
ኤሊዮት አንደርሰን ከኖቲንግሃም ፎረስት ወደ ማንቸስተር ሲቲ በ116 ሚሊዮን ፓውንድ ዝውውሩን አጠናቋል።
የእንግሊዙ አማካይ ተጫዋች ከፕሪሚየር ሊግ ክለብ ጋር የአምስት ዓመት ውል ለመፈራረም ተስማምቷል ፤ይህም እስከዛሬ ድረስ እጅግ ውዱ የእንግሊዝ እግር ኳስ ተጫዋች ቀዳሚው እንዲሆን አድርጎታል።

አንደርሰን በአሁኑ ጊዜ በእንግሊዝ የዓለም ዋንጫ እየተሳተፈ ነው የሚገኘው ። ብሔራዊ ቡድኑ ያደረጋቸውን ሦስቱንም ጨዋታ በቋሚነት ተሰላፊ ሆኖ ተጫውቷል፤ የሕክምና ምርመራውን ለማለፍና ሪከርድ የሰበረ ዝውውር ለማጠናቀቅ እዛው ውድድር ቦታ ሆኖ እንደጨረስ ተነግሯል ።
ማንችስተር ሲቲ አንደርሰንን «በካንሳስ የሕክምና ምርመራውን እንዳጠናቀቀ አስታውቋል። ዝውውሩ ግን በመደበኛነት ወደ እንግሊዝ ሲመለስ ይጠናቀቃል» ብሏል።
የ23 ዓመቱ አማካይ ተጫዋች በ2024 ከኒውካስል ዩናይትድ ወደ ኖቲንግሀም ፎረስት በ35 ሚሊዮን ፓውንድ ብቻ በመዛወር በእንግሊዝ እግር ኳስ ውስጥ ካሉት በጣም ድንቅ ችሎታ ካላቸው አንዱ ለመሆን ችሏል።

አንደርሰን በኖቲንግሀም ፎረስት 92 ጨዋታዎችን አድርጓል፣ ይህም ክለቡ በሁለት አስርት ዓመታት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ አውሮፓ እግር ኳስ ሲመለስ በመጀመሪያው የውድድር ዘመኑ ሰባተኛ ደረጃን ይዞ እንዲጨርስ አስችሎት ነበር ።
ባለፈው የውድድር ዘመን ፎረስት በ16ኛ ደረጃ ላይ ይዞ እንዲጨርስና ከመውረድ ቡድኑን ታድጎታል ፤ ነገር ግን አንደርሰን በዩሮፓ ሊግ ግማሽ ፍፃሜ ላይ ቡድኑ ሲደርስ ቁልፍ ተጫዋች ነበር፣ በመጨረሻው ጨዋታ ቡድኑ በአሸናፊው በአስቶን ቪላ ነበር የተሸነፈው።
ማንችስተር ሲቲ ቀደም ሲል ከፍተኛ ገንዘብ በማውጣት ተጨዋቹን ለመግዛት አላንገራገረም፤ ይህ ደግሞ በእንግሊዝ እግር ኳስ ታሪክ ሪከርድ ሆኖ እንዲመዘገብ አስችሎታል ።ማንችስተር ሲቲ በ2021 ለአስቶን ቪላው ለጃክ ግሪሊሽ ያወጣው 100 ሚሊዮን ፓውንድ ሲሆን ይህም ቀደም ሲል ለአንድ እንግሊዛዊ ተጫዋች ከፍተኛ የዝውውር ክፍያ የተከፈለበት ሆኖ ነበር።
ማንችስተር ሲቲ ፔፕ ጋርዲዮላን በመተካት ኤንዞ ማሬስካን አዲሱ አሰልጣኝ አድርጎ መሾሙን ካወጀ ከጥቂት ቀናት በኋላ አንደርሰን የመጀመሪያው ቡድኑን ተቀላቃይ ሆኗል ።
አንደርሰን የተወለደው በታይኔሳይድ ሲሆን ለዚሁ የዎልስሴንድ ቦይስ ክለብ ተጫውቷል፤ ይህም የእንግሊዝ ብሄራዊ ቡድን ተጫዋነትን ጨምሮ የበርካታ ፕሮፌሽናል የእግር ኳስ ተጫዋች እንዲሆን አስችሎታል ።
ኒውካስትልን በስምንት ዓመቱ ነበር የተቀላቀለው፤ በጥር 2021 ከአርሰናል ጋር በነበረው የኤፍኤ ካፕ ሶስተኛ ዙር ጨዋታ ቡድኑ ሽንፈት ቢገጥመውም የመጀመሪያ ጨዋታውን አድርጓል፤ ከዚያም ከአንድ ሳምንት በኋላ ብዙም ሳይቆይ በኒውካጽትል ቡድን ውስጥ በፕሪሚየር ሊጉ ውድድር ላይ ተቀያሪ ሆኖ ተጫውቷል።
አንደርሰን ከአንድ አመት በኋላ በውሰት የሶስተኛ ደረጃ ብሪስቶል ሮቨርስን ተቀላቅሏል፤ በ21 ጨዋታዎች ሰባት ጎሎችን በማስቆጠር የሶስተኛ ደረጃን በመያዝ ቡድኑ ወደ ሊግ አንድ እንዲያድግ እረድቶታል።
