ቼልሲ እንግሊዛዊውን የአስቶን ቪላ የፊት መስመር ተጫዋች በ117 ሚሊዮን ፓውንድ የዝውውር ዋጋ ማስፈረሙ ታውቋል ። ይህም ዝውውር ለብሪታንያ ተጫዋች የተከፈለ ከፍተኛው የዝውውር ክብረ ወስን ያደርገዋል። 


ሮጀርስ በስታምፎርድ ብሪጅ እስከ ሰኔ 2032 የሚያቆየውን የ6 ዓመት ውል የፈረመ ሲሆን፣ ውሉ ለተጨማሪ አንድ ዓመት (እስከ 2033) ሊራዘም የሚችልበት የውል አማራጭ አለው።
ተጫዋቹ ከእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ጋር በዓለም ዋንጫው ላይ ከተሳተፈ በኋላ ወደ ለንደን ተመልሶ ሰኞ ዕለት የህክምና ምርመራውን በተሳካ ሁኔታ አጠናቆ ፊርማውን አኑሯል።

 የቼልሲው አዲስ አሰልጣኝ ዣቪ አሎንሶ ተጫዋቹን በስልክ በማነጋገር ወደ ክለቡ እንዲመጣ በማሳመን ረገድ ከፍተኛ ሚና ተጫውተዋል።

 አርሰናል ተጫዋቹን ለማስፈረም ቀዳሚው ፈላጊ እና ተፎካካሪ የነበረ ቢሆንም፣ ቼልሲ ያቀረበውን ከፍተኛ የገንዘብ መጠን ለመክፈል ባለመፈለጋቸው ዝውውሩን በቼልሲ ተነጥቀዋል።

አርሴናል ከተጫዋቹ ጋር በግል ጥቅማጥቅሞች ላይ ቢስማማም፣ ከአስቶን ቪላ ጋር መደበኛ ድርድር ሳይጀምር በመዘግየቱ ቼልሲ ዝውውሩን በብልጠት አጠናቋል።

ስምምነቱ እንዲቋረጥ ያደረጉ ዋንኛ  ምክንያቶች  አስቶን ቪላ ለተጫዋቹ ከ100 ሚሊዮን ፓውንድ በላይ ከፍተኛ ዋጋ ይፈልግ  ስለነበር አርሴናል  ግን የዝውውር ዋጋው ከ90-100 ሚሊዮን ፓውንድ በላይ እንዲሆን ባለመፈለጉና የዓለም ዋንጫው እስኪያልቅ ድረስ ሂደቱን በማዘግየቱ የተነሳ፣ ቼልሲ በእንግሊዝ የእንግሊዝ ተጨዋቾች ትልቁ የዝውውር ዋጋ በሆነው  በ117 ሚሊዮን ፓውንድ ሂሳብ ዝውውሩን በአስገራሚ ፍጥነት ዝውውሩን አጠናቋል ።
አርሴናል ሮጀርስን ቁጥር አንድ ኢላማው አድርጎ ቢይዘውም፣ በተመሳሳይ ሰዓት እንደ ጁሊያን አልቫሬዝ እና ብራድሌይ ባርኮላ ካሉ ሌሎች ተጫዋቾች ጋር ስሙ መያያዙ በሮጀርስ ወገን ላይ “እውነት እሱን ብቻ ነው የሚፈልጉት?” የሚል የጥርጣሬ ስሜት ፈጥሮ ነበር። ቼልሲ ግን ሙሉ ትኩረቱን እሱ ላይ ብቻ በማድረጉ ተጫዋቹ የቼልሲን ፕሮጀክት መርጧል።

ቼልሲው አዲስ አሰልጣኝ ዣቪ አሎንሶ ለሞርጋን ሮጀርስ በስልክ በመደወል ለክለቡ ስላለው እቅድ እና ተጫዋቹ በቡድኑ ውስጥ ስለሚኖረው ቁልፍ ሚና በግልፅ አብራርቶለታል። ይህም ተጫዋቹ ሃሳቡን እንዲቀይር ትልቅ ተጽዕኖ ፈጥሯል።

