የ2026 ቺካጎ ማራቶን ቅድመ-ዳሰሳ፦ የኢትዮጵያ አትሌቶች ክብርን ለማስጠበቅ ወደ ንፋሷ ከተማ ያቀናሉ!

በዓለም ታዋቂ ከሆኑት ስድስቱ ታላላቅ ማራቶኖች (World Marathon Majors) አንዱ የሆነው የቺካጎ ማራቶን፣ በዚሁ ሳምንት እሁድ ጥቅምት 11 ቀን 2026 ዓ.ም በይፋ ይካሄዳል። የዘንድሮው ውድድር የዓለም ሪኮርድን ለመስበር በሚያልሙና በከፍተኛ ብቃት ላይ ባሉ የምስራቅ አፍሪካ የረጅም ርቀት ፈርጦች የተሞላ በመሆኑ በጉጉት እየተጠበቀ ይገኛል።
ማርካ ኢትዮጵያ (Marca Ethiopia) ወደ አሜሪካ ቺካጎ በተደረገልን ግብዣ በቦታው ባንገኝም፤ ከአዘጋጆቹ ባገኘነው ይፋዊ የሚዲያ ዕውቅና መሠረት፣ ከኢትዮጵያ ሆነን በቦታው ከተገኘ ጋዜጠኛ እኩል (እንዲያውም በሚበልጥ ጥራት) Marca Ethiopia ላይ ሰፊና ማራኪ ዘገባዎችን እንሰራለን፤

በተለይም በተሰን ልዩ የሚዲያ አማራጮች (Press Room & Satellite) በአግባቡ መጠቀም እንችላለን።
ዋናው ነገር ከዓለም ተዋቂ ጋዜጠኞችና አዘጋጆቹ ለተመረጡ ጋዜጠኞች ብቻ የተሰጡትን መረጃዎች Marca Ethiopia በእጃችን በማስገባታች ለእኛ ብቻ ሳይሆን ለሀገራችንም ኩራት ነው።
የቀጥታ ውጤትና መረጃ (Live Results & Press Room) እንዲሁም በተቻለን አቅም በተላከልን የሳተላይት ስርጭት (Satellite Feed) የሚዲያ ተቋማችን በዩቲዩብ የቀጥታ ስርጭቱን ትንተና በትእላከልን የሳተላይት መጋጠሚያዎች (SES 1 Transponder 8 Slot F) [በመጠቀም ውድድሩን በከፍተኛ ጥራት መከታተልና ለተመልካቾችህ ለማድረስ እንሞክራለን ።

በነገራችን ላይ በዘንድሮው ውድድር ላይ የሀገራችንን ሰንደቅ ዓላማ ከፍ ለማድረግ የሚወዳደሩት የኢትዮጵያ አትሌቶች እና ዋና ተቀናቃኞቻቸውን እንደሚከተለው ቃኝተናል።
🏃♂️ በወንዶች Elite ዘርፍ፦ የሚልኬሳ መንገሻ እና ታደሰ ታከለ ፍልሚያ

በወንዶች በኩል ውድድሩን በአካል ለመታደም ባንችልም፣ የሀገራችን አትሌቶች ከኡጋንዳው የወቅቱ ሻምፒዮን ያቆብ ኪፕሊሞ (Jacob Kiplimo – ምርጥ ሰዓት 2:00:28) እና ከኬንያው አሞስ ኪፕሩቶ ጋር ከባድ ፉክክር ያደርጋሉ።
አትሌት ሚልኬሳ መንገሻ (Milkesa Mengesha): የ2024 የበርሊን ማራቶን አሸናፊ። በ2:03:17 የግል ምርጥ ሰዓቱ በዘንድሮው የቺካጎ ማራቶን ላይ ቀዳሚ ግምት ከተሰጣቸው ሶስት ፈጣን አትሌቶች መካከል አንዱ ሆኖ ተመዝግቧል።

አትሌት ታደሰ ታከለ ቢኪላ (Tadese Takele Bikila): የቶኪዮ ማራቶን የ2025 እና 2026 የወርቅ ሜዳሊያ አሸናፊ። በ 2:03:23 የግል ምርጥ ሰዓቱ የቺካጎን ፈጣን መንገድ በመጠቀም አዲስ ታሪክ ለመጻፍ ተዘጋጅቷል።
🏃♀️ በሴቶች Elite ዘርፍ፦ ሐዊ ፈይሳ አክሊሏን ለማስጠበቅ ትፋለማለች!

በሴቶች በኩል የኢትዮጵያ አትሌቶች ፍጹም የበላይነት ይዘው የሚገቡ ሲሆን፣ ትልቁ ትኩረት በፈጣን ሰዓት ላይ ነው።
አትሌት ሐዊ ፈይሳ (Hawi Feysa): የባለፈው ዓመት (2025) የቺካጎ ማራቶን የወቅቱ ሻምፒዮን ናት። በ 2:14:57 የግል ምርጥ ሰዓቷ ዋንጫዋን ለማስጠበቅ የምትገባ ሲሆን፣ ከኬንያዋ የቀድሞ የዓለም ሪኮርድ ባለቤት ብሪጅድ ኮስጌይ (Brigid Kosgei) ጋር ብርቱ ፉክክር ታደርጋለች።

አትሌት መገርቱ ዓለሙ (Megertu Alemu): ባለፈው ዓመት ሁለተኛ ደረጃን ይዛ ያጠናቀቀችው መገርቱ፣ ዘንድሮም ከሐዊ ጋር በመሆን ለሀገራችን ድርብ ድል ለማስመዝገብ ትሮጣለች።

አትሌት በዳቱ ሂርፓ (Bedatu Hirpa) እና እጅጋየሁ ታዬ (Ejgayehu Taye): በከፍተኛ ብቃት ላይ የሚገኙት እነዚህ አትሌቶች የኢትዮጵያን የቡድን ጥንካሬ ይበልጥ ያጠናክሩታል።
ማርካ ኢትዮጵያ የውድድሩን የቀጥታ ውጤቶችና መግለጫዎች ከአዘጋጆቹ የሚዲያ ማዕከል እሁድ ጠዋት ጀምሮ በየደቂቃው በቀጥታ የምናደርሳችሁ ይሆናል! አብራችሁን ሁኑ።
ዘጋቢ፦ ወሰንሰገድ መርሻ (ማርካ ኢትዮጵያ)