«ወደ ፕሪምየር ሊጉ በመግባት ወዲያውኑ እምቅ ችሎታውን አሳይቷል። ምንም የሚያስደነግጠው ነገር አልነበረም። ይህ ልጅ ወዲያውኑ የተለየ መሆኑን ማየት ትችላላችሁ» ሲል በሮቨርስ ቡድን የተጫዋቹ-አሰልጣኝ የነበሩት የቀድሞው የአየርላንድ ሪፐብሊክ ኢንተርናሽናል ግሌን ዌላን ተናግረዋል ።
«አሰልጣኝ እንደመሆኔ መጠን በስልጠና ወቅት ትንሽ ጫና ውስጥ ለማስገባት ስሞክር የተወሰኑ ሁኔታዎች ነበሩ። አንዳንድ ልጆች ትንሽ የበለጠ ዝግምተኛ ይሆኑና ወደ ኋላ ይመለሳሉ። ኤሊዮት እንደዚህ አይደለም ። »
«ለሁሉም ሰው ምን ያህል ጥሩ እንደሆነ ለማሳየት በእሱ ላይ እምነት ነበረው። እብሪት አልነበረውም። ከቤተሰቡ ጥሩ አስተዳደግ እንደነበረውና ጂኦርዲ በእሱ ውስጥ እንደነበረ ግልጽ ነው።»
ወደ ኒውካስል ቡድን ተመልሶ በመጀመሪያው ቡድን ውስጥ ቋሚ አሰላለፍ ለመግባት ቢሞክርም አልተሳካላትም በ2024 የበጋ ወቅት ማግፒዎች የትርፍና የዘላቂነት ደንቦችን (PSR) ላለማፍረስ ሽያጭ እንዲያደርጉ ስለተገደዱ ተጨዋቹን መሸጥ ግድ ሆነባቸው ።
«እሱን ስንሸጠው የተጸጸትነው ነገር ነበር። ያ በጣም የሚያም ዝውውር እንደሚሆን እናውቅ ነበር» ሲሉ የኒውካስል አሰልጣኝ ኤዲ ሀው ተናግረዋል ። «ምንም ምርጫ አልነበረንም፣ ግን ምናልባት የማለው በጣም ቸልተኛነት የታየበት ዝውውር ሊሆን ይችላል።»ሲሉ አክለዋል።
በኖቲንግሀም ፎረስት አማካይ ሜዳ ላይ እራሱን እንደ ዋና ተጫዋች አድርጎ በማሳየት ችሎታውን ለማሳየት የበቃው አንደርሰን ፣ ለብሄራዊ ቡድን በመመረጥም ከሁንዱራስ ጋር በተደረገው የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ላይ ቡድኑ ድል ቀንቶት ሲወጣ የመጀመሪያውን ግብ ለእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን አስቆጠረ ።
« በመጀመሪያ ደረጃ፣ ለእንደዚህ አይነቱ ወጣት ተጫዋች አስደናቂ ተሰጥኦ ነው» ሲል በወቅቱ የኖቲንግ ሀም ፎረስት አሰልጣኝ ኑኖ ኤስፒሪቶ ሳንቶ በኖቬምበር 2024 ለስካይ ስፖርት ተናግረዋል። «እሱ ተወዳዳሪ ነው እራሱን ማሻሻል ይፈልጋል። ጥሩ እንደሆነ ያውቃል ግን የተሻለ መሆን ይፈልጋል። ይህ የመጀመሪያው እርምጃ ነው። እሱን በማግኘታችን በጣም ደስተኞች ነን። በጣም ጥሩ ስምምነት ያደረግን ይመስለኛል።»ብለዋል።
አንደርሰን በ2021 ወደ እንግሊዝ ዜግነቱን ከመቀየሩ በፊት ለስኮትላንድ የወጣት ብሔራዊ ቡድን ኢንተርናሽናል ተጫዋች ሆኖ ነበር፤ ይህም ብሔራዊ ቡድኑን በ2025 ከ21 ዓመት በታች የአውሮፓ ሻምፒዮናን እንዲያሸንፉ ረድቷል፤ በዚህም ብቃቱ በውድድሩ ቡድን ውስጥ ቦታ እንዲያገኝ አስችሎታል።
የመጀመሪያ ደረጃውን የእንግሊዝ አሰልጣኝ ቶማስ ቱሀል፣ ስለ ተሰጥኦው ምንም ጥርጥር የላቸውም። «እሱ ምርጥ ተጫዋች ነው» ሲሉ ጀርመናዊው አሰልጣኝ ከዓለም ዋንጫው በፊት ተናግረዋል። «ከዚህ በላይ የሚነገር ነገር የለም፣ እሱ ሁሉንም ያሟላ ተጨዋች ነው። በዚያ ደረጃ ከእኛ ጋር በመሆኑና ለእኛ ቁልፍ ተጫዋች በመሆኑ ደስተኞች ነን።»ሲሉ ተናግረዋል።
ስለዚህ ግዙፍ የእንግሊዝ ውድ ተጨዋች ስምምነት ምን ያስባሉ? 🤔
