019 የተደረገ)

ኢትዮ ኤሌክትሪክ 1 – 0 ኢትዮጵያ ቡና (እሁድ ጥቅምት 15/2019 የተደረገ)

የካፍ ገለልተኛ የገምጋሚዎች ቡድን የሀዋሳ ስታዲየም እና የከተማውን የማስተናገድ አቅም ሲገመግም ውሏል

በጉብኝቱ ላይ የሲዳማ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የገንዘብ ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ዳዊት ሀዬሶ፣ የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ አቶ ጥራቱ በየነ እንዲሁም የክልሉና የከተማዋ አስተዳደር የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

የካፍ ባለሙያዎች ቡድን ሀዋሳ ስታዲየምን በተመለከተ ባደረጉት ምልከታ ሪፖርት አቅርበዋል። በምልከታቸውም ስታዲየሙ ማሻሻያ ለማድረግ የሚያስችል ሰፊ ክፍት ቦታዎች እንዳሉት ነገር ግን ሙሉ ለሙሉ እድሳት እንደሚገባው፣ ስታዲየሙ እና የልምምድ ሜዳው የእድሳት ሥራ በአንድ ዓመት ውስጥ ሊጠናቀቁ እንደሚገባ አንስተዋል። ስታዲየሙ ዲዛይኑ በጥሩ ሁኔታ የተሰራ ቢሆንም ማሻሻያ መደረግ አለበት የሚል ሀሳብ ቀርቧል።

ታላቁ 53ኛው የሸገር ደርቢ በኢትዮጵያ ቡና አሸናፊነት ተጠናቀቀ

ቅዳሜ ጥቅምት 17 ቀን 2019 ዓ.ም (እ.ኤ.አ. ኦክቶበር 17, 2026) በሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሁለተኛ ሳምንት መርሃ ግብር ከተደረጉት ጨዋታዎች መካከል የሀገሪቱ ታላቁ የሸገር ደርቢ (የ53ኛው የሸገር ደርቢ) በኢትዮጵያ ቡና አሸናፊነት መጠናቀቁ ትልቁ የዕለቱ አጀንዳ ነበር።

የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ታዳጊ ብሔራዊ ቡድን በሴካፍ (CECAFA) የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ በዩጋንዳ በሰፊ ግብ ተሸነፈ

ቅዳሜ ጥቅምት 17 ቀን 2026 (እ.ኤ.አ.) የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ታዳጊ ብሔራዊ ቡድን በሴካፍ (CECAFA) የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ በዩጋንዳ አቻው 4 ለ 0 በሆነ ሰፊ ውጤት መሸነፉ የስፖርቱ ማህበረሰብ ዘንድ ትልቅ ድንጋጤና ቁጭትን ፈጥሯል። ጨዋታው በሩዋንዳ ኪጋሊ ፔሌ ስታዲየም የተካሄደ ሲሆን፣ የታዳጊዎቹ ሽንፈት በበርካታ የቴክኒክ ክፍተቶች የተሞላ ነበር።

የካፍ ገለልተኛ ከፍተኛ የባለሞያዎች ቡድን በባህር ዳር ከተማ ስታዲየም ምዘና አከናወነ

ኢትዮጵያ የ2028 አፍሪካ ዋንጫን ለማስተናገድ ያቀረበችውን ጥያቄ ተከትሎ ካፍ በላከው ገለልተኛ የባለሙያዎች ቡድን አማካኝነት ባሕር ዳር ስታዲየም ያለውን ዝግጅት በጥልቀት ገምግሟል።

በካፍ የተመደቡ ገለልተኛ ከፍተኛ የባለሙያዎች ቡድን በባህር ዳር ደጃዝማች በላይ ዘለቀ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ በክልሉ እና በባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር የሥራ ኃላፊዎች አቀባበል ተደርጎለታል። በጉብኝቱም ወቅት የወጣቶች እና ስፖርት ሚኒስትር አክሊሉ ታደሰ (ዶ/ር)፣ ሚኒስትር ዴኤታ መኪዩ መሐመድ፣ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ባህሩ ጥላሁን፣ የምኒስቴሩ፣ የክልሉ እና የፌዴሬሽኑ የሥራ ኃላፊዎች ከልዑካን ቡድኑ ጋር ተገኝተዋል።

የሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የለተመልካች ተጀምሯል፤የኢትዮጵያ እግር ኳስ ወቅታዊ ፈተናዎች

ዓርብ ጥቅምት 9 ቀን 2019 ዓ.ም (October 9, 2026) የተጀመረው የ2019/2027 የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የመክፈቻ ጨዋታዎች በጠንካራ ፉክክርና ያልተጠበቁ ውጤቶች የታዩበት ሆኖ ጅማሮ ሆኗል።

የአዳማ ከተማ አስገራሚ ድል

አዳማ ከተማ ወደ ሊጉ የተመለሰውን ኢትዮ ኤሌክትሪክን (መብራት ኃይል) 1 ለ 0 በሆነ ጠባብ ውጤት በማሸነፍ፣ ከ2013 ዓ.ም በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የሊጉን መክፈቻ ጨዋታ በድል መጀመር ችሏል።

የአዲስ አደጎቹና የነባሮቹ አቻ መለያየት

ወደ ሊጉ ለመጀመሪያ ጊዜ ያደገው ሀላባ ከተማ በሜዳው ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲን አስተናግዶ 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይቷል።

ቅዳሜ ጥቅምት 10 ቀን 2019 ዓ.ም የተደረጉት ሁለቱም የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች በጠንካራ ፉክክር ያለ አሸናፊ በአቻ ውጤት ተጠናቀዋል።

