
ማንችስተር ዩናይትድ አዲሱን የውድድር ዘመን አዲስ ካደጉ ክለቦች ጋር በመግጠም ለመጀመር እየተዘጋጀ ይገኛል።
ክለቡ የቅድመ ውድድር ዝግጅት ከመጀመሩ በፊት ዋና ዋና የዝውውር እቅዶችን ለማጠናቀቅ በስፋት እየሰራ ነው። በተለይም የአማካኝ መስመርን ለማጠናከር የታለሙ እንቅስቃሴዎች እያካሄደ ነው።
በአውሮፓ እግር ኳስ ማኅበር ይፋዊ መረጃ መሠረት ማንችስተር ዩናይትድ በስታዲየም ተገኝቶ የተመለከተው ከፍተኛ ተመልካች ያለው ክለብ በመሆን ቀዳሚነቱን ይዟል ።
ይህን ደጋፊ ዘንድሮ ለማስደሰት ክለቡ ቆርጦ ተነስቷል ።
ለ2026/27 አዲሱ የውድድር ዘመን ቡድኑን በከፍተኛ ሁኔታ ለመገንባት አዳዲስ ተጫዋቾችን ማስፈረም ችሏል። ክለቡ የመሐል ሜዳውን ለማጠናከር ከፍተኛ ወጪ እያወጣ ነው የሚገኘው ።
የቅርብ ጊዜ የተጫዋቾች ዝውውር መረጃ

ዩናይትድ የ29 ዓመቱን ቤልጄማዊ አማካይ ዩሪ ቲሌማንስን ከአስቶን ቪላ በ35 ሚሊዮን ፓውንድ ማስፈር ችሏል። የቀድሞው የዩናይትድ ተከላካይ ጆኒ ኢቫንስ ዝውውሩ እንዲሳካ ትልቅ ሚና ተጫውቷል ተብሏል።
ብራዚላዊው ወጣት አማካይ ተጨዋች አንድሬ ሳንቶስ በ50 ሚሊዮን ፓውንድ ከቼልሲ ማንችስተር ዩናይትድን በይፋ ተቀላቅሏል። እስከ ሰኔ 2031 የሚያቆይ ረጅም ኮንትራትም ተፈራርሟል።
ክለቡ ከሮማው አማካይ ማኑ ኮኔ ጋር በ45 ሚሊዮን ፓውንድ የስምምነት ደረጃ ላይ መድረሱ እየተነገረ ይገኛል።
ዩናይትድ ክሪሰንሲዮ ሰመርቪልን አርሰናልን በመፎካከር ይህንን ሆላንዳዊ የፊት መስመር ተጫዋች በ30 ሚሊዮን ፓውንድ ለማስፈረም ዝግጅቱን አጠናቋል።
ቅድመ ውድድር ጨዋታዎች መርሃ ግብር (Pre-season 2026)
ክለቡ ለአዲሱ የውድድር ዘመን ዝግጅት የሚያደርጋቸውን ስድስት የወዳጅነት ጨዋታዎች ይፋ አድርጓል።
እነሱም የሚያደርግባቸው ሀገሮች የሚከተሉት ናቸው ሬክስሃም (Wrexham)ፊንላንድ ፣ሮዘንቦርግ (Rosenborg) ኖርዌይ፣አትሌቲኮ ማድሪድ (Atletico de Madrid) ስዊድን (Snapdragon Cup)፣ፓሪስ ሳን ዠርሜን (PSG)አሜሪካ ፣ሊድስ ዩናይትድ (Leeds United)አየርላንድ፣ኤሲ ሚላን (AC Milan)ፖላንድ ናቸው
