
ዲጄድ ስፔንስ ወደ ኢንተር ሚላን፦ የቶተንሃሙ ተከላካይ ዲጄድ ስፔንስ በ30 ሚሊዮን ፓውንድ ዝውውር ወደ ጣሊያኑ ታላቅ ክለብ ኢንተር ሚላን ዝውውሩን በይፋ አጠናቋል።
አማር ዴዲች ወደ ኒውካስል ዩናይትድ፦ ኒውካስል ዩናይትዶች የቤንፊካውን የ23 ዓመት የቀኝ መስመር ተከላካይ አማር ዴዲች በ30 ሚሊዮን ፓውንድ ለማስፈረም ከክለቡ ጋር የላቀ ድርድር ላይ ደርሰዋል።
ዳያን ሜታሊ ወደ ሳንደርላንድ፦ የ20 ዓመቱ የቱሉዝ የግራ መስመር ተከላካይ ዳያን ሜታሊ በ30 ሚሊዮን ዩሮ የሪከርድ ዋጋ ወደ እንግሊዙ ሳንደርላንድ ለመዛወር ሙሉ ስምምነት ላይ ደርሷል።

የፈራን ቶሬስ ወደ ፒኤስጂ (PSG) መጓዝ፦ ስፓኝያዊው የባርሴሎና አጥቂ ፈራን ቶሬስ በ50 ሚሊዮን ዩሮ ዝውውር ወደ ፈረንሳዩ ፒኤስጂ ለመዘዋወር ሙሉ ስምምነት ላይ ደርሶ ወደ ፓሪስ አቅንቷል።
ክሪስቲያን ሮሜሮ ወደ አትሌቲኮ ማድሪድ፤የቶተንሃሙ የኋላ ደጀን ክሪስቲያን ሮሜሮ በ34.2 ሚሊዮን ፓውንድ ወደ ስፔኑ አትሌቲኮ ማድሪድ የ5 ዓመት ኮንትራት በመፈረም ዝውውሩን አጠናቋል።

ፍራንኪ ዴ ጆንግ በጋዜጠኞች ላይ ተቆጣ፤ የባርሴሎናው አማካኝ ፍራንኪ ዴ ጆንግ ስለ ጉዳቱ የተሳሳተ መረጃ በሚያሰራጩ ጋዜጠኞች ላይ ጠንከር ያለ ትችት ሰንዝሯል።
የኤንዞ ፈርናንዴዝ ጉዳይ፤ ማንቸስተር ሲቲ ለኤንዞ ፈርናንዴዝ ያቀረበውን የ120 ሚሊዮን ፓውንድ ሂሳብ ቼልሲዎች በሰጡት የጊዜ ገደብ ባለማጠናቀቃቸው ዝውውሩ መስተጓጎሉ ተሰምቷል።
