አርሰናል ከክርስቲያን ኮፋኔ ወኪሎች ጋር እየተነጋገረ ነው ተብሏል። ነገር ግን የባየር ሊቨርኩሰንን አጥቂ ለማስፈረም ከኒውካስል ጋር የሚደረገውን ፉክክር በልጦ መገኘት ሊኖርበት ይችላል።

ኮፋኔ ባለፈው የውድድር ዘመን ከአልባሴቴ ወደ ሊቨርኩሰን ጋር በ5.25 ሚሊዮን ዩሮ (4.5 ሚሊዮን ፓውንድ) ስምምነት ነበር ክለቡን የተቀላቀለው፤በቡንደስሊጋው የመጀመሪያ የውድድር ዘመን አስደናቂ የሆነ የመጀመሪያ ጊዜን አሳልፏል። በመጀመሪያዎቹ 29 ጨዋታዎች ሰባት ጎሎችንና አራት ግብ የሆኑ ኳሶችን አመቻች አቀብሏል።

የ19 ዓመቱ ተጫዋች በቻምፒዮንስ ሊግ ላይም ከፍተኛ ተጽዕኖ አሳድሯል፣ በተለይም በመጋቢት ወር ሊቨርኩሰን በአርሰናል በተሸነፈበት የመጨረሻ 16 ጨዋታ ላይ ድንቅ ብቃት አሳይቶ ነበር።

ከዚያን ጊዜ ጀምሮ የኮፋኔ የወደፊት ዕጣ ፈንታ ከፍተኛ ግምት የሚሰጠው ተጨዋች ሆኖ ሰንብቷል፤ የአጥቂው ውስጣዊ ስሜት በበጋ ወቅት ከፍተኛ ገንዘብ ሊያስገኝ ይችላል ለሚለው ወሬ ብዙም አስተዋጽኦ አላበረከተም፣ ወኪሉ ኤሪክ ዴፖሎ ለዴይሊ ስለ አርሰናል ክለብ ተጨዋቹን እንደሚፈልገው ለተጠየቀው ጥያቄ በሰጠው አስተያየት «አሰልጣኙ [ማይክል አርቴታ] በጣም ይወደዋል» ሲል ለዴይሊ አርሰናል ተናግሯል።
ዴፖሎ ሌሎች ክለቦች በኮፋኔ ላይ ፍላጎት እንዳላቸው በተመለከተ ለተጠየቀው ጥያቄ ሲመልስ «ቼልሲ፣ ኒውካስትል፣ ኤቨርተን፣ ብሬንትፎርድ፣ ባርሴሎናና ባየርን ሙኒክም ይፈልጉታል» ሲል መልሷል።

ዴፖሎ አርቴታና ዊሊያም ሳሊባ በሰሜን ለንደን መገኘታቸው ለተጨዋቹ ምቾት ሰጦታል፤ክለቡ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ለሚገኘው ታዳጊ ወጣት ከስምምነት ላይ ለማድረስ ከፍተኛ ቦታ ተጫዋቹ እንዳሰጠው ተጠቁሟል።

«የትኛው ክለብ ተጨዋቹን ለማስፈረም ውድድሩን እየመራ እንደሆነ ለመናገር በጣም ገና ነው ብዬ አስባለሁ» ሲል አክሏል።

ነገር ግን ተጫዋቹ እንደ ሚኬል አርቴታ አይነት አሰልጣኝና አሰልጣኙ ስፓኒሽ የሚናገር በመሆኑና ዊሊያም ሳሊባ ከካሜሩን የመጣ በመሆኑ አርሰናል በፖል አመለካከት ቅድሚያ ተጨዋቹ እንደሰጠው ግምቱን አስቀምጧል።

«በእኔና በአርሰናል መካከል ግንኙነት አለ። ነገር ግን አሁን ትኩረታቸው ዝውውሩን ማሸነፍ ነው – ከዚያ በኋላ ሁሉም ነገር መስመር ይይዛል።»በማለት ወኪሉ ይገልጻል ።

እንደ ቢልድ የጀርመኑ ህትመት ዘገባ፣ መድፈኞቹ ኮፋኔን በቻምፒየንስ ሊግ የመጨረሻ 16 ድል ካሳዩበት ጊዜ ጀምሮ «ራዳቸው» እሱ ላይ እንደሆነ ይገልጻል፤ ከተጫዋቹ ወኪሎች ጋር አርሴናል «በቅርብ ግንኙነት» ላይ እንደሆነና ተጨዋቹን ሊያስፈርም ይችላል ሲል ገልጿል ።

