ካፍ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ የሜዳው ጨዋታውን በባህር ዳር ስታዲየም እንዲያከናውን ጊዜያዊ ፈቃድ መሰጠቱ ይታወሳል።
በዚህም መሰረት በ2027 የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ 10 ሁለተኛ የምድብ ጨዋታውን ከሴኔጋል ብሔራዊ ቡድን ጋር በባህር ዳር ስታዲየም ማክሰኞ መስከረም 19/2019 ከቀኑ 10፡00 ላይ የሚያከናውን ይሆናል።

በዚህም መሰረት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለ2027 የአፍሪካ ዋንጫ የመጀመርያ የምድብ ማጣርያ ጨዋታዎች የሚያደርገውን ዝግጅት ጀምሯል።

አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳሕሌ ጥሪ ያደረጉላቸው ተጫዋቾች ዓርብ ነሐሴ 8 በጁፒተር ሆቴል የተሰባሰቡ ሲሆን በትናንትናው ዕለት የስብ መጠን እና ተያያዥ ምርመራዎች በዶ/ር ኤልያስ አቢሻክራ አማካኝነት የተደረገለቻው ሲሆን በዛሬው ዕለት ደግሞ በአዲስ አበባ ስታዲየም የአካል ብቃት ምዘና ተከናውኗል።

ጥሪ ከተደረገላቸው ተጫዋቾች መካከል 31 ተጫዋቾች በስብስብ ውስጥ የሚገኙ ሲሆን የሲዳማ ቡና ተጫዋቾች እንዲሁም በውጪ ሀገር የክለቦች የሚገኙ ተጫዋቾች በቀጣይ ጊዜያት ብሔራዊ ቡድናችንን የሚቀላቀሉ ይሆናል።