ሀቨርትዝ በጉዳት ስላለ አርቴታ ዮኬሬሽን ለብሄራዊ ቡድኑ ባሳየው ድንቅ ብቃት ሳይሆን ባጣቆየኝ አድርጎ ነው አርቴታ የሚያሰልፈው

አርቴታ ተጫዋቾችን ከተለመደው ውጪ ባልተጠበቀ ቦታ ማሰለፍ የሚወድ አሰልጣኝ ነው። ሀቨርትዝ በጉዳት ከሌለ እና አርቴታ ዮኬሬሽ በሲስተሙ ውስጥ እንዲገባ ካልፈለገ፣ አማካዩን ሚኬል መሪኖን የፊት መስመር ላይ እንደ “Target Man” ወይም “False 9” አድርጎ የመጠቀም ሰፊ ዕድል አለው። መሪኖ በአየር ላይ ኳሶችን የማሸነፍ እና ኳስን የማቆየት (Hold-up play) ብቃቱ ከፍተኛ በመሆኑ ለአርቴታ አማራጭ ታክቲክ ይሆናል።

“በአጣ ቆየኝ” እንደሚባለው፣ አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ ሚኬል አርቴታ ሌላ ምንም አማራጭ የለውም፤ ቪክቶር ዮኬሬሽን (Viktor Gyökeres) የግድ ለማሰለፍ ይገደዳል ።
አሁን ባለው የወቅቱ ነባራዊ ሁኔታ ዮኬሬሽ መጫወት ያለበት “የግድ” የሆነባቸው ዋንኛ ምክንያቶች።
ካይ ሀቨርትዝ በብሔራዊ ቡድን ጨዋታ ላይ ባጋጠመው የጡንቻ (Hamstring) ጉዳት ምክንያት ለአርሰናል የፊት መስመር ላይ ትልቅ ክፍተት ፈጥሯል ።

አርሰናል ባለፈው የዝውውር መስኮት የፊት መስመር እና የክንፍ አማራጮቹን (ለምሳሌ ጋብሬል ማርቲኔሊን ጨምሮ) አሳልፎ ሰጥቷል ። አዲሱ የክንፍ አጥቂ ክሪስቶስ ጾሊስም ጭምር በጉዳት ላይ ይገኛል። ስለዚህ አርሰናል ቤት አሁን ላይ የሚገኝ ብቸኛው እና የተፈጥሮ ዘጠኝ ቁጥር (Recognised Centre-forward) ቪክቶር ዮኬሬሽ ብቻ ነው።

የዮኬሬሽ ወቅታዊ ግልፅ መልዕክት፦ ዮኬሬሽ በስዊድን ብሔራዊ ቡድን ቤት በተከታታይ ጎሎችን በማስቆጠር በታሪክ አስደናቂ ሪከርድ ላይ ይገኛል ። በቅርቡ በሰጠው አስተያየትም “በአርሰናል ቤት መቆየት እና መታገል እፈልጋለሁ፤ በተቻለ መጠን ብዙ መጫወት ነው የምፈልገው” በማለት ለአርቴታ ዝግጁነቱን አሳይቷል ።
ስለዚህ አርቴታ ታክቲኩን ወደ ጎን አቁሞ፣ ከፊት ለሚጠብቀው የሊድስ ዩናይትድ ጨዋታ ዮኬሬሽን በቋሚነት ማሰለፍ ግዴታው ነው ። ይህ አጋጣሚ ለዮኬሬሽ በአርሰናል ቤት ያለውን ዕድል ሙሉ በሙሉ ለመቀየር እና እራሱን በቋሚነት ለማስከበር የመጣለት ወሳኝ የ”በአጣ ቆየኝ” ወርቃማ ዕድል ነው።