ሉሲዎቹ በኦሊምፒክ የሴቶች እግር ኳስ ማጣሪያ የመጀመሪያ ዙር ጨዋታ ሩዋንዳን አሸነፉ

የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን (ሉሲዎቹ) በኦሊምፒክ የሴቶች እግር ኳስ ማጣሪያ የመጀመሪያ ዙር ጨዋታ ሩዋንዳን 1 ለ 0 በሆነ ጠባብ ውጤት አሸንፈዋል።

🇷🇼 ሩዋንዳ 0  🇪🇹 ኢትዮጵያ 1 ኡዛዬ ሴንጋ ሊድያ (በራሷ ላይ ግቡን አስቆጥራለች – 45+3′)

ሁለቱ ቡድኖች የመልስ ጨዋታቸውን በጥቅምት 3 ቀን ያደርጋሉ።
ጨዋታው በድሬዳዋ ስታዲየም ላይ የሚካሄድ ይሆናል።

የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን የመጀመርያውን ጨዋታ ዛሬ ኪጋሊ ላይ ያደርጋል

በ2028 ኦሊምፒክ ሴቶች እግር ኳስ ማጣርያ ከሩዋንዳ ጋር ጨዋታውን የሚያደርገው የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን የመጀመርያውን ጨዋታ ዛሬ ረቡዕ መስከረም 27 ኪጋሊ ላይ ያካሄዳል።

ቡድኑ የመጨረሻ ልምምዱን ትናትና ምሽት 1፡00 ላይ በኪጋሊ ፔሌ ስታዲየም ያከናወነ ሲሆን ሁሉም ተጫዋቾች በተሟላ ጤንነት እና የቡድን መንፈስ ልምምዳቸውን አከናውነዋል።

የኢትዮጵያ ቡድን በሴኔጋል ቢሸነፍም እጅግ የሚበረታታ፣ ለወደፊቱ ትልቅ ተስፋ የሚሰጥ ነው

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን (ዋሊያዎቹ) ሜዳው ላይ ሙሉ ጥረታቸውን ቢያደርጉም እና ሴኔጋልን በከፍተኛ ሁኔታ ለማጥቃት ቢሞክሩም፣ ጨዋታውን በሽንፈት አጠናቀዋል።

የጨዋታው ቁልፍ ነጥቦች እና የዋሊያዎቹ አፈጻጸም

ሴኔጋልን አሸናፊ ያደረገችውን ብቸኛ ግብ በ11ኛው ደቂቃ ላይ ኢብራሂም ምባዬ (Ibrahim Mbaye) የኒኮላስ ጃክሰንን (Nicolas Jackson) ኳስ ተጠቅሞ አስቆጥሯል።

ዋሊያዎቹ ከግብ መቆጠር በኋላ አልተስረከረኩም። በተለይ በአቤል ያለው (Abel Yalew) እና በቸርነት ጉግሳ (Chernet Gugsa) አማካኝነት ወደ ሴኔጋል ሳጥን በተደጋጋሚ በመድረስ ጫና ለመፍጠር እና ግብ ለማስቆጠር ጥረት አድርገዋል。 በአጠቃላይ ኢትዮጵያ 11 ሙከራዎችን (2 ኢላማቸውን የጠበቁ) ማድረግ የቻለች ሲሆን፣ ሴኔጋል ግን 5 ሙከራዎችን ብቻ ነው ያደረገችው።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ማክሰኞ ከሴኔጋል ይጋጠማል፤የሴኔጋል ቡድን ትናት ምሽት ገብቷል

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በብሉ ናይል ሪዞርት ሆቴል ማረፊያውን ያደረገ ሲሆን በዛሬው ዕለት የመጀመርያ ልምምዱን በባህር ዳር ስታዲየም አከናውኗል።

ከኢትዮጽያ ብሔራዊ ቡድን በኩል መስፍን ታፈሰ ከሱዳን ጋር በተደረገው ጨዋታ የማስጠንቀቂያ ካርድ በመመልከቱ በሁለት ቢጫ ካርድ ቅጣት ምክንያት ከሴኔጋል ጋር ከሚደረገው ጨዋታ ውጪ ሆኗል።

የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ከሲሸልስ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ጋር ያደርጋል

በ2028 ኦሊምፒክ ሴቶች እግር ኳስ ማጣርያ ከሩዋንዳ ጋር ለሚያደርጉት ጨዋታ በዝግጅት ላይ የሚገኙት የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ከሲሸልስ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ጋር ሁለት ዓለምአቀፍ የወዳጅነት ጨዋታዎች ያደርጋሉ።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ዛሬ ከሱዳን ጋር ከሚያደርገው ጨዋታ

ዛሬ በመላው አፍሪካ ታላላቅ ሀገራት ለ2027ቱ የአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ የሚያደርጉት የምድብ ማጣሪያ ጨዋታዎች በከፍተኛ ጉጉት ይቀጥላሉ። በአሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ የሚመራው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን (ዋሊያዎቹ) ከጎረቤት ሱዳን ጋር የሚያደርጉት ተጠባቂ ደርቢ የቀኑ ቀዳሚ ፍልሚያ ነው!

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንና የአፍሪካ ሀገራት ትልልቅ ማጣሪያ ጨዋታዎች

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን (ዋሊያዎቹ) ለ2027ቱ የአፍሪካ ዋንጫ (AFCON 2027) ለማለፍ የሚያደርጉት የማጣሪያ ጨዋታ በዚህ ሳምንት በአዲሱ የፊፋ ካላንደር መሠረት በይፋ ይጀምራል። ይህ ማጣሪያ ኬንያ፣ ኡጋንዳ እና ታንዛኒያ በጋራ ለሚያስተናግዱት ታሪካዊ ውድድር የሚካሄድ ነው።

ቅዱስ ጊዮርጊስ ለውድድሩ ዝግጁ ለመሆን ተጨማሪ የአገር ውስጥ የአቋም መለኪያ ጨዋታዎች ያስፈልጉታል

ወደ ታንዛኒያ ዳሬሰላም ያመራው የቅዱስ ጊዮርጊስ ስብስብ መስከረም 8 ቀን 2019 ዓ.ም (September 18, 2026) ከታንዛኒያው ኃያል ክለብ ያንግ አፍሪካንስ (ያንጋ) ጋር ባደረገው ዓለም አቀፍ የወዳጅነት ጨዋታ 1 ለ 0 በሆነ ጠባብ ውጤት እንዲሁም ከዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎው ኃያል ክለብ ማኒዬማ ዩናይትድ (AS Maniema Union) ጋር ባደረገው ሁለተኛ ጨዋታ 2 ለ 0 በሆነ ውጤት ተሸንፏል ።

በደካማው የሴካፋ ውድድር በታንዛኒያ በሰፊ ጎል ተሸንፎ ከውድድር ስለወጣው ቡድናችን ተጠያቂው ማን ነው?

የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች (U-20) ወጣት ብሔራዊ ቡድን በሴካፋ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ውድድር በአዘጋጇ ታንዛኒያ 4ለ0 ተሸንፏል።ግቦቹን ለታንዛኒያ
                    31′ በሽር ኪባሊያ
                45+2′ በሽር ኪባሊያ
                    53′ ጁማ ሳሙኤል
                    55′ ጁማ ሳሙኤል አስቅጥረው  4 ለ 0 በሆነ ሰፊ ውጤት ተሸንፎ ከውድድሩ መሰናበቱ ለኢትዮጵያ እግር ኳስ አሳዛኝ እና ትልቅ ትምህርት ሊወሰድበት የሚገባ አጋጣሚ ነው።

የኢትዮጵያ ወጣቶች ብሔራዊ ቡድን (ዋሊያዎቹ) በሴካፋ ውድድር የማለፍ እድል አለው

በታንዛኒያ ዳሬሰላም ኡሁሩ ስታዲየም በተደረገው ከ20 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ የሴካፋ ቀጠና ማጣሪያ (CAF U-20 AFCON CECAFA Qualifiers) የምድብ A ጨዋታ የኢትዮጵያ ወጣቶች ብሔራዊ ቡድን (ዋሊያዎቹ) ከሩዋንዳ እኩያቸው ጋር ያደረጉትን የመክፈቻ ጨዋታ 0 ለ 0 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።በጨዋታው ላይ ቡድናችን ሙሉ ነጭ መለያ (ኪት) ለብሶ ነው ወደ ሜዳ የገባው።

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን 18ኛ መደበኛ እና የምርጫ ጠቅላላ ጉባዔ በአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን /ECA/ እየተካሄደ ይገኛል።

በ2018 የውድድር ዓመት በህይወት ያጣናቸው የእግር ኳስ ቤተሰቦችን በማሰብ በሕሊና ጸሎት በማድረግ የተጀመረው ጉባዔው በማስከተል የባህል እና ስፖርት ሚኒስቴርን በመወከል አቶ ከበደ እጅጉ ፣ የኦሊምፒክ ኮሚቴን በመወከል አቶ ገዛኸኝ ወልዴ ንግግር ያደረጉ ሲሆን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ  የኢትዮጵያን ብሔራዊ ቡድንን በተመለከተ ለጉባዔው ተሳታፊዎች ንግግር አድርገዋል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አዲስ መረጃዎች

የወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ተጫዋቾች በረከት ሳሙኤል እና ካርሎስ ዳምጠው ለ2027 የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ዝግጅቱን እያደረገ የሚገኘው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን እንዲቀላቀሉ ጥሪ ቀርቦላቸዋል። ተጫዋቾቹ ነገ ከሰዓት ብሔራዊ ቡድኑ የሚገኝበት ሀዋሳ እንዲገኙም ጥሪ ተላልፏል።

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አዲስ የውድድር ዘመን እየተደረጉ ያሉ ቅድመ-ዝግጅቶችና ሁነቶች

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አክሲዮን ማህበር በቅርቡ ባወጣው ይፋዊ መግለጫ መሠረት፣ አዲሱ የ2019 የውድድር ዘመን መስከረም 30 ቀን 2019 ዓ.ም (October 10, 2026) በይፋ ይጀምራል።

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ እጣ ፕሮግራም ማውጣት መስከረም 7/2019 ዓ.ም ይደረጋል!

መስከረም 30 የሚጀምረው የ2019 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር በተመረጡ 7 ሜዳዎች እና በተዘጋጁ 6 ቋቶች በሚወጣው እጣ መሰረት የውድድር አመቱ መርሃ ግብር ይዘጋጃል።

ቅዱስ ጊዮርጊስ በቀጣዩ ሳምንት አጋማሽ ከሀገር ውጪ ጉዞ ሊያደርግ ነው።

የቀድሞ አለቃውን ሰርዲዮቪን ሚሉቲን ሚቾ ዳግም በመንበሩ የቀጠረው ቅዱስ ጊዮርጊስ ያለፉትን ወራት ከአስተዳደራዊ እስከ ሜዳ ድረስ የተለያዩ ለውጦችን እያደረገ ክለቡን እንደ አዲስ እያደራጀ የሚገኝ ሲሆን በክረምቱ የዝውውር መስኮትም በርከት ያሉ አዳዲስ ተጫዋቾችን ይጠቅሙኛል ካላቸው ነባር ተጫዋቾች ጋር አቀላቅሎ ለቀጣዩ የውድድር ዓመት ዝግጅቱን ቀጥሏል። ቡድኑ የቅድመ ውድድር ዝግጅቱን መቀመጫውን በክቡር ይድነቃቸው ተሰማ አካዳሚ አድርጎ እያከናወነ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን ጨማሮ ከሌሎች የሀገር ውስጥ ቡድኖች ጋር የአቋም መፈተሻ ጨዋታ ያከናወነ ሲሆን በቀጣዩ ሳምንት ደግሞ ወደ ታንዛኒያ አምርቶ ሁለት የአቋም መፈተሻ ጨዋታዎችን እንደሚያደርግ ሶከር ኢትዮጵያ አውቃለች።

ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድናችን የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የሴካፋ ዞን ማጣሪያ የምድብ ተጋጣሚዎቹን አወቀ

ዘጠኝ ብሔራዊ ቡድኖች በሚሳተፉበት ውድድርም በምድብ ሁለት ከደቡብ ሱዳን እና ሩዋንዳ ተደልድሏል።

ውድድሩ ከመስከረም 6 እስከ መስከረም 20 ድረስ በታንዛኒያ አስተናጋጅነት ይደጋል።

ለፍፃሜ የሚደርሱ ብሔራዊ ቡድኖች ወደ የ20 ዓመት በታች አፍሪካ ተሳታፊ መሆናቸውን ያረጋግጣሉ።

ኢትዮጵያዊው ተጫዋች ለአላረቢያ ❨Al-Arabi ❩ ክለብ ፈረመ

የኢዲዋይ የቀድሞ ተጫዋች የሆነው ካምላክ ጥላሁን በዱባይ ፕሮፌሽናል ሊግ ለሚገኘው አላረቢያ (Al-Arabi) ከ21 ዓመት በታች ቡድን በይፋ ፈርሟል

ዋሊያዎቹ እና ዲያስፓራ ተጨዋቾች

የሴኔጋል አሰልጣኝ ፓትሪክ ቪየራን ጨምሮ 12 ዲያስፓራ ተጨዋቾችን ይዛ ወደ ኢትዮጵያ ልትመጣ ነው

ኤርትራ በሚያስገርም ሁኔታ 27 ዲያስፓራ ተጨዋቾችን ለደቡብ አፍሪካ ጨዋታ ጠራች

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ኮከብ ግብ አግቢም ተመርጡዋል

ከነዓን እና ጋቶች ብቸኛ ተጨዋቾች ናቸው

አሹ የካናዳ የእግር ኳስ ቡድኑን ይዞ ኢትዮጵያ ይገኛል

የሰውነት ቢሻው ከ17 ዓመት በታች አካዳሚ ከትውልደ ኢትዮጵያዊው አሸናፊ ግርማ የካናዳ የእግር ኳስ አካዳሚ ጋር የወዳጅነት ውድድር አደረገ።

የእግር ኳስ ልምድ ልውውጥን ዓላማ ያደረገው ይህ ውድድር የአካዳሚው ታዳጊዎች በስልጠና ያዳበሩትን ክህሎት በተግባር እንዲያሳዩ አግዟቸዋል።

የፊፋ የኤሊት የጨዋታ አመራሮች ስልጠና በዛሬው ዕለት መካሄድ ጀምሯል።

በስልጠናው መክፈቻ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ብሔራዊ የዳኞች ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ሸዋንግዛው ተባባል ባደረጉት ንግግር “የአካል ብቃት ምዘናውን በስኬት አልፋችሁ እዚህ በመገናኘታችን ደስ ብሎኛል። ሁለቱን ኢንስትራክተሮች በማግኘታችን በእውነት እድለኞች ነን፤ እናንተ ከፊፋ ከፍተኛ አሰልጣኞች መካከል ግንባር ቀደም ናችሁ። ስለዚህ ዳኞች ከዚህ ኮርስ እስከ ጥግ እንዲጠቀሙበት እመክራለሁ፤ ማድረግ የምትችሉትን ያህል ከፍተኛ ጥረት አድርጉ። ጥሩ እና አዝናኝ አምስት ቀናት ይኖረናል ብዬ አስባለሁ፤ መልካሙን ሁሉ እመኝላችኋለሁ” ብለዋል።

የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ለሴካፋ ማጣሪያ ቅድመ ዝግጅት ጀምረ

በታንዛንያ አስተናጋጅነት በሚካሄደው ከ20 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ የሴካፋ ማጣሪያ ውድድር የሚሳተፈው የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ለውድድሩ ቅድመ ዝግጅት ጥሪ የተደረገላቸው 40 ተጫዋቾችን በመያዝ በዛሬው ዕለት ናሽናል ካምፒንግ ጀመራ’ሯል።

የአፍሪካ ዋንጫ የማዘጋጀት ሰነድ ማዘገባትና የመጀመሪያ የማጣሪያ ጨዋታ

ኢትዮጵያ የ2028ቱን የአፍሪካ ዋንጫ ለማስተናገድ ጥያቄዋን ያቀረበችበት ሰነድ (Bid Document) ለአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) አስገባች

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከኢፌዴሪ መንግሥት ጋር በጋራ አስፈላጊ ዶክመንቶችን ያካተተ ሰነድ (BID HAND BOOK) ለካፍ በማስገባት ይህንን ታላቅ አህጉራዊ የእግር ኳስ ድግስ ለአራተኛ ጊዜ በስኬት ለማስተናገድና በአፍሪካ እግር ኳስ ያላትን ጉልህ ታሪክ ዳግም ለማደስ ዝግጁነቷን አረጋግጣለች።

አቶ ኢሳያስ ጅራ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንታዊ ተወዳዳሪነት የቀረቡ ብቸኛ ዕጩ መሆናቸው ተገለጸ

