
ወደ መጠናቀቁ የተቃረበው የቱር ደ ፍራንስ ውድድር ትናትናና ከትናት ውዲያ የተካሄደ ሲሆን ዛሬም ቀጥሎ ይውላል፤በትናንትናው (17ኛ መድረክ) እና ከትናንት በስቲያ በተካሄደው (16ኛ መድረክ) የተካሄዱት የቱር ደ ፍራንስ ውድድሮች አስደናቂ ፋክክር የተካሄደበት ነበር፣ ሬምኮ ኢቨንፖኤልና ጃስፐር ፊሊፕሰን የየዕለቱን የአሸናፊነት ድል ተቀዳጅተዋል።
ከትናንት በስቲያ ማክሰኞ ሐምሌ 14 ቀን በተካሄደው – 16ኛ የውድድር መድረክ ከኤቪያን-ሌ-ባን እስከ ቶኖን-ሌ-ባን ከ26.1 ኪሎ ሜትር ርቀት የሚሸፍን ነበር ፤በዚህ የግል የሰዓት ፍሊሚያ (Individual Time-Trial) ቤልጄማዊው የሰዓት ፍልሚያ የዓለም ሻምፒዮኑ ሬምኮ ኢቨንፖኤል (Remco Evenepoel) በ32 ደቂቃ ከ19 ሰከንድ በማጠናቀቅ ውድድሩን አሸንፏል።
ቢጫ ማሊያውን የለበሰው ታደይ ፖጋቻር (Tadej Pogačar) ከኢቨንፖኤል በ28 ሰከንድ ዘግይቶ በመግባት ሁለተኛ ሆኗል።
በውድድሩ ወቅት ጀርመናዊው ተወዳዳሪ ፍሎሪያን ሊፖዊትዝ (Florian Lipowitz) በደረሰበት ከባድ አደጋ ከውድድር ውጭ ሆኗል።
በትናንትናው የረቡዕ ሐምሌ 15 ቀን – 17ኛ መድረክ ውድድር የተካሄደው
ከሻምቤሪ እስከ ቮይሮን 174.7 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ሜዳማና ኮረብታማ፣ ለፈጣን ሰዓት የሚመች ውድድር ነበር።
ቤልጄማዊው ጃስፐር ፊሊፕሰን (Jasper Philipsen) በቡድን አጋሩ ማቲው ቫን ደር ፖል አስደናቂ እገዛ የዘንድሮውን የመጀመሪያ የደረጃ ድሉን አስመዝግቧል።
ማውሮ ሽሚድ (Mauro Schmid) ከስዊዘርላንድ ሁለተኛ ሆኖ ሲያጠናቅቅ፤ኦላቭ ኮይ (Olav Kooij) ከኔዘርላንድስ ውድድሩን በሦስተኝነት አጠናቋል።
ጠቅላላ የደረጃ መሪነት (General Classification efter እስከ ዛሬ ባለው ውጤት መሰረት ታደይ ፖጋቻር ጠቅላላ መሪነቱን በከፍተኛ ነጥብ እየመራ ነው።
በዚሁ መሰረት 1ኛ .ታደይ ፖጋቻር (ስሎቬኒያ)UAE Team Emirates-XRGመሪ (60:04:17)2ኛ.ሬምኮ ኢቨንፖኤል (ቤልጄም)Red Bull-Bora-Hansgrohe በ4:32 አንሶ ሲከተል 3ኛ.ኢሳቅ ዴል ቶሮ (ሜክሲኮ)UAE Team Emirates-XRG በ6:51 ደቂቃ አንሶ ይከተላቸዋል።

በአረንጓዴ ማሊያ በዴንማርካዊው ማድስ ፔደርሰንና በቤልጄማዊው ጃስፐር ፊሊፕሰን መካከል ያለው ልዩነት ወደ 7 ነጥብ ጠቧል። ኤርትራዊው ኮከብ ቢኒያም ግርማይ ከእነሱ በ84 ነጥብ አንሶ በ361 ነጥብ ሶስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፤ቢንያም የዘንድሮ ውድድር የከበደው ይመስላል፤ውድድሩን የማሸነፉ ሁኔታ ጥያቄ የገባ ነው።
