
የ ሲዳማ ቡናው ተከላካይ ያሬድ ባየህ የፕሪሚየር ሊጉ የአመቱ ምርጥ ተጨዋች በመባል ተመርጧል።
ያሬድ ባየህ የዋንጫ እና 250ሺህ ብር የገንዘብ ሽልማት ተበርክቶለታል።
የሲዳማ ቡናው አሰልጣኝ ያሬድ ገመቹ በበኩላቸው የአመቱ ምርጥ አሰልጣኝ ሽልማት አሸንፈዋል።
ሌሎች አሸናፊዎች እነማን ናቸው ?
- ኮከብ ግብ ጠባቂ :- ፔፔ ሰይዶ ( ባሕር ዳር ከተማ )
- ተስፈኛ ተጫዋች :- ሐብታሙ ጉልላት ( ቅዱስ ጊዮርጊስ )
*ኮከብ ግብ አግቢዎች :- ናትናኤል ዳንኤል ከ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ታምራት ኢያሱ ከ ፋሲል ከነማ
- ምስጉን ዋና ዳኛ :- ሃይማኖት አዳነ
- ምስጉን ረዳት ዳኛ :- ፋሲካ የኋላሸት
በሌላ በኩል ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ – የ2018 የኢትዮጵያ ዋንጫ አሸናፊ ሆኗል።
የ2018 የኢትዮጵያ ዋንጫ ፍፃሜ ውጤት ሲዳማ ቡና ከወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ጋር ባደረጉት ጨዋታ ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ የፕሪምየር ሊጉን ሻምፕዮና ሲዳማ ቡናን 2ለ0 በማሸነፍ የዋንጫ ባለቤት ሆኗል ።ግቦቹን ለወልዋሎ ዓ/ዩ
በ47 ኛው ደቂቃ ኮንኮኒ ሀፊዝና በባከነ ሰዓት ማለትም
በ99ኛው ደቂቃ በየነ ባንጃ ባስቆጠሩት ግብ 2ለ0 አሸንፎ ወጥቷል ።
ውጤቱን ተከትሎ ወልዋሎ ዓ/ዩ የ2018 የኢትዮጵያ ዋንጫ አሸናፊ ለመሆን በቅቷል ።
