ሲዳማ ቡና የአምበሉን ያሬድ ባየህ ጨምሮ የወሳኝ ተጫዋቹን ውል አራዘመ

በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግን በውድድር ዘመኑ ማሸነፍ የቻሉት ሲዳማ ቡናዎች፤ የወሳኝ ተጫዋቾቻውን ውል ለማራዘም እንቅስቃሴ ጀምረዋል።
ኢቲቪ ከክለቡ ባገኘው መረጃ መሰረትም የቡድኑ አምበል እና የሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ኮከብ ተጫዋቹን ያሬድ ባየህን ውል ለተጨማሪ ሁለት ዓመት ለማራዘም ከስምምነት ደርሷል።
ሻምፒዮኖቹ በተጨማሪም የተከላካዩ ደስታ ደሙን እና የመስመር አጥቂው መስፍን ታፈሰን ውል በተመሳሳይ ለተጨማሪ ሁለት ዓመት ለማራዘም ተስማምተዋል።
ክለቡ በቀጣይም የሌሎች ተጫዋቾችን ውል የማራዘም እና አዳዲስ ተጫዋቾችን የማስፈረም እንቅስቃሴ ላይ እንደሚሳተፍ ይጠበቃል።
