የሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ በታላቁ ጉጉት የሚጠብቀው “የጣና ደርቢ” ጨዋታ

ዛሬ ቅዳሜ ጥቅምት 21 ቀን 2019 ዓ.ም. (October 31, 2026) የሚደረጉት የሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ (CBE Ethiopian Premier League 2026/27) የአምስተኛ ሳምንት ጨዋታዎች
ኢትዮጵያ ቡና ከ አዳማ ከተማ
ሰዓት፦ ከቀኑ 09:00 ሰዓት
ስታዲየም፦ አዲስ አበባ ስታዲየም
ወቅታዊ ሁኔታ፦
ኢትዮጵያ ቡና፦ ባለፉት ሁለት ጨዋታዎች ሽንፈት ያስተናገደ ሲሆን በ3 ነጥብ በደረጃ ሰንጠረዡ 13ኛ ላይ ይገኛል።
አዳማ ከተማ፦ በአንጻሩ ባለፉት ሦስት ጨዋታዎች ድል ባያገኝም በ5 ነጥብ 8ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። ሁለቱም ክለቦች ወደ አሸናፊነት ለመመለስ የሚያደርጉት ተጠባቂ ጨዋታ ነው።
ፋሲል ከነማ ከ ባህር ዳር ከተማ (የጣና ደርቢ)
ሰዓት፦ ከቀኑ 09:00 ሰዓት
ስታዲየም፦ ባህር ዳር ኢንተርናሽናል ስታዲየም
ይህ ጨዋታ በታላቁ “የጣና ደርቢ” (የአማራ ደርቢ) ስያሜ የሚታወቅ እጅግ ተጠባቂ የሳምንቱ መርሃ ግብር ነው። ፋሲል ከነማዎች ከመጀመሪያ ሳምንታት መደናቀፍ ወጥተው ውጤታቸውን ለማስተካከል የሚጫወቱበት ሲሆን ባህር ዳር ከተማ በአንጻሩ በሊጉ ጥሩ አጀማመር ካላቸው ክለቦች አንዱ ነው።

ከ5 ዓመት በኋላ አህጉር አቀፍ ውድድሮችን የማዘጋጀት ጊዜያዊ ፈቃድ አግኝቶ ለ2027 አፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ ኢትዮጵያ እና ከሴኔጋል ያደርጉትን ጨዋታ ያስተናገደው የባህርዳር ዓለም አቅፍ ስታዲየም አሁን ደግሞ ሌላኛውን ጨዋታ ለመቀበል ተዘጋጅቷል።
ካፍ ከጠየቀው የደርጃ ሦስት መስፈርት ከፍ ብሎ ሌሎች ጉዳዮችን ያሟላው እና ሙሉ ፈቃድ ለማግኝት ጥቂት ስራዎችን ብቻ ማጠናቀቅ የቀረው ግዙፉ ስታዲየም በተመሳሳይ ከዓመታት በኋላ የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ይደረጉበታል።
5ኛ ሳምንቱ ላይ በደረሰው ሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ ቅዳሜ 9 ስዓት ላይ በአማራ ክልል ደርቢ ባህርዳር ከተማ ከ ፋሲል ከነማ የሚገናኙብተ ጨዋታ ይጠበቃል።
በዋልያዎቹ የአፍሪካ ማጣሪያ ስታዲየሙ በደጋፊዎች መሞላቱ የሚታወስ ሲሆን ዛሬ በደርቢው ጨዋታም በተመሳሳይ የሁለቱ ቡድን ደጋፊዎች እንዲሁም ገለልተኛ ደጋፊዎች ከ5 ዓመት በኋላ ወደ ክልሉ የተመለሰውን ጨዋታ ለመታደም በብዛት እንደሚገቡም ይጠበቃል።
በተለይ 2 ሺዎቹ ማብቂያ ላይ ወደ ኢትዮጵያ ትልቁ የሀገሪቱ ሊግ ከተመለሱ በኋላ በየዓመቱ ለዋንጫ የሚፎካካሩ ከመሆናቸው ባሻገር የእርስ በእርስ ግንኙነታቸው ደግሞ አንድ ደርቢ ሊያሟላው የሚገባውን ጡዝት በማሳይት ከሜዳ ላይ ትንቅንቅ እስከ ቀይ ካርድ የሚደርስ ትእይንት ሲያሳዩ ቆይተዋል።

ሁለቱ ቡድኖች እያንዳንዳቸው አንድ ተስተካካይ ጨዋታ የሚቀራቸው ሲሆን ፋሲል ከነማ ካደረጋቸው ሦስት ጨዋታዎች አንዱንም ማሸነፍ አልቻለም። በሁለቱ አቻ ተለያይቶ በአንድ ጨዋታ ደግሞ ተሸንፎ በ2 ነጥብ 15ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።
የ2013 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮኑ ፋሲል ከነማ የመጀመሪያ ድሉን ለማግኝት ወደ ሜዳ በሚገባበት ጨዋታ ሌላ ከባድ ፈተና ይጠብቀዋል።
በአንጻሩ ባህርዳር ዳር ከተማ ካደረጋቸው ሦስት ጨዋታዎች ሁለቱን ሲያሸነፍ በአንዱ ብቻ ተሸንፎ በ6 ነጥብ በደረጃ ሰንጠረጁ 5ኛ ላይ ተቀምጧል።
በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ኢትዮጵያ ከሴኔጋል በነበራቸው ጨዋታ ደጋፊዎች ወደ ስታዲየም በሚገቡበት ሰዓት የነበርው መጨናነቅ እና የመግቢያ ትኬት ለማግኝት የነበርው ድካበደጋፊዎች በኩል በቅሬታ የተነሳ እና መስተካክል ያለበት ጉዳይ ነው።
በዋናነት ደግሞ አዘጋጆቹ ባለፈው ጨዋታ የተነሳውን ቅሬታ መነሻ በማድርግ ተመልካቾች ትኬት የሚያገኙበትን ሁኔታ
ቀድሞ በግልጽ ማሳውቅ እንደ አንድ መፍትሄ ሊወሰድ የሚችል ነው። በሌላ በኩል ከዘመኑ ቴክኖሎጂ ጋር አብሮ በመጓዝ የተለያዩ የኦንላይን የትኬት መሸጫ መንገዶችን መከተል አስፈላጊ ነው።
