የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን የመጀመርያውን ጨዋታ ዛሬ ኪጋሊ ላይ ያደርጋል

በ2028 ኦሊምፒክ ሴቶች እግር ኳስ ማጣርያ ከሩዋንዳ ጋር ጨዋታውን የሚያደርገው የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን የመጀመርያውን ጨዋታ ዛሬ ረቡዕ መስከረም 27 ኪጋሊ ላይ ያካሄዳል።
ቡድኑ የመጨረሻ ልምምዱን ትናትና ምሽት 1፡00 ላይ በኪጋሊ ፔሌ ስታዲየም ያከናወነ ሲሆን ሁሉም ተጫዋቾች በተሟላ ጤንነት እና የቡድን መንፈስ ልምምዳቸውን አከናውነዋል።
ቡድኑ ዛሬ ምሽት 1፡00 ላይ በሚደረገው ጨዋታ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ቀይ ማልያ ቀይ ቁምጣ እና ቀይ ካሶተኒ፤ የሩዋንዳ ብሔራዊ ቡድን ደግሞ ቢጫ ማሊያ ሰማያዊ ቁምጣ እና ቢጫ ካሶተኒ ለብሰው ወደ ሜዳ ይገባሉ።
የመልሱ ጨዋታ ድሬዳዋ ላይ ጥቅምት 3 ይከናወናል።
