የኢትዮጵያ ዋንጫ ፍፃሜ በአዲስ አበባ ስታዲየም ይካሄዳል

የኢትዮጵያ ዋንጫ ፍፃሜ አስቀድሞ እንዲካሄድ መርሐ ግብር ተይዞለት ከነበረው ከአበበ ቢቂላ ስታዲየም ወደ አዲስ አበባ ስታዲየም የተቀየረ መሆኑን ፌዴሬሽኑ ገልጿል ።
በዚህም መሠረት የኢትዮጵያ ዋንጫ የፍፃሜ ጨዋታ የፊታችን ሐሙስ ሐምሌ 2 ቀን 2018 ዓ/ም በአዲስ አበባ ስታዲየም ከቀኑ 5፡00 ይካሄዳል ሲል የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ገልጿል።
በሲዳማ ቡናና ወልዋሎ ዓ/ዩ መካከል የሚደረገው ይህ የኢትዮጵያ ዋንጫ ፍፃሜ ጨዋታ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በቀጥታ ስርጭት በሳተላይትና በኦንላይን አማራጮች እንደሚተላለፍ በተጨማሪ ገልጿል።