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የምርጫ አስፈፃሚ ኮሚቴ ሐምሌ 22 ቀን 2018 ዓ.ም ለፌዴሬሽኑ የጠቅላላ ጉባኤ አባላት በላከው ደብዳቤ መስከረም 5 ቀን 2019 ዓ.ም ለሚደረገው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንታዊ እና በፕሬዝዳንቱ አቅራቢነት የሚመረጡ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ከነተጠባባቂያቸው በፌዴሬሽኑ መተዳደሪያ ደንብ መሰረት እስከ ነሐሴ 4 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ለፌዴሬሽኑ ጽ/ቤት እንዲልኩ ማሳወቁ ይታወሳል፡፡

የኢትዮጵያ የፕሪምየር ሊግ የዝውውር እንቅስቃሴዎች

የአዳማ ከተማ እና የኢትዮጵያ መድን (በተለምዶ ኢንሹራንስ) የዝውውር እንቅስቃሴዎች ለአዲሱ የውድድር ዘመን ክለቦቹን ጠንካራ ተፎካካሪ ለማድረግ ያለሙ ትልልቅ እርምጃዎች እየሰሩ ነው።

ስለ እነዚህ ክለቦች ዝውውሮች እና ስለ ክለቦቹ አዲስ መዋቅር ፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከሴኔጋል ብሔራዊ ቡድን ጋር በባህር ዳር ስታዲየም ማክሰኞ መስከረም 19 ያደርጋል

ካፍ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ የሜዳው ጨዋታውን በባህር ዳር ስታዲየም እንዲያከናውን ጊዜያዊ ፈቃድ መሰጠቱ ይታወሳል።

በዚህም መሰረት በ2027 የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ 10 ሁለተኛ የምድብ ጨዋታውን ከሴኔጋል ብሔራዊ ቡድን ጋር በባህር ዳር ስታዲየም ማክሰኞ መስከረም 19/2019 ከቀኑ 10፡00 ላይ የሚያከናውን ይሆናል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሴቶች እግር ኳስ ቡድን ለአህጉራዊው የካፍ ሴቶች ሻምፒዮንስ ሊግ ዝግጅት እያደረገ ነው

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሴቶች እግር ኳስ ቡድን ለአህጉራዊው የካፍ ሴቶች ሻምፒዮንስ ሊግ (CAF Women’s Champions League) የሴካፋ ዞን ማጣሪያ ውድድር የመጨረሻ ዝግጅቱን እያደረገ ይገኛል። በሩዋንዳ ኪጋሊ አስተናጋጅነት ከነሐሴ 16 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ በሚካሄደው የሴካፋ (CECAFA) ማጣሪያ ውድድር ላይ ንግድ ባንክ ጠንካራ ምድብ ውስጥ የተደለደለ ሲሆን፣ ዝግጅቱን ያወካው ዋነኛው ፈተና የአንዳንድ ቁልፍ ተጫዋቾች በጉዳት መያዝ ነው።

የባህር ዳር ስታዲየም ለአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ጨዋታ ጊዜያዊ ፈቃድ አገኘ

የባህር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም የካፍ (CAF) እና የፊፋ (FIFA) ዝቅተኛ መስፈርቶችን ባለማሟላቱ ተጥሎበት የነበረው ዓለም አቀፍ እገዳ በይፋ ተነስቶለታል። ስታዲየሙ ዓለም አቀፍ የብሔራዊ ቡድን እና የክለቦች ጨዋታዎችን እንዲያስተናግድ በካፍ በኩል ሙሉ እውቅና እና ፍቃድ አግኝቷል።

የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) በቅርቡ በባህር ዳር ስታዲየም ላይ ያደረገውን ፍተሻ እና ግምገማ  ተከተሎ ብሄራዊ ቡድናችን በመስከረም ወር 2019 በሜዳው ለሚያደርገው ጨዋታ የሚያገለግል ጊዜያዊ የካቴጎሪ 3 (CAT 3) ፈቃድ መስጠቱን ዛሬ ለኢ/እ/ፌ በላከው ደብዳቤ አስታውቋል። ይህ ጊዜያዊ ፈቃድ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የሚጠብቀውን የ2027 የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የሜዳው ጨዋታን በሀገሩ እንዲያደርግ ያስችለዋል። 

ቅዱስ ጊዮርጊስ ከአንድ ትልቅ አለም አቀፍ ኩባንያ ጋር ስለሚያደርግእው የስፖንሰርሺፕ ስምምነትና ስለሚያደርገው የወዳጅነት ጨዋታ

  የኢትዮጵያ እግር ኳስ ታላቁ  ክለብ ቅዱስ ጊዮርጊስ (ፈረሰኞቹ) አዲስ አሰልጣኝ በመሾም እና ሰፊ የተጫዋቾች ስብስብ መልሶ ግንባታ (Squad Rebuild) በማድረግ ላይ ይገኛል። ክለቡ በፊፋ (FIFA) የዝውውር እገዳ ቢጣልበትም፣ ለቀጣዩ የ2019 ዓ.ም. (2026/27) የውድድር ዘመን እራሱን እያዘጋጀ ይገኛል።

አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳሕሌ ለ39 ተጫዋቾች ጥሪ አደረጉ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በመጪው መስከረም ወር ለሚያደርጋቸው የ2027 የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ የምድብ 10 የመጀመርያ ሁለት ጨዋታዎች ዝግጅት አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳሕሌ ለ39 ተጫዋቾች ጥሪ አድርገዋል። ጥሪ ከተደረገላቸው ተጫዋቾች መካከል ከ20 ዓመት በታች ናሽናል ካምፕ ላይ የሚገኙ 6 ተጫዋቾች ተካተዋል።

የኢትዮጵያ ክለቦች ሻምፒዮና የሴቶች ውድድር በኢትዮጵያ ቡና አሸናፊነት ፍፃሜውን አግኝቷል

ውድድሩ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት፣ የካፍ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ እና የፊፋ ቋሚ ኮሚቴ አባል አቶ ኢሳያስ ጅራ ፣ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የውድድር ዳይሬክተር አቶ ከበደ ወርቁ ፣ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የከፍተኛ ሊግ ሰብሳቢ አቶ ሙራድ አብዲ ፣ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል አቶ ሸረፋ ዴሌቾ እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በድሬዳዋ ስታዲየም ፍፃሜ አግኝቷል።

በስዊድን ጎተንበርግ በተካሄደው ውድድር ላይ ተካፋይ ስለነበሩትና በዛው ስለቀሩ የእግር ኳስ ተጨዋቾች ጉዳይ ምን አዲስ ነገር አለ

በዓመታዊው የጎቲያ ካፕ ውድድር ላይ ለመካፈል በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ስም ወደ ስዊድን አምርተው 7ለ0 ከተሸነፉ በኋላ ሀገራቸውን የከዱት ኳስ ተጨዋችች  በፖሊስ ተያዙ።

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የቡድኑ አባላት መጥፋት ያሳዘነው መሆኑን ገልጾ ታዳጊ ቡድኖች በመሰል ውድድሮች ላይ በራሳቸው ጥረት በሚያገኙት እድል ወደ ውድድሩ የሚያመሩ እንጂ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን የወከሉ አለመሆኑን መግለጹ ይታወሳል።

ሀላባ ከነማ የወሳኝ ተጨዋቾችን ውል እያራዘመ ነው

በትላንትናው ዕለት ወደ ተጫዋቾች ዝውውር ገበያ በስፋት በመግባት የአምስት አዳዲስ ፈራሚዎችን ዝውውር ማጠናቀቃቸውን ያበሰሩት በአሰልጣኝ በሽር አብደላ የሚመሩት «በርበሬዎቹ»፣ በዛሬው ዕለት ደግሞ የወሳኙን የመስመር አጥቂ የዮናታን ሐይሉን ውል ማራዘማቸውን ይፋ አድርገዋል።

​በዝውውር መስኮቱ ከተለያዩ የሀገራችን ክለቦች ጋር ስሙ በተደጋጋሚ ሲያያዝ የቆየው የቀድሞው የደደቢት መስመር አጥቂ፤ በ2018 በከፍተኛ ሊጉ ወደ አዲሱ ምዕራፍ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ባሳደገው ምርጥ የሚባል ግዜ ባሳለፈው ክለቡ ሀላባ ከነማጋር ለመቀጠል በመስማማት አዲሱን ውሉን አራዝሟል።

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽንናየተጫዋቾቹ የ100 ዶላር ውዝግብ

ከአራት ወራት በፊት የአውሮፓ እግርኳስ ማህበር በፍሬንዲሽፕ ካፕ ብትሳተፉልን ብሎ ለኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ግብዣ ላከ፤ ፌዴሬሽኑም ጥሪውን ተቀበለ፤ የኢትዮጵያ ከ18 አመት በታች ሴቶች ብሄራዊ ቡድን 30 ልዑካንን ይዞ ወደ አዘጋጇ ሃገር ቱርኪዬ ሄደ፤ ቡድኑ ከኡራጋይ፣ ኮስታሪካና ኖርዌይ ጋር ተደለደለ፤ በመጀመሪያ ጨዋታው ኡራጋይን 3-0 አሸነፈ፤ በሁለተኛው ኮስታሪካን 1-0 ረታ፤ በሶስተኛው የምድብ ጨዋታ በኖርዌይ 1-0 ተሸነፈ፤ በመጨረሻም በአዘጋጇ ቱርኪዬ 3-1 ተሸንፎ ከስምንት ሃገራት አራተኛ ሆኖ አጠናቀቀ

ስዊዲን ላይ የጠፉት ተጨዋቾች የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን እንዳላካቸው ገለጸ

በዓመታዊው የጎቲያ ካፕ ውድድር ላይ ለመካፈል ወደ ስዊድን ያመሩ ታዳጊዎች እና የቡድን አባላት በስዊድን መጥፋታቸውን አስመልክቶ የተለያዩ መረጃዎች እየወጡ ይገኛሉ።

በጉዳዩ ዙርያ ምላሽ ወይም ማብራርያ በተመለከተ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለቀረበለት ጥያቄ በሰጠው ምላሽ 

ንግሥት በቀለ በፈረንሳዩ ክለብ ሜትዝ ሙከራ እያደረገች ትገኛለች

የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን አጥቂ የሆነችው ንግስት በቀለ በአውሮፓ የሙከራ ዕድል ተሰጧት በፈረንሳዩ የሴቶች ሁለተኛ ሊግ ክለብ ኤፍ ሲ ሜትዝ (FC Metz) የሙከራ ዕድል ተሰጥቷት ፈረንሣይ እንደምትገኝ ተገልጿል ።
‎
‎ለተጫዋቿ የሙከራ ዕድል የሰጣት ክለብ ሜትዝ በአሁኑ ወቅት በ2ተኛው የሊግ እርከን በመሳተፍ ላይ የሚገኝ እና በ1974 የተመሰረተ ሲሆን ባለፈው የውድድር ዓመት 12ኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቋል ፤ የሴቶች እግር ኳስ ከፍተኛ ትኩረት በሚሰጥበት ፈረንሳይ ውስጥ የሚገኝ አንጋፋ ክለብ ነው።

ፍፁም ጥላሁን ከቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ መውጫ በር ላይ ቆሟል

የኢትዮጵያ ብ/ቡድን እና የቅዱስ ጊዮርጊስ ድንቁ የፊት መስመር ተጫዋች የሆነው ፍፁም ጥላሁን ውሉ ማለቁን ተከትሎ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር እስከ አሁኗ ሰዓት ድረስ ንግግር ያላደረገ ሲሆን ምን አልባት ነገሩ በዝህ ከቀጠለ ከፈረሰኞቹ ጋር ሊለያይ ይችላል ተብሏል ።