አጠቃላይ ውጤት ስንመለከት ማድስ ፔደርሰን (Mads Pedersen) — በ452 ነጥብ አንደኛ ሲሆን፤
ጃስፐር ፊሊፕሰን (Jasper Philipsen) — በ445 ነጥብ ሁለተኛ ነው፤ፉክክሩ በሁለቱ መካከል ይመስላል፤
ቢኒያም ግርማይ (Biniam Girmay) — በ361 ነጥብ የሦስተኛ ስፍራ ላይ ይገኛል
ዛሬ ሐምሌ 16 ቀን 2018 ዓ.ም. የቱር ደ ፍራንስ 18ኛ መድረክ ውድድር ምሽት ላይ ይካሄዳል ። ይህ ውድድር የአልፕስ ተራራማ ቦታዎች ፍልሚያ የመጀመሪያው ምዕራፍ ነው።
ይህ ዛሬ የሚካሄደው 18ኛ መድረክ ውድድር (Stage 18) ከቮይሮን እስከ ኦርሲየርስ-ሜርሌት 185.2 ኪሎ ሜትር ይሸፍናል።
3,900 ሜትር ከፍታ ያለው እጅግ ፈታኝ የተራራ ላይ ውድድር (Mountain Stage) ያለው ነው። ውድድሩ 5 ከባድ የተራራ መውጫዎችን የያዘ ሲሆን፣ የመጨረሻው 7.1 ኪሎ ሜትር በ6.7% አቀበት ተወዳዳሪዎቹን ወደ 1,825 ሜትር ከፍታ ላይ ወደሚገኘው የበረዶ መንሸራተቻ ጣቢያ (Ski Station) ይወስዳቸዋል።
የዛሬው ውድድር ዋና የአሸናፊ ግምት (The Contenders) ቅድሚያ የተሰጠው ለታደይ ፖጋቻር (Tadej Pogačar) ነው ።ምንም እንኳን በ2020 እዚህ ቦታ ላይ በፕሪሞዝ ሮግሊች ተቀድሞ ሁለተኛ ወጥቶ የነበረ ስለሆነ ዛሬ ያንን ታሪክ ለመቀየርና መሪነቱን ይበልጥ ለማጠናከር እንደሚፎካከር ይጠበቃል።
ፍጥነቱን የሚመሩት ተወዳዳሪዎች ጠቅላላ መሪዎቹ ራሳቸውን ለቀጣይ ቀናት ለማዳን ፍጥነቱን ከቀነሱት፣ እንደ ሪቻርድ ካራፓዝ (Richard Carapaz) እና ኤጋን በርናል (Egan Bernal) ያሉ የተራራ ላይ ስፔሻሊስቶች የዕለቱን ድል ሊነጥቁ ይችላሉ።
ይህ የ18ኛ መድረክ ውድድር ካለቀ በኋላ፣ ቱር ደ ፍራንስ 2026ን ሙሉ በሙሉ የሚወሰኑ ሁለት አስፈሪ የተራራ ላይ ፍልሚያዎች ይጠብቃሉ፤ ነገ አርብ 19ኛ የውድድር መድረክ) ታዋቂው አልፕ ዲ ሁዌዝ (Alpe d’Huez) የተራራ ጫፍን መውጣት የሚካሄድ ውድድር ነው።
የፊታችን ቅዳሜ 20ኛው የውድድር መድረክ ሁለተኛው ተከታታይ የአልፕ ዲ ሁዌዝ (Alpe d’Huez) ፍልሚያ ሲሆን፣ የቢጫ ማሊያው አሸናፊ እዚህ ውድድር ላይ ሙሉ በሙሉ የሚለይበት ነው።
የፊታችን እሁድ 21ኛው የውድድር መድረክ በፓሪስ ሻምፕስ-ኤሊሴ (Champs-Élysées) የሚደረገው የክብርና የማጠናቀቂያ ውድድር ከተካሄደ በኋላ የዘንድሮ ውድድር ይጠናቀቃል።
