ግብፃዊው የእግር ኳስ ኮከብ ሞሐመድ ሳላህ (Mohamed Salah) ለቱርኩ ክለብ ቤሽኪታሽ (Beşiktaş) በይፋ እስከ አሁን የጨረሰው ነገር የለም። በቅርቡ በያዝነው ሐምሌ ወር ተጫዋቹ ከክለቡ ጋር የቃል ስምምነት ላይ መድረሱን የሚገልጹ የብዙ መገናኛ ብዙኃን ዘገባዎች ቢወጡም፣ ቤሽኪታሽና የተጫዋቹ ወኪል የወጣውን መረጃ ሙሉ በሙሉ አስተባብለዋል።

እንደ ፉትቦል መርካቶ (Football Mercato) ያሉ የስፖርት ሚዲያዎች ሳላህ ከሊቨርፑል በነፃ ከተሰናበተ በኋላ በዓመት 10 ሚሊዮን ዩሮ ደመወዝና 2 ሚሊዮን ዩሮ ቦነስ የሚያገኝበት የ1+1 ዓመት ስምምነት ከቤሽኪታሽ ጋር ማድረጉን ዘግበው ነበር። [የቱርኩ ክለብ ቤሽኪታሽ ይፋዊ መግለጫ በማውጣት ዝውውሩ ተጠናቋል ተብሎ የተሰራጨው ወሬ «ፈጠራ»መሆኑን ገልጾ፣ ጉዳዩ ከእውነት የራቀ ነው ብሏል።

የሳላህ ወኪል ራሚ አባስ (Ramy Abbas Issa) በበኩሉ ሳላህ በቀጣይ የት እንደሚጫወት እስካሁን እንደማያውቅ ና ከክለቦች ጋር ድርድር እንደዳላደረጉ ተናግሯል።

ታዋቂው ጋዜጠኛ ፋብሪዚዮ ሮማኖ እንደገለጸው ቤሽኪታሽ ለሳላህ ጥያቄ ማቅረቡ እውነት ቢሆንም፣ ክለቡ ማስተባበያ የሰጠው ስምምነቱ ሙሉ በሙሉ ስላልተጠናቀቀና ጥንቃቄ ማድረግ ስለፈለገ ነው ብሎ ነበር ።

ሞሐመድ ሳላህ ከሊቨርፑል ጋር ያለው ኮንትራት ሊጠናቀቅ በመቃረቡ በርካታ ታላላቅ ክለቦች እሱን ለማስፈርም ከፍተኛ ፍላጎት አሳይተዋል።

ከቤሽኪታሽ በተጨማሪ ሳላህን ለማስፈርም ጥረት እያደረጉ ያሉ ክለቦች የሚከተሉት ናቸው፦

የሳውዲ ክለቦች አል ሂላል (Al-Hilal) እና አል ኢትሀድ (Al-Ittihad) ለሳላህ እጅግ ከፍተኛ የሆነ የገንዘብ ማቅረቢያ ይዘው እየተጠባበቁ ይገኛሉ።

ፓሪስ ሳን ዠርመን (PSG) እና ባርሴሎና የተጫዋቹን ሁኔታ በቅርብ እየተከታተሉ ካሉ ክለቦች መካከል ይጠቀሳሉ።
የአሜሪካው ኤም ኤል ሲ ሳን ዲዬጎ ኤፍሲ (San Diego FC) የተባለው አዲሱ ክለብም ሳላህን የክለቡ ዋና ኮከብ ለማድረግ ፍላጎት እንዳለው ተገልጿል።

የሳውዲ አረቢያ ሊግ ክለቦች (በተለይም አል ሂላልና አል ኢትሀድ) ሳላህን በሊጉ ትልቁ ተከፋይ ለማድረግ ዝግጁ ናቸው።

በዓመት እስከ 150 ሚሊዮን ፓውንድ (ወደ 200 ሚሊዮን ዶላር ገደማ) የሚጠጋ እጅግ ግዙፍ የገንዘብ ስጦታ ቀርቦለታል።
ከዚህ ሌላ ከደመወዙ በተጨማሪ የሳውዲ አረቢያ የቱሪዝም አምባሳደር የመሆን ዕድልና በረጅም ጊዜ ሂደት የክለብ ከፊል ባለቤትነት (Partial Ownership) የመያዝ መብትን የሚያካትቱ ጥቅማጥቅሞች ቀርበውለታል።

