ኢትዮጵያ ዛሬ ከሜዳዋ ውጪ ዛምቢያን ትገጥማለች

0

በሞሮኮ አስተናጋጅነት ለሚካሄደው የ2026ቱ ዓለም ዋንጫ የመጨረሻ ዙር ማጣሪያ የመጀመርያ ጨዋታ ዛምቢያን የሚገጥመው የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድናችን በንዶላ ሌቪ ምዋናዋሳ ስታዲየም የመጨረሻ ልምምዱን ትናት አድርጎ አጠናቆ ለዛሬው ጨዋታ ተዘጋጅቷል ። ሙሉ የተጫዋቾች ስብስብም በጥሩ ጤንነትና ሞራል ላይ ይገኛልም ተብሏል ።

በ2026 ከ17 ዓመት በታች ሴቶች የዓለም ዋንጫ የመጨረሻ ዙር ማጣርያ የመጀመርያውን ጨዋታ ኢትዮጵያ ዛሬ ከሜዳዋ ውጪ ዛምቢያን ትገጥማለች።

ጨዋታው ከቀኑ 10፡00 ላይ በንዶላ ሌቪ ምዋናዋሳ ስታዲየም ሲካሄድ በጨዋታው የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን አረንጓዴ ማልያ፣ ቢጫ ቁምጣ፣ ቀይ ካሶተኒ ለብሰው ወደ ሜዳ የሚገቡ ይሆናል።

ድል ለኢትዮጵያ 🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Facebooktwitterlinkedinyoutubetumblrinstagramflickrfoursquaremail
Facebooktwitterredditpinterestlinkedintumblrmail