የቀድሞ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድንና የቡና ተጨዋች የሆነው አንዳርጋቸው በፌስቡክ ላይ እንደገለጸው ፍፁም ጥላሁን የዘንድሮ አመት የፕሪሚየር ሊጉ ድንቅ ተጫዋች ከመሆን አልፎ በብ/ቡድን ከማላዊ ጋር በነበረው ጨዋታ አንድ ጎል በማግባት እና አንድ አሲስት በማድረግ ምርጥ ኳሊቲ እንዳለሁ ገልጿል ።

የታዳጊና የወጣት ብሔራዊ ቡድንን የሚወክሉትን ተጨዋቾች ፌዴሬሽኑ ሊመለምል ነው

ለአፍሪካ ዋንጫ ለሴካፋ ዞን የታዳጊዎች የማጣርያ ውድድር ብሔራዊ ቡድኑን የሚወክሉትን ተጨዋቾች ለመመልመል ሥራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ገለጸ ።

ፌዴሬሽኑ እንዳለው በቀጣይ ዓመት መጀመርያ ለሚካሄዱት ከ17 እና ከ20 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ ሴካፋ ዞን የማጣርያ ውድድሮች ለሁለቱም የዕድሜ እርከን ብሔራዊ ቡድኖቻችን ብቁ የሚሆኑ ተጫዋቾችን ለመለየት እንዲያስችል የናሽናል ካምፒንግ የመጀመርያ ምዕራፍ ዛሬ ተጀምሯል ብሏል።

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የዝውውርና የምዝገባ ጊዜ አራዘመ

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የ2019 የውድድር ዘመን የተጫዋቾች ዝውውር እና ምዝገባ ጊዜ ላይ የቀን ማሻሻያ ማድረጉን ፌዴሬሽኑ አሳወቀ።

በዚህም መሠረት የዝውውር ጊዜ እና ምዝገባው ሐምሌ 30/2018 የሚጀምር ሲሆን እስከ መስከረም 20/2019 ድረስ ክፍት ሆኖ ይቆያል ።

የካናዳ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋች አሊ አህመድ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጽ/ቤት ጎበኘ

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ባሕሩ ጥላሁን ለትውልደ ኢትዮጵያዊው የካናዳ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋች አሊ አህመድ ወሎ ሰፈር የሚኘው የፌዴሬሽኑ ጽ/ቤት አስጎብኝተዋል፡፡

ዋና ሥራ አስፈፃሚው በጉብኝቱ ወቅት ከአሊ አህመድ ጋር ባደረጉት ቆይታ ኢትዮጵያ በአፍሪካ እግር ኳስ ላይ ስለተጫወተችው ጉልህ ሚና ፤ የአፍሪካ ዋንጫ እና ካፍን ከመመስረት አንስቶ ውድድሩን በማስተናገድ እና ዋንጫ በማንሳት የነበራትን ታሪክ፣ በኢ/እ/ፌ በዋና ፀሐፊነት እንዲሁም የካፍ ኘሬዝዳንትነት ለረጅም ዓመት የመሩት የአፍሪካ እግር ኳስ አባት ክቡር አቶ ይድነቃቸው ተሰማ በካፍ ላይ የነበራቸው ታላቅ አበርክቶ ምን እንደነበረ እንዲሁም አሁን ካፍ ለያዘው ቅርፅ የነበራቸውን ወሳኝ ሚና አስረድተዋል።

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን የብሔራዊ የዳኞች ኮሚቴ የቀድሞ አንጋፋ የዳኝነት ሙያተኞችን እውቅና ሰጠ

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ብሔራዊ የዳኞች ኮሚቴ በሀገራችን የዳኝነት ሙያ ላይ ላበረከቱት የላቀ አስተዋፅኦ፣ ለፈፀሙት ታላቅ አገልግሎት እና ለሙያው እድገት ላበረከቱት ዘላቂ አሻራ ለሁለት አንጋፋ የቀድሞ የዳኝነት ሙያተኞች ኢንስትራክተር ሽፈራው እሸቱ እና ኃይለመላክ ተሰማ እውቅና ሰጥቷል።

በዳኝነት ሙያ ለብዙ ዓመታት በታማኝነት፣ በሙያዊ ብቃት እና በከፍተኛ ቁርጠኝነት ያገለገሉት እነዚህ አንጋፋ ባለሙያዎች የዳኝነት ሙያን በማሳደግ፣ የተሻለ የዳኝነት ባህል በመገንባት እና ለቀጣዩ ትውልድ አርአያ በመሆን የማይረሱ አስተዋፅኦዎችን አበርክተዋል።

በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የፀደቁ ውሎች

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የሴቶች ፕሪምየር ሊግ የዝውውር ውሎችን አጽዱቋል ፤መብራት ኃይል ኤርሚያስ አማረን ለሁለት አመት አሰልጣኝ አድርጎ ሾሟል ፤ከዚህ ሌላ ቡድኑ በርካታ ተጨዋቾችን አስፈርሟል፤መብራት ኃይል ና ንግድ ባንክ አዳዲስ ተጨዋቾችን አስፈርመዋል፤ውላቸው የጸደቀላቸውን ተጨዋቾች በፎቶ ይመልከቱ