በቼልሲ ቤት የሚገኙት የቅርብ ጓደኛው ኮል ፓልመርና የቡድኑ ካፒቴን ሪስ ጄምስ፣ በእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ካምፕ ውስጥ በነበሩበት ወቅት ወደ ቼልሲ እንዲመጣ ከፍተኛ ግፊት አድርገዋል ተብሏል።

አርሴናል በሮጀርስ ዝውውር መክሸፍ ምክንያት አሁን ፊቱን ወደ ሌላ አማራጭ ተጫዋቾች ማዞሩ ተሰምቷል።
ሪስቶስ ትዞሊስ (Christos Tzolis)፦ አርሴናል ከፎርዋርዱ ጋር በ34 ሚሊዮን ፓውንድ ሙሉ ስምምነት ላይ የደረሰ ሲሆን ዝውውሩ በቅርቡ በይፋ ይታወቃል።
ሌላው ብራድሌይ ባርኮላ (Bradley Barcola) ከፓሪስ ሳንዠርሜን (PSG) ፈጣኑን የግራ መስመር ተጫዋች ለማስፈረም አርሴናል እንደ ዋና አማራጭ እየተመለከተው ይገኛል። አሁን የተሰማው  ወሬ የግራ ክንፍ ተጨዋች ፍለጋ ላይ ሲሆን ከኒኮ ዊሊያምስ ጋር አዲስ ግንኙነት መጀመራኡ ተዘግቧል

አንድሪያ ቤርታ በአሁኑ ወቅት ለኒኮ ዊሊያምስ ለሚደረገው ስምምነት  የውል ማፍረሻ ውል 77 ሚሊዮን ፓውንድ አካባቢ ለማቅረብ እንደተዘጋጀ ተነግሯል።
ከዚህ ሌላ ጆን ስቶንስ (John Stones) በነጻ ዝውውር (Free Agent) ለማስፈረም እንግሊዛዊውን ተከላካይ ጆን ስቶንስን ለማስፈረም አርሴናል ንግግር ጀምሯል።

Facebooktwitterlinkedinyoutubetumblrinstagramflickrfoursquaremail
Facebooktwitterredditpinterestlinkedintumblrmail

By admin

Hello, dear. I am Wosenseged Mersha Demissie. Author, Journalist, and Sociological Criticism. He has worked in several media in Ethiopia and foreign media also. I have come to my country, Ethiopia, from abroad, and for the past eight years, I have been giving political analysis and writing in magazines, newspapers, and televisions on all the free press in Ethiopia. I have six books that I wrote and published during my stay abroad and after I came back to my country and are on the market. Above all, I feel spiritual satisfaction for coming from a developed country and working in a country where there is no freedom of the press. I have sacrificed a lot in this profession. Imprisonment, abuse—I was crushed economically. I have been living separately from my family for many years, but I am happy and proud of my career to be a voice for the voiceless people of Ethiopia, whom I love and respect by working in the press without payment. After leaving my country and returning to my country, Growing up in Arat Kilo, YMCA, I was exposed to various sports. I know many sports. I have worked as a referee, player, and tournament organizer. As a result, I have worked as a sports editor on radio, television, and newspapers for many years. I have worked alongside other media outlets for more than 20 years by preparing and publishing my own sports newspaper called San George.I have traveled to many countries, including Europe, the Far East, Asia, Oceania, and Africa, and have been present at many competitions, including athletics.This is because I have this love for sports. I have reopened this media outlet for sports. In addition to this, I have worked for the past 30 years. May God protect Ethiopia and its people and give peace and love to our world. Thank you anyway. Wosenseged Mersha Demissie Author, Journalist, Sociological Criticism

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *