ሮናልዶ ለፓሪስ ሳን ዠርማኑ (PSG) ካቬቻ ኰቨረአትስኬሊያ የማጽናኛ መልዕክትና የቡድኑ ቁልፍ ተጨዋቾች ጉዳት

0
IMG_20261022_091153_341

የፓሪስ ሳን ዠርማኑ (PSG) ክንፍ መስመር ተጫዋች  ካቬቻ ኰቨረአትስኬሊያ (Khvicha Kvaratskhelia) ማክሰኞ ምሽት ባርሴሎናን 4-2 ባሸነፉበት ጨዋታ ላይ የቀኝ እግሩ የጅማት መቀደድ (ACL) ጉዳት ካጋጠመው በኋላ፣ የህፃንነት አርአያው (Idol) የሆነው ሮናልዶ ያቀረበለት ማበረታቻ ለተጫዋቹ ትልቅ የሞራል ስንቅ ሆኖታል።

ካቬቻ ኰቨረአትስኬሊያ  ሁልጊዜም ክርስቲያኖ ሮናልዶን እንደ ትልቅ አርአያ አድርጎ እንደሚመለከተው በግልጽ ይናገራል። በዩሮ 2024 ጆርጂያ ፖርቱጋልን 2-0 ስታሸንፍ የሮናልዶን ማሊያ ተለዋውጦ “ይህ ለጆርጂያ ደጋፊዎች ምርጡ ቀን ነው” ማለቱ ይታወሳል። አሁን ባጋጠመው ከባድ የሙያ ፈተና ወቅት ከሚወደው ተጫዋች እንዲህ አይነት ጥልቅ መልዕክት ማግኘቱ በትልቅ ስሜት ውስጥ ጥሎታል።

ሮናልዶ “በእግር ኳስ ውስጥ በጣም ከባዱ ውጊያ ማንም የማያየው (ከሜዳ ውጪ የሚደረገው የትግል) ክፍል ነው” ማለቱ ያለ ምክንያት አይደለም። እሱ ራሱ በረጅም የእግር ኳስ ዘመኑ እንደዚህ ያሉ ከባድ የጉልበት ጉዳቶችን በፅናት አልፎ ለስኬት የበቃ በመሆኑ፣ የኳራን ስሜት በሚገባ ተረድቶታል።

የካቬቻ ኰቨረአትስኬሊያ  ጉዳት ለራሱ ብቻ ሳይሆን ለክለቡ ፒኤስጂም (PSG) ከባድ መርዶ ነው። ቡድኑ የሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫውን ለመከላከል በሚያደርገው ጉዞ ላይ እሱን ለቀሪው የውድድር ዘመን ሊያጣው እንደሚችል ተነግሯል። ከእሱ በተጨማሪ የባሎን ዶር አሸናፊው ኡስማን ዴምቤሌ እና ካፒታኑ ማርኪኞስም በዚሁ ጨዋታ ተጎድተው ለሳምንታት ከሜዳ መራቃቸው የሉዊስ ኤንሪኬን ቡድን ትልቅ ፈተና ውስጥ ጥሎታል።

ፓሪስ ሳን ዠርማን (PSG) ባወጣው ይፋዊ የህክምና መግለጫ መሠረት፣ በባርሴሎናው ጨዋታ ላይ ጉዳት ያስተናገዱት ኡስማን ዴምቤሌ እና ካፒታኑ ማርኪኞስ ለበርካታ ሳምንታት (Several Weeks) ከሜዳ ይርቃሉ።

ኡስማን ዴምቤሌ (Ousmane Dembélé)፦ በግራ እግሩ የጀርባ ጡንቻ (Left Hamstring) ላይ ጉዳት የደረሰበት ሲሆን፣ ክለቡ ለሚቀጥሉት ሳምንታት የህክምና ክትትል እንደሚያደርግለት ገልጿል። የመጀመሪያ ደረጃ ግምቶች ከ2 እስከ 3 ጨዋታዎች ሊያመልጡት እንደሚችሉ ቢጠቁሙም፣ ጉዳቱ ሳምንታትን ስለሚወስድ ከዚህ ሊረዝም ይችላል።

ማርኪኞስ (Marquinhos)፦ የክለቡ ካፒታን በቀኝ እግሩ ጭን ጡንቻ (Right Thigh) ላይ በደረሰበት ጉዳት ምክንያት በተመሳሳይ መልኩ ለሚቀጥሉት ሳምንታት በህክምና ክፍል ውስጥ ይቆያል።

በአንፃሩ፣ የቀኝ እግሩ የጅማት መቀደድ (ACL) የደረሰበት ካቬቻ ኰቨረአትስኬሊያ ግን ቀዶ ጥገና የሚደረግለት በመሆኑ፣ የማገገሚያ ጊዜው ከ6 እስከ 9 ወራት ሊወስድ እንደሚችል እና ለቀሪው የውድድር ዘመን ሙሉ በሙሉ ከሜዳ ሊርቅ እንደሚችል ታውቋል።

Facebooktwitterlinkedinyoutubetumblrinstagramflickrfoursquaremail
Facebooktwitterredditpinterestlinkedintumblrmail