«ሀገሬን በአለም ዋንጫ መወከል እፈልጋለሁ »ከነአን

ከነአን ማርክነህ በሜዳ ላይ ባለው ታታሪነትና ግብ የማግባት ብቃቱ የሚታወቅ፣ በሀገር ውስጥ እንደ ቅዱስ ጊዮርጊስና መቻል ባሉ ትልልቅ ክለቦች ተጫውቶ ካሳለፈ በኋላ አሁን ላይ ፕሮፌሽናል ህይወቱን በውጭ ሀገራት እያሳለፈ የሚገኝ ድንቅ ተጫዋች ነው።
‎
‎ከሊቢያና ኦማን ቆይታው በኋላ ወደ ኩዌቱ አል አራቢያ ስፖርት ክለብ ከማምራቱ በፊት ኤፍ ኤም አዲስ 97.1 መሰንበቻ ፕሮግራም ስለ እግር ኳስ ህይወቱና ስለ ወደፊት አላማው ጠይቆት የሚከተለውን ብሏል።

ሲዳማ ቡና የአምበሉን ያሬድ ባየህ ጨምሮ የወሳኝ ተጫዋቹን ውል አራዘመ

በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግን በውድድር ዘመኑ ማሸነፍ የቻሉት ሲዳማ ቡናዎች፤ የወሳኝ ተጫዋቾቻውን ውል ለማራዘም እንቅስቃሴ ጀምረዋል።

ኢቲቪ ከክለቡ ባገኘው መረጃ መሰረትም የቡድኑ አምበል እና የሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ኮከብ ተጫዋቹን ያሬድ ባየህን ውል ለተጨማሪ ሁለት ዓመት ለማራዘም ከስምምነት ደርሷል።

ሲዳማ ቡና የተጨዋቾች የደሞዝ ሪከርድ ሰበረ?

የኢትዬጵያ ፕሪሚየር ሊግ የተጨዋቾች የዝውውር መስኮት በይፋ ከመከፈቱ አስቀድሞ ክለቦች በተጨዋቾች እና በአሰልጣኞች ዝውውር ተጠምደዋል።

ኢትዬጵያ ቡና እና መቻል የአሰልጣኝ ለውጥ በማድረግ ገብረመድህን ሃይሌ እና ውበቱ አባተን ቀጥረዋል።

ወላይታ ድቻ ደግሞ የአሰልጣኝ መሳይ ተፈሪን ውል ያራዘመ ሲሆን በቀጣዬቹ ቀናት የአሰልጣኝ ለውጥ አድርገው የሚመጡ ክለቦች መኖራቸው ርግጥ ሆናል።

የጨዋታ አመራሮችን ክብርና ደህንነት መጠበቅ የሁላችንም ኃላፊነት ነው ሲል ኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ብሔራዊ የዳኞች ኮሚቴ ገለጸ

ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በተለያዩ የእግር ኳስ ውድድሮች ላይ በጨዋታ አመራሮች ላይ የሚፈጸሙ አካላዊ ጥቃቶችን የሚያሳዩ ምስሎች በተለያዩ የማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች በስፋት ሲሰራጩ እየተመለከትን እንገኛለን። እነዚህ አሳዛኝ ድርጊቶች በወቅቱ፣ በጥብቅ እና በተቀናጀ መልኩ መቆጣጠር ካልተቻለ በእግር ኳሳችን ላይ የሚያስከትሉት ጉዳት ከፍተኛ ነው።

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዝውውር መስኮት እንደተጠጠፈ ነው

የ2018 የውድድር ዓመት መጠናቀቁን ተከትሎ፣ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ይፋዊ የክረምት የዝውውር መስኮት ከሐምሌ 20/2018 ዓ.ም. ጀምሮ በይፋ መከፈቱን አረጋግጧል። በዚህም መሰረት  የሊጉ የውድድር ዓመት መጠናቀቁን ተከትሎ፣ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ክለቦች በአሁኑ ወቅት በከፍተኛ የዝውውር

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን (ዋሊያዎቹ) ትኩረቱን የአፍሪካ ዋንጫ ላይ አድርጓል

ዋሊያዎቹ ለ2026 የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ የነበራቸውን ጨዋታዎች ካጠናቀቁ በኋላ፣ አሁን ሙሉ ትኩረታቸውን ወደ 2027 የአፍሪካ ዋንጫ (AFCON) ማጣሪያ ጨዋታዎች ዝግጅት አዙረዋል። የቡድኑን የማጥቃት መስመር ለማጠናከር አዳዲስ ወጣቶች ወደ ስብስብ እየገቡ ይገኛል።

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በአሰልጣኝ ውበቱ አባተ እና በመሳይ ተፈሪ ምትክ የሚሆን አዲስ ዋና አሰልጣኝ አድርጎ ዮሐንስ ሳሕሌን ለ2 ዓመታት ውል መሾሙ አይዘነጋም ። አሰልጣኝ በለጠ ገብረኪዳን በምክትልነት፣ መሐመድ ጀማል ደግሞ በግብ ጠባቂዎች አሰልጣኝነት አብረው  እየሰሩ ይገኛሉ።

አሰልጣኝ ውበቱ አባተ መቻልን በመረከብ አዳዲስ ተጫዋቾችን በማስፈረም ጠንካራ ቡድን ለመገንባት አስቧል

ውበቱ አባተ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ስር ታዋቂ ክለቦችን እንዲሁም ብሔራዊ ቡድኑን በማሰልጠን ትልቅ ልምድ ያካበተ አንጋፋ አሰልጣኝ ነው።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን (ዋሊያዎችን) በመምራት ቡድኑ ለ2021 ለካሜሩን የአፍሪካ ዋንጫ እንዲያልፍ አስችለዋል፤በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ እንደ ቡና፣ ፋሲል ከነማ እና ሌሎች በርካታ ክለቦችን አሰልጥነዋል።

በሱዳን፣ ደቡብ ሱዳን (እንደ ጃሙስ ኤፍሲ) እና በላይቤሪያ ሊጎች ውስጥም በመስራት ዓለም አቀፍ ልምድ አግኝተዋል。