ማይክል ካሪክ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ለክለቡ ያለውን ጥልቅ ፍቅር ገለጸ

0
IMG_20261025_072749_339

የማንቸስተር ዩናይትዱ አሰልጣኝ ማይክል ካሪክ ከቦርንማውዝ ጋር ለሚደረገው የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ለክለቡ ያለውን ጥልቅ ፍቅር እና ቁርጠኝነት የሚያሳይ እጅግ ስሜታዊ እና ግልጽ መልዕክት አስተላልፏል።

ቡድኑ በሻምፒዮንስ ሊግ በኮሞ 4 ለ 1 በሆነ አስከፊ ውጤት መሸነፉን እና ካፒቴኑ ብሩኖ ፈርናንዴዝ በአሰልጣኞች ታክቲክ ላይ ትችት መሰንዘሩን ተከትሎ፣ ካሪክ ጋዜጠኞች ጥያቄ ከመጠየቃቸው በፊት ለ6 ደቂቃ ያህል የፈጀ አስደናቂ ንግግር አድርጓል።

“እዚህ የመሆን ልዩ መብት አለኝ ብዬ አላስብም። በዚህ ክለብ ውስጥ ‘የማሸነፍ መብት አለኝ’ የሚል ስሜት ሊኖር አይገባም። ከዚህ በፊት አሸንፈናል፣ አስደናቂ ታሪክም አለን፤ ይህ ግን ዝም ብለን እንድናሸንፍ መብት አይሰጠንም።” ብሏል፤

“ማሸነፍ ከባድ ስራ እና ከፍተኛ መስዋዕትነትን ይጠይቃል። ራስን ሙሉ በሙሉ ለክለቡ አሳልፎ መስጠት ያስፈልጋል። ይህንን ክለብ እና እዚህ ለመድረስ ምን እንደሚያስፈልግ እናከብራለን።” ሲልም ገልጿል።

“እውነቱን ለመናገር በቅርብ ሳምንታት ውስጥ በትንሹ መንገዳችንን ስተናል። ነገር ግን ይህንን በፍጥነት እንደምናስተካክለው 100% እርግጠኛ ነኝ።”

ብሩኖ ፈርናንዴዝ በይፋ የሰነዘረውን ትችት በተመለከተ ካፒቴንነቱን ስለመቀማት የተጠየቀውን ጥያቄ ሲመልስ፦ “ለእኔ ዋናው ነገር ቡድኑ እና የክለቡ አንድነት ነው። ምንም ይሁን ምን ሁልጊዜ ለክለቡ የሚበጀውን ውሳኔ አስተላልፋለሁ። እኔ ዝናብ ውስጥ ቆሜ ሌሎቹን የማስጠለል ሃላፊነት አለብኝ።” ብሏል።

ካሪክ የክለቡ የበላይ አካላት ቢጨነቁም ለቡድኑ ማልቀስ ሳይሆን ጠንክሮ መስራት እንደሚገባ እና ለደጋፊዎች ክብር ሲባል ቡድኑ ወደ ቀድሞ ማንነቱ መመለስ እንዳለበት በፅናት ተናግሯል።

Facebooktwitterlinkedinyoutubetumblrinstagramflickrfoursquaremail
Facebooktwitterredditpinterestlinkedintumblrmail