ሳላህ ወደ ሳውዲ ለመሄድ አሁንም በጣም ከፍተኛ የደመወዝ ጭማሪዎችን በመጠየቁና በአውሮፓ የመቆየት ፍላጎት ስላለው ድርድሩ እስካሁን ሙሉ በሙሉ አልተቋጨም

ሞሐመድ ሳላህ እና ሊቨርፑል በይፋ የተለያዩ ሲሆን ተጫዋቹ በአሁኑ ወቅት በነፃ ወኪል (Free Agent) ነው ክለቡን የሚለቀው ።

ሳላህ በ2025 አጋማሽ ላይ ውሉን እስከ 2027 አራዝሞ የነበረ ቢሆንም፣ በ2025/26 የውድድር ዘመን ክለቡ 5ኛ ደረጃን ይዞ ማጠናቀቁንንአ ከተተኪው አሰልጣኝ አርነ ስሎት (Arne Slot) ጋር በነበረው አለመግባባት ምክንያት ውሉን በአንድ ዓመት ቀድሞ በስምምነት አቋርጧል።

ሊቨርፑል ከተጫዋቹ ጋር በስምምነት መለያየቱን በማወጅ በክለቡ ላደረገው ታላቅ ታሪክ አድናቆቱን በመግለጽ የስንብት መልዕክት አስተላልፏል ።

ሳላህ ከ2026ቱ የዓለም ዋንጫ ግብፅ በሽንፈት ከወጣች በኋላ ቀጣይ ማረፊያውን ለመወሰን በጥንቃቄ እያሰበበት ይገኛል።

ሳላህ አሁንም ቢሆን በከፍተኛ የአውሮፓ ውድድሮች ላይ የመጫወት ፍላጎት አለው። ለዚህም ነው ወደ ቱርኩ ቤሽኪታሽ ለመዘዋወር የደመወዝ ፍላጎቱን ከ15 ሚሊዮን ዩሮ ወደ 10 ሚሊዮን ዩሮ ዝቅ አድርጎ ለመደራደር ፍቃደኛ የሆነው።

አንዳንድ የግብፅ ጋዜጠኞች እንደዘገቡት ከሆነ ሳላህ በእንግሊዝ የመቆየት ዕድል ካገኘ የቀድሞ ክለቡ ቼልሲ (Chelsea) የመጀመሪያ ምርጫው እንደሆነ ተገልጿል።

የአሜሪካው ሳን ዲዬጎ ኤፍሲ በግብፃዊ ባለሀብት የሚመራ ክለብ ሲሆን እንዲሁም ስፖርቲንግ ካንሳስ ሲቲም ተጨዋቹን ለማስፈረም ከፍተኛ ፍላጎት ስላሳዩት፣ ሳላህ አሜሪካን የመቆየት ፍላጎቱንም ሙሉ በሙሉ አልዘጋውም።

በአሁኑ ሰዓት ወኪሉ ራሚ አባስ «በጣም በቅርቡ ውሳኔያችንን እናሳውቃለን» ብሏል።

የሳላህ ወኪል እና የቤሽክታሽ ክለብ ዘገባዎቹን ቢያስተባብሉም፣ ከስተጀርባ ያሉ እውነታዎች የሚከተሉት ናቸው ፤

ታዋቂው የስፖርት ጋዜጠኛ ፋብሪዚዮ ሮማኖ (Fabrizio Romano) እንዳረጋገጠው ቤሽኪታሽ (Beşiktaş) ለሳላህ ይፋዊ የውል ማቅረቢያ ማቅረቡ እውነት ነው ሲል ተናግሯል።

ሳላህ መጀመሪያ ላይ በዓመት 15 ሚሊዮን ዩሮ የጠየቀ ቢሆንም፣ ወደ ቱርክ ለመዘዋወር ፍላጎት ስላለው ፍላጎቱን ወደ 10 ሚሊዮን ዩሮ መሠረታዊ ደመወዝና 2 ሚሊዮን ዩሮ ቦነስ በጠቅላላው 12 ሚሊዮን ዩሮ ገንዘብ እንዲከፈልእው ይፈልጋል፤ሳላህ ዝቅ አድርጎ እየተደራደረ መሆኑ ተሰምቷል።

