
የኢትዬጵያ ፕሪሚየር ሊግ የተጨዋቾች የዝውውር መስኮት በይፋ ከመከፈቱ አስቀድሞ ክለቦች በተጨዋቾች እና በአሰልጣኞች ዝውውር ተጠምደዋል።
ኢትዬጵያ ቡና እና መቻል የአሰልጣኝ ለውጥ በማድረግ ገብረመድህን ሃይሌ እና ውበቱ አባተን ቀጥረዋል።
ወላይታ ድቻ ደግሞ የአሰልጣኝ መሳይ ተፈሪን ውል ያራዘመ ሲሆን በቀጣዬቹ ቀናት የአሰልጣኝ ለውጥ አድርገው የሚመጡ ክለቦች መኖራቸው ርግጥ ሆናል።
በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጥራት ካላቸው ተጨዋቾች መካከል ከፊት የምናገኛቸው አጥቂው አቡበከር ናስር እና ግብ ጠባቂው አቡበከር ኑራ ደግሞ በቀጣዩ ዓመት በአዲስ ክለብ የምንመለከታቸው ተጨዋቾች መሆናቸው ተስምቱዋል።
ሁለቱ ተጨዋቾች በትላልቅ ክለቦች ውስጥ የምንመለከታቸው ስለመሆኑ እና ማረፊያቸውን እንዳመቻቹ መረጃው ያመለክታል።
ከአራት ዓመት በኋላ ወደ ፕሪሚየር ሊጉ የሚመለሰው እና የፕሪሚየር ሊጉ የምንግዜውም ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ አቡበከር ናስር እና የአምናው የሊጉ ምርጥ ግብ ጠባቂ አቡበከር ኑራ በትላልቅ ክለቦች ዕቅድ ውስጥ መቆየታቸው አይዘነጋም።
ጥራት ያላቸውን ተጨዋቾች እናዘዋውራልን ሲል ትናንት ይፋ ያደረገው ኢትዮጵያ ቡና በ72 ሰዓት ውስጥ ትላልቅ ዝውውሮችን ይፋ እንደሚያደርግ ወርልድ አረጋግጣለች። በክለቡ ሰርፕራይዝ እንደሚኖር ጭምር።
በሌላ በኩል የሊጉ ሻምፒዮን ሲዳማ ቡና የያሬድ ባዬ መስፍን ታፈሰ እና ደስታ ደሙን ቆይታ አራዝማል።በሃዋሳ ከነማው አማካይ አብነት ደምሴ የተያዘው ሪከርድ መሰበሩም ይነገራል።
አብነት በሳምንት 800 ሺህ ብር የሚከፈለው ቁጥር አንድ የፕሪሚየር ሊጉ ከፍተኛ ተከፋ
ጋዜጠኛ ጥሩነህ ካሳ (ወርልድ ስፖርት)
