ቅዱስ ጊዮርጊስ በውድድር ዓመቱ የመጀመሪያውን ድል አስመዘገበ

በሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አምስተኛ ሳምንት በተከታታይ አቻ ውጤቶችና አንድ ሽንፈት የተጓዘው ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ኢትዮ ኤሌክትሪክን 1 ለ 0 በማሸነፍ የመጀመሪያ ድሉን አሳክቷል።

በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ቅዱስ ጊዮርጊስ በውድድር ዓመቱ የመጀመሪያውን ሦስት ነጥብ ይዞ እንዲወጣ ያስቻለች ግብ 80ኛው ደቂቃ ላይ ተቀይሮ የገባው ቢላል ገመዳ ከመረብ አሳርፏል።

ሀዋሳ ላይ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደ ጨዋታ ሀዋሳ ከተማ ከመመራት ተነስቶ ጋሞ ጨንቻን 2 ለ 1 አሸንፏል።

የትም ጌታ ታደሰ አዲስ አዳጊውን ጋሞ ጨንቻን ቀዳሚ ቢያደርግም፤ ቃል ኪዳን ዘላለም ያስቆጠራቸው ሁለት ግቦች ሀዋሳን አሸናፊ አድርገዋል።
