የኢትዮጵያ ክለቦች ሻምፒዮና የሴቶች ውድድር በኢትዮጵያ ቡና አሸናፊነት ፍፃሜውን አግኝቷል።

0
IMG_20260802_094241_522

ውድድሩ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት፣ የካፍ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ እና የፊፋ ቋሚ ኮሚቴ አባል አቶ ኢሳያስ ጅራ ፣ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የውድድር ዳይሬክተር አቶ ከበደ ወርቁ ፣ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የከፍተኛ ሊግ ሰብሳቢ አቶ ሙራድ አብዲ ፣ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል አቶ ሸረፋ ዴሌቾ እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በድሬዳዋ ስታዲየም ፍፃሜ አግኝቷል።

በፍፃሜው ጨዋታ ኢትዮጵያ ቡና 1-0 ምድረገነት ሽረን በሳሚያ ሬድዋን 46ኛ ደቂቃ ላይ ባስቆጠረችው ግብ ማሽነፍ ችሏል።

የውድድሩ ኮከቦች ሽልማት

  • ኮከብ ተጨዋች
    ወርቅነሽ ፋሮ ከኢትዮጵያ ቡና
  • ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ
    ሳሚያ ሬድዋን ከኢትዮጵያ ቡና
  • ኮከብ ግብ ጠባቂ
    ብዙዓየሁ ደጀኔ ከኢትዮጵያ ቡና
  • ኮከብ አሰልጣኝ
    ቶሎሣ ብርብርሳ ከኢትዮጵያ ቡና

-የስፖርታዊ ጨዋነት ዋንጫ አሸናፊ ጅማ ከተማ

Facebooktwitterlinkedinyoutubetumblrinstagramflickrfoursquaremail
Facebooktwitterredditpinterestlinkedintumblrmail