
ውበቱ አባተ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ስር ታዋቂ ክለቦችን እንዲሁም ብሔራዊ ቡድኑን በማሰልጠን ትልቅ ልምድ ያካበተ አንጋፋ አሰልጣኝ ነው።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን (ዋሊያዎችን) በመምራት ቡድኑ ለ2021 ለካሜሩን የአፍሪካ ዋንጫ እንዲያልፍ አስችለዋል፤በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ እንደ ቡና፣ ፋሲል ከነማ እና ሌሎች በርካታ ክለቦችን አሰልጥነዋል።
በሱዳን፣ ደቡብ ሱዳን (እንደ ጃሙስ ኤፍሲ) እና በላይቤሪያ ሊጎች ውስጥም በመስራት ዓለም አቀፍ ልምድ አግኝተዋል。
የቀድሞው የብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ከአንድ ዓመት ቆይታ በኋላ ወደ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በይፋ ተመልሰዋል። አሰልጣኙ የመቻል እግር ኳስ ክለብን በዋና አሰልጣኝነት ለመምራት ሙሉ ስምምነት ላይ ደርሰው ፊርማቸውን አኑረዋል።
ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ ቡና ፣ አዳማ ከተማ ፣ ሀዋሳ ከተማ ፣ ፋሲል ከነማ ፣ ሰበታ ከተማ እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን እንዲሁም ከሀገር ውጭ የሱዳኑን አልአህሊ ሸንዲ ፣ የላይቤሪያውን ‘Liscr’ እና የደቡብ ሱዳኑን ጃሙስን ማሰልጠን የቻሉት አሠልጣኝ ውበተ አባተ በሁለት ዓመት ውል መቻልን ለማሰልጠን ከስምምነት ደርሰዋል ።
አሰልጣኝ ውበቱ አባተ መቻልን በመረከብ አዳዲስ ተጫዋቾችን በማስፈረም ጠንካራ ቡድን ለመገንባት አስቧል በተለይም፤ አጥቂውን ታፈሰ ሰርካን ጨምሮ በርካታ አንጋፋ ተጫዋቾችን በማሰናበት፣ በምትካቸው ወጣቶችና ፈጣን የክንፍ ተጫዋቾችን ለማስፈረም ማቀዱ ታውቋል ።
