
በ2026 የፕሪፎንቴይን ክላሲክ -ዩጂን ዳይመንድ ሊግ እና በአሜሪካው የፒችትሪ የጎዳና ሩጫ ላይ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አሸናፊ ሆነዋል ።

በአሜሪካዋ ዩጂን በተካሄደው የዳይመንድ ሊግ ውድድር፣ በሴቶች የሁለት ማይል ርቀት ብርቱ ፉክክር የተስተዋለበት ነበር።
ውድድሩን በአሸናፊነት ያጠናቀቀችው አትሌት አለሺኝ ባወቀ ስትሆን፣ የወቅቱ ፈጣን የሆነ ሰዓት 9:20.02 በማስመዝገብ በአንደኝነት አጠናቃለች።
ሌላኛዋ ጠንካራ ኢትዮጵያዊት አትሌት ሒሩት መሸሻ በ9:20.20 በሆነ ሰዓት በቅርብ ልዩነት ሁለተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች።

በዚሁ የሁለት ማይል ውድድር ላይ የተሳተፉት ሌሎች ኢትዮጵያውያን አትሌቶችም ጠንካራ ፉክክር ያደረጉ ሲሆን ፣አትሌት ማርታ አለማየሁ በ9:21.42 4ኛ ፣አትሌት የኔዋ ንብረት በ9:22.93 7ኛ እና አትሌት አሳየች አይቼው በ9:23.04 8ኛ ደረጃን በመያዝ በቅደም ተከተል አጠናቀዋል።
በሴቶች የአንድ ማይል ውድድር ላይ የተሳተፉት አትሌት ሳሮን በርሀ በ4:22.50 11ኛ ደረጃን እንዲሁም አትሌት ወርቅነሽ መሰለ በ4:36.80 13ኛ ደረጃን ይዘው ፈፅመዋል።
በሌላ በኩል በአሜሪካ የነፃነት ቀን ክብረ በዓል አካል ሆኖ በተካሄደው 57ኛው የፒችትሪ የጎዳና ሩጫ ላይ የኢትዮጵያ አትሌቶች የበላይነታቸውን አረጋግጠዋል።
ለረጅም ርቀት ሩጫ አትሌቶች ፈታኝ በሆነው በዚህ ውድድር፣ አትሌት ፅጌ ገብረሰላማ በመጨረሻዎቹ ሜትሮች ላይ አስደናቂ ፍጥነት በመጨመር ውድድሩን በ31:02 በሆነ ሰዓት በአሸናፊነት አጠናቃለች።
ሌላኛዋ አትሌት መልክናት ውዱ በሰከንድ ልዩነት ማለትም በ31:03 ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቃለች።
Ethiopian athletes record impressive victories at the Eugene Diamond League race.
July 4th ,2026
Ethiopian athletes have won the 2026 Prefontaine Classic-Eugene Diamond League and the Peachtree Road Race in the United States.
The women’s two-mile race at the Eugene Diamond League race in the United States was a closely contested event.
The winner of the race was Aleshin Baweke, who clocked a time of 9:20.02, the fastest time of the season.
Another strong Ethiopian athlete, Hirut Meshesha, finished in second place with a time of 9:20.20.
Other Ethiopian athletes competing in the two-mile race also competed strongly, with athlete Martha Alemayehu finishing 4th in 9:21.42, athlete Newa Malana finishing 7th in 9:22.93, and athlete Asayech Aichew finishing 8th in 9:23.04.
In the women’s one-mile race, athlete Sharon Berha finished 11th in 4:22.50, and athlete Worknesh Mesele finished 13th in 4:36.80.
On the other hand, Ethiopian athletes proved their dominance at the 57th Peachtree Road Run held as part of the US Independence Day celebration.
In a race that is challenging for long-distance runners, athlete Tsige Gebreselama accelerated in the final meters to win the race in 31:02.
Another athlete, Meleknat Wudu, finished in second place in 31:03, a second behind.