የሳላህ የሕግ ተወካይ የውሉን ዝርዝር ሁኔታና የምስል መብት (Image Rights) ጉዳዮችን ለመወያየት ኢስታንቡል መግባታቸው በሰፊው ተዘግቧል። ክለቡ ማስተባበያ የሰጠው ስምምነቱ ሙሉ በሙሉ ባለመጠናቀቁና ሚስጥራዊነቱን ለመጠበቅ ነው ተብሏል።

ሳላህ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ለመቆየት ከወሰነ የቀድሞ ክለቡን ይመርጣል፦

በወጡ የቅርብ ጊዜ የስፖርት ዘገባዎች መሠረት፣ ሳላህ በእንግሊዝ ለመቆየት ከወሰነ ቼልሲ (Chelsea) የመጀመሪያ እና ዋነኛ ምርጫው እንደሆነ ለቅርብ ሰዎቹ ተናግሯል።

ቼልሲ ተጫዋቹን በነፃ ዝውውር (Free Transfer) የማግኘት ዕድል ስላለው ሁኔታውን በቅርብ እየተከታተለ ይገኛል። ሳላህ በቼልሲ ቤት ከዚህ ቀደም የነበረውን ያልተሳካ ቆይታ በታላቅ ብቃት ለመቀየር ይፈልጋል።

የግብፃዊው ባለሀብት ክለብ ሳን ዲዬጎ ኤፍሲ (San Diego FC) በግብፃዊው ቢሊየነር መሐመድ ማንሱር (Mohamed Mansour) የሚመራ በመሆኑ፣ ሳላህን የአሜሪካው ሊግ ትልቁ ኮከብ ለማድረግ ከፍተኛ ፍላጎት አላቸው።ክለቡ ለሳላህ ከስፖርታዊ ውድድር ባለፈ በአሜሪካ ውስጥ የንግድና የማስታወቂያ ብራንድ እንዲሆን ትልቅ የረጅም ጊዜ ፕሮጄክት አቅርበውለታል። ሳላህ የአሜሪካውን ክለብ ለቤተሰቡ ምቾት ሲል በአማራጭነት ይዞታል ።

ለማጠቃለል ያህል በአሁኑ ሰዓት ሳላህ ከግብፅ ብሔራዊ ቡድን ጋር በ2026ቱ የዓለም ዋንጫ ቡድኑ በአርጀንቲና ከተሸነፉ በኋላ ያደረገውን ቆይታ አጠናቆ በዕረፍት ላይ ይገኛል። ወኪሉ ራሚ አባስ «በጣም በቅርቡ የት እንደሚጫወት እናሳውቃለን» ማለቱን ተከትሎ የትኛውን ክለብ እንደሚመርጥ ግን በሚቀጥሉት ቀናት የሚታወቅ ይሆናል የሚል ግምት አለ።

Facebooktwitterlinkedinyoutubetumblrinstagramflickrfoursquaremail
Facebooktwitterredditpinterestlinkedintumblrmail

By admin

Hello, dear. I am Wosenseged Mersha Demissie. Author, Journalist, and Sociological Criticism. He has worked in several media in Ethiopia and foreign media also. I have come to my country, Ethiopia, from abroad, and for the past eight years, I have been giving political analysis and writing in magazines, newspapers, and televisions on all the free press in Ethiopia. I have six books that I wrote and published during my stay abroad and after I came back to my country and are on the market. Above all, I feel spiritual satisfaction for coming from a developed country and working in a country where there is no freedom of the press. I have sacrificed a lot in this profession. Imprisonment, abuse—I was crushed economically. I have been living separately from my family for many years, but I am happy and proud of my career to be a voice for the voiceless people of Ethiopia, whom I love and respect by working in the press without payment. After leaving my country and returning to my country, Growing up in Arat Kilo, YMCA, I was exposed to various sports. I know many sports. I have worked as a referee, player, and tournament organizer. As a result, I have worked as a sports editor on radio, television, and newspapers for many years. I have worked alongside other media outlets for more than 20 years by preparing and publishing my own sports newspaper called San George.I have traveled to many countries, including Europe, the Far East, Asia, Oceania, and Africa, and have been present at many competitions, including athletics.This is because I have this love for sports. I have reopened this media outlet for sports. In addition to this, I have worked for the past 30 years. May God protect Ethiopia and its people and give peace and love to our world. Thank you anyway. Wosenseged Mersha Demissie Author, Journalist, Sociological Criticism

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *