
የ2026ቱ የፊፋ ዓለም ዋንጫ ታላቅ የፍፃሜ ጨዋታ ዛሬ እሁድ ሐምሌ 12 ቀን 2018 ዓ.ም በሊዮኔል ሜሲ የምትመራው አርጀንቲናና በላሚን ያማል በምትመራው በስፔን መካከል በኒው ዮርክ ኒው ጀርሲ (ሜትላይፍ) ስታዲየም ይደረጋል ።
በዛሬው ታሪካዊ የፍፃሜ ጨዋታ አዳዲስና ልዩ ክስተቶች ይታያሉ ተብሎ ይጠበቃል ።
በዓለም ዋንጫ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ፣ አሸናፊው ቡድን ከተለመደው የወርቅ ሜዳሊያና ዋንጫ በተጨማሪ የአሜሪካ ስፖርታዊ ባህል የሆነውን የሻምፒዮና ቀለበት (Championship Rings) ይሸለማል። ፊፋ ለተጫዋቾችና ለክለብ አባላት የሚሆኑ 30 ልዩ ቀለበቶችን ያዘጋጀ ሲሆን፣ ለደጋፊዎች የሚሸጡ ደግሞ 1,996 ቀለበቶች ማዘጋጀቱ ታውቋል።

ሌላው የአሜሪካውን የሱፐር ቦውል (Super Bowl) ውድድርን ኮፒ በማድረግ ፣ በዓለም ዋንጫ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የ11 ደቂቃ የዕረፍት ሰዓት የሙዚቃ ትርኢት ይቀርባል። ትርኢቱን በኮልድፕሌይ (Coldplay) ባንድ መሪ ክሪስ ማርቲን የሚመራ ሲሆን ማዶና፣ ጀስቲን ቢበር፣ ሻኪራና ቢቲኤስ (BTS) የመሳሰሉ ከዋክብት ይሳተፉበታል። በዚህም ምክንያት የተለመደው የ15 ደቂቃ የዕረፍት ሰዓት እስከ 30 ደቂቃ ሊራዘም ይችላል ተብሎ ይጠበቃል።
የ39 ዓመቱ ሊዮኔል ሜሲ አርጀንቲናን በተከታታይ ለሁለተኛ ጊዜ የዓለም ሻምፒዮን በማድረግ ከብራዚሉ ፔሌ (1962) በኋላ ታሪክ ለመድገም የዛሬው ጨዋታ ለእሱ ልዩ ነው።
በሌላ በኩል የስፔኑ የ19 ዓመቱ ወጣት ኮከብ ላሚን ያማል ሀገሩን ለሁለተኛ የዓለም ዋንጫ ክብር ለማብቃት እሱም በነገው ጨዋታ ከጡንቻ መሸማቀቅ አገግሞ ቡድኑን ይመራል።
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በስታዲየሙ ተገኝተው ጨዋታውን የሚከታተሉ ሲሆን፣ ከፊፋ ፕሬዝዳንት ጂያኒ ኢንፋንቲኖ ጋር በመሆን ዋንጫውን ለአሸናፊው ቡድን ያስረክባሉ ተብሎ ይጠበቃል።
የዘንድሮውን የዓለም ዋንጫን ታሪክ የሚቀይሩ ሁለት አዳዲስ ክስተቶች አሉ ፦አንደኛው የሻምፒዮና ቀለበት (Championship Rings) ነው ፤ይህ ቀለበት
ፊፋ የአሜሪካን የስፖርት ባህል (እንደ NBA እና NFL) በመውሰድ ያዘጋጀው ልዩ ቀለበት ከፍተኛ ዋጋ ያላቸው ማዕድናት የተጠገኑበት ነው፦
ቀለበቱ ከ14 ካራት ነጭ ወርቅ የተሰራ ሲሆን፣ በላዩ ላይ የ2026ቱ የዓለም ዋንጫ አርማ በደማቁ ተቀርጾበታል።
በእያንዳንዱ ቀለበት ላይ 26 ትናንሽ አልማዞች (Diamonds) እና በአርማው ዙሪያ ደግሞ የፊፋን ቀለማት የሚወክሉ ሰማያዊ ሳፋየር (Sapphires) እና አረንጓዴ ኤመራልድ (Emeralds) ድንጋዮች አርፈውበታል።
ለተጫዋቾቹ በሚሰጡት 30 ቀለበቶች ላይ የእያንዳንዱ ተጫዋች ስም፣ የጀርባ ቁጥርና የሀገሪቱ ባንዲራ በልዩ ሁኔታ ተቀርጾባቸዋል።
ለሽያጭ ከቀረቡት 1,996 ቀለበቶች መካከል ቁጥር 1 የተሰኘው የመጀመሪያው ቀለበት በጨረታ ተሽጦ ገቢው ለህፃናት መርጃ ድርጅት ይውላል ተብሏል።
ሁለተኛው የዕረፍት ሰዓት የሙዚቃ ትርኢት (Halftime Show) ነው፤የፊፋ ስፖርታዊ እንቅስቃሴን ወደ ታላቅ የኪነጥበብ መድረክ የሚቀይረው ይህ ትርኢት በአይነቱ ልዩ የሆነ ዝግጅትይቀርባል ተብሎ ይጠበቃል ።
ጨዋታው እንደተጠናቀቀ በስታዲየሙ ሜዳ ላይ በ90 ሰከንዶች ውስጥ ብቻ ተገጣጥሞ የሚያልቅ ዘመናዊ መድረክ በቴክኖሎጂ ባለሙያዎች ተዘጋጅቷል ።

የትርኢቱ ዋና መሪ ክሪስ ማርቲን ሲሆን፣ ታዋቂው ባንዲቸው ኮልድፕሌይ “A Sky Full of Stars” የተሰኘውን ዜማቸውን ጨምሮ ልዩ ልዩ ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ።
በጠቅላላው 11 ደቂቃ በሚፈጀው ትርኢት ላይ ማዶና እና ጀስቲን ቢበር የፖፕ ሙዚቃ ንግሥናቸውን የሚያሳዩበት፣ ሻኪራ የላቲን ውዝዋዜ የምታደምቅበት፣ እንዲሁም የኮሪያው BTS የኬ-ፖፕ (K-Pop) ብቃቱን የሚያሳይበት የጥምረት ስራ (Medley) ይቀርባል ተብሏል።
መድረኩን ለመግጠም፣ ትርኢቱን ለማቅረብና መድረኩን መልሶ ለማንሳት በአጠቃላይ 30 ደቂቃ ስለሚፈጅ፣ ሁለተኛው አጋማሽ ጨዋታ ከተለመደው ዘግይቶ ይጀምራል። ይህ አሰራር ተጫዋቾች በቂ እረፍት እንዲያገኙ ቢረዳም የቡድኖቹን ትኩረት እንዳይበታትን አሰልጣኞቹ ስጋታቸውን ገልጸዋል።
በኒው ዮርክ ኒው ጀርሲ (ሜትላይፍ) ስታዲየም በሚደረገው በዚህ ጨዋታ ላይ ከ80,000 በላይ ደጋፊዎች ይታደማሉ።
ለታላቁ የፍፃሜ ጨዋታ የወጡት ይፋዊ የቪአይፒ (VIP) እና የሆስፒታሊቲ ትኬቶች ዋጋ እስከ 15,000 የአሜሪካ ዶላር ($) በመድረሱ የተነሳ በታሪክ ውዱ የዓለም ዋንጫ ጨዋታ ተብሏል።
ከስታዲየሙ ውጭ በሚገኙት የደጋፊዎች መንደር (Fan Zones) ውስጥ ከ200,000 በላይ የሚሆኑ የአርጀንቲናና የስፔን ደጋፊዎች ጨዋታውን በትልልቅ ስክሪኖች ለመከታተል ከወዲሁ ተሰባስበዋል።
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕና በርካታ የዓለም መሪዎች ስለሚገኙ የጸጥታው ጥበቃ እጅግ ከፍተኛ በሆነ ሁኔታ «በብሔራዊ የደህንነት ልዩ ክስተት» (NSSE) ደረጃ ላይ ነው የተዋቀረው፦ ‘
በስታዲየሙ ዙሪያ ያለው የአየር ክልል ሙሉ በሙሉ ለደህንነት ሲባል የተዘጋ ሲሆን፣ ወታደራዊ ድሮኖችና የደህንነት ሄሊኮፕተሮች ሰማዩን ይቆጣጠራሉ።

የፊት መለያ ቴክኖሎጂ (Face Recognition) ተገጥመዋል፦ በስታዲየሙ መግቢያዎች ላይ የተገጠሙት ዘመናዊ ካሜራዎች ማንኛውንም ተጠርጣሪ ግለሰብ በሰከንዶች ውስጥ ለይተው የማወቅ አቅም አላቸው።
ከእረፍት ሰዓቱ የሙዚቃ ትርኢት (Halftime Show) በተጨማሪ፣ ጨዋታው ከመጀመሩ በፊት በሚደረገው የመዝጊያ ስነ-ስርዓት ላይ አስገራሚ የሆሊውድና የሙዚቃ ከዋክብት ዝግጅታቸውን ያቀርባሉ፦
የቶም ክሩዝ ልዩ ክስተት፦ የሆሊውዱ ታዋቂ ተዋናይ ቶም ክሩዝ (Tom Cruise) ለየት ያለ አስደናቂ ትርኢት (Stunt) በውድድሩ ላይ እንደሚያሳይ ይጠበቃል።
በሙዚቃ ድግስ ዝግጅት ላይ ታዋቂው ድምፃዊ ሮቢ ዊሊያምስ (Robbie Williams)፣ ኒኮል ሸርዚንገር እና የዩቲዩብ ኮከቡ IShowSpeed በመድረኩ ላይ ይገኛሉ። የአሜሪካን ብሔራዊ መዝሙር ደግሞ ኦስካር ተሸላሚዋ ጄኒፈር ሁድሰን (Jennifer Hudson) ዝግጅቷን ታቀርባለች።

የዛሬውን ታሪካዊ ጨዋታ በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 4:00 ሰዓት ጀምሮ በቀጥታ መከታተል ይቻላል።
ለዛሬው ታሪካዊ የ2026 የዓለም ዋንጫ ፍፃሜ ጨዋታ በስፖርት ሚዲያዎች በስፋት እየተጠበቁ ያሉ የሁለቱ ቡድኖች ሊሰለፉ የሚችሉበት ግምታዊ አሰላለፍ (Predicted Lineups) እንግለጽላችሁ፦
🇦🇷 የአርጀንቲና ግምታዊ አሰላለፍ (4-4-2 ወይም 4-3-3)
አሰልጣኝ ሊዮኔል ስካሎኒ የተለመደውን ጠንካራ ስብስባቸውን ይዘው የሚገቡ ሲሆን፣ ሮድሪጎ ደ ፖል ወደ መጀመሪያ አሰላለፍ እንደሚመለስ ይጠበቃል።
ግብ ጠባቂ፦ ኤሚሊያኖ ማርቲኔዝ (E. Martínez)
ተከላካዮች፦ ጎንዛሎ ሞንቲኤል (ወይም ሞሊና)፣ ክሪስቲያን ሮሜሮ፣ ሊሳንድሮ ማርቲኔዝ፣ ኒኮላስ ታግሊያፊኮ
አማካዮች፦ ሮድሪጎ ደ ፖል፣ ሊያንድሮ ፓሬዴስ፣ ኤንዞ ፈርናንዴዝ፣ አሌክሲስ ማክ አሊስተር
አጥቂዎች፦ ሊዮኔል ሜሲ (ካፒቴን)፣ ጁሊያን አልቫሬዝ
🇪🇸 የስፔን ግምታዊ አሰላለፍ (4-2-3-1)
አሰልጣኝ ሉዊስ ዴ ላ ፉዌንቴ ምንም አይነት የጉዳት ዜና የሌለባቸውን እስከ ፍፃሜው እጅግ አስደናቂ ብቃት ያሳዩትን ወጣቶችና አንጋፋ ተጫዋቾች ጥምረት ይዘው ይገባሉ።
ግብ ጠባቂ፦ ኡናይ ሲሞን (Unai Simón)
ተከላካዮች፦ ፔድሮ ፖሮ፣ ፓው ኩባርሲ፣ አይሜሪክ ላፖርት፣ ማርክ ኩኩሬላ
የመሃል አማካዮች፦ ሮድሪ (Rodri)፣ ፋቢያን ሩዊዝ
የፊት አማካዮች፦ ላሚን ያማል፣ ዳኒ ኦልሞ፣ አሌክስ ባኤና
አጥቂ፦ ሚኬል ኦያርዛባል
ይህ አሰላለፍ ጨዋታው ከመጀመሩ አንድ ሰዓት በፊት ይፋዊ በሚሆንበት ጊዜ መጠነኛ ለውጦች ሊኖሩት ይችላል።
በእነዚህ ተጫዋቾች ስብስብ መሰረት፣ ዛሬ የትኛው ወገን የመሃል ሜዳውን የበላይነት በመቆጣጠር ዋንጫውን ያነሳል ብለው ይገምታሉ አስተያየቶትን በተሞቾት በኩል ያጋሩን ? የሮድሪ ስፔን ወይስ የደ ፖልና ፈርናንዴዝ አርጀንቲና?
