የርገን ክሎፕ ከሲቲ ጋር የነበረውን በሜዳ ላይ የተደረገውን ታላቅ ትግል አደንቃለው አለ

0
IMG_20261001_152653_648

የቀድሞው የሊቨርፑል አሰልጣኝ የርገን ክሎፕ (Jürgen Klopp) ማንቸስተር ሲቲ በፕሪሚየር ሊጉ የፋይናንስ ደንብ ጥሰት ጥፋተኛ መባሉን ተከትሎ፣ በጀርመን ብሔራዊ ቡድን ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የሰጠው አስተያየት እጅግ ሚዛናዊ እና ስፖርታዊ ጨዋነት የተሞላበት ነው።

ክሎፕ ለስምንት ዓመታት ያህል ከአንፊልድ ሆኖ ከፔፕ ጓርዲዮላ ጋር ብርቱ ፉክክር ማድረጉ ይታወሳል።

ክሎፕ ከማንቸስተር ሲቲ ጋር በነበራቸው ፉክክር ወቅት ለተጫወቱት የእግር ኳስ ጥራት እና በሜዳ ላይ ላሳዩት ደረጃ እጅግ ከፍተኛ አክብሮት እንዳለው ገልጿል። “ያሳዩት የእግር ኳስ አይነት እና ለእኛ የነበሩን ተቃራኒነት በጣም ትልቅ ነበር፤ የጨዋታው ደረጃ እጅግ በጣም ከፍተኛ ነበር” ብሏል።

ማንቸስተር ሲቲ ላይ ስለሚጣለው ማንኛውም አይነት ቅጣት እሱ ምንም የሚያውቀው ነገር እንደሌለ እና ሂደቱ ምን እንደሚሆን ዝም ብሎ እየተጠባበቀ መሆኑን ተናግሯል። ህጋዊ ሂደቱ ረጅም ጊዜ እንደፈጀና የይግባኝ ሂደቱም አመታትን ሊወስድ እንደሚችል ይገምታል።

ከዚህ ቀደም ማንቸስተር ሲቲ ዋንጫ ከተቀማ ሊቨርፑል የአሸናፊነት አውቶቡስ ሰልፍ (Victory Parade) ሊያደርግ ይችላል ብሎ ለቀለደው ቀልድ አሁን ላይ ምንም ፍላጎት እንደሌለው ገልጿል። “አሁን ላይ የፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮንነትን ጥቂት ተጨማሪ ጊዜያት ማሸነፍ አያስፈልገኝም። እኛ በሜዳ ላይ ባሳካነው ነገር ሙሉ በሙሉ ደስተኛ ነኝ” በማለት በሜዳ ላይ የተደረገውን ታላቅ ትግል ብቻ እንደሚያከብር አስታውቋል።

Facebooktwitterlinkedinyoutubetumblrinstagramflickrfoursquaremail
Facebooktwitterredditpinterestlinkedintumblrmail