ሆኖም፣ ኒውካስትል ኮፋኔን ለማዛወር ፉክክር ውስጥ ገብተዋል ። የሆፈንሃይም ክንፍ ተጫዋች ባዙማና ቱሬ ከፈረሙ በኋላ የካሜሩን ኢንተርናሽናል ተጫዋች ከስምምነት ለመድረስ ትኩረት አድርገው እየሰሩ ሊህን እንደሚችል ተነግሯል።

ማግፒስ በሚቀጥለው የውድድር ዘመን የቻምፒየንስ ሊግ እግር ኳስን ማረጋገጥ አለመቻላቸው ኮፋኔን የማግኘት ተስፋቸውን አሉታዊ ተጽዕኖ ሊያሳድር ይችላል፣ አርሰናል የፕሪሚየር ሊግ ተቀናቃኞቻቸውን በተጨዋቹ ድርድር እንደሚያሸንፉ እርግጠኞች ናቸው።

ሌቨርኩሰን ኮፋኔን ከአንድ አመት በኋላ ብቻ ለማጣት ፈቃደኛ ባይሆኑም፣ ሪፖርቱ የቡንደስሊጋውን ቡድን ወጣቱን እንዲሸጥ ለማድረግ 100 ሚሊዮን ዩሮ (86 ሚሊዮን ፓውንድ) የሚያወጣ ዋጋ በቂ ሊሆን እንደሚችል ይገልጻል።
«በሕይወቴ ውስጥ እንደ ኮፋኔ ብዙ ጥሪዎችን አጋጥመውኝ አያውቅም። አሁን በአውሮፓ ውስጥ ከ21 ዓመት በታች አጥቂና በጣም የተሟላ ችልታ ያለው ነው።»

«ፍጥነት፣ ቴክኒክ፣ በጣም ጥሩ መከላከልና በአየር ላይ የመጣ ኳስን በመምታት ጠንካራ ነው። እነዚህን ሁሉ ባህሪያት በአንድ አጥቂ ውስጥ ማግኘት በጣም ከባድ ነው።»

ከሌቨርኩሰን ከመባረራቸው በፊት የቀድሞው ዋና አሰልጣኝ ካስፐር ህጁልማንድ ኮፋኔን «ጥሩ የወደፊት ጊዜ እንዳለው» ነግረውታል።

«ለእኔ፣ ኮፊ በ2024 መጨረሻ ወደ አውሮፓ መጥቶ በ2025 የበጋ ወቅት ወደዚህ መዛወሩና ከዚያን ጊዜ ጀምሮ እንዴት እንዳደገ ስመለከት በጣም አስደናቂ ነው» ብለዋል።

Facebooktwitterlinkedinyoutubetumblrinstagramflickrfoursquaremail
Facebooktwitterredditpinterestlinkedintumblrmail

By admin

Hello, dear. I am Wosenseged Mersha Demissie. Author, Journalist, and Sociological Criticism. He has worked in several media in Ethiopia and foreign media also. I have come to my country, Ethiopia, from abroad, and for the past eight years, I have been giving political analysis and writing in magazines, newspapers, and televisions on all the free press in Ethiopia. I have six books that I wrote and published during my stay abroad and after I came back to my country and are on the market. Above all, I feel spiritual satisfaction for coming from a developed country and working in a country where there is no freedom of the press. I have sacrificed a lot in this profession. Imprisonment, abuse—I was crushed economically. I have been living separately from my family for many years, but I am happy and proud of my career to be a voice for the voiceless people of Ethiopia, whom I love and respect by working in the press without payment. After leaving my country and returning to my country, Growing up in Arat Kilo, YMCA, I was exposed to various sports. I know many sports. I have worked as a referee, player, and tournament organizer. As a result, I have worked as a sports editor on radio, television, and newspapers for many years. I have worked alongside other media outlets for more than 20 years by preparing and publishing my own sports newspaper called San George.I have traveled to many countries, including Europe, the Far East, Asia, Oceania, and Africa, and have been present at many competitions, including athletics.This is because I have this love for sports. I have reopened this media outlet for sports. In addition to this, I have worked for the past 30 years. May God protect Ethiopia and its people and give peace and love to our world. Thank you anyway. Wosenseged Mersha Demissie Author, Journalist, Sociological Criticism

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *