የአርሴናሊ የኋላ ደጀን ሳሊባ በዓለም ዋንጫው ወቅት ፈረንሳይን ወክሎ ሲጫወት በጀርባ ህመም ሲሰቃይ የነበረ ሲሆን፣ በግማሽ ፍጻሜው ከስፔን ጋር በነበረው ጨዋታ በ30ኛው ደቂቃ ላይ ህመሙ በርትቶበት ለመቀየር ተገዷል።

ተጫዋቹ ወደ ለንደን ከተመለሰ በኋላ በልዩ ባለሙያዎች ከፍተኛ ምርመራ የተደረገለት ሲሆን፣ ቀዶ ጥገና (Surgery) እንደማያስፈልገው ተረጋግጧል።

አርሰናል ባወጣው ይፋዊ መግለጫ በሳሊባ ላይ የተደረጉት ሰፊ የሕክምና ግምገማዎች ቀዶ ጥገና (Surgery) እንዳማያስፈልገው (NOT recommended) በምክረ-ሐሳብ ደምድመዋል።

ተጫዋቹ ወዲያውኑ የተቀናጀና ጥንቃቄ የተሞላበት የማገገሚያ ፕሮግራም (Structured Rehabilitation Programme) መጀመር እንዳለበት ተገልጿል።

ጉዳቱን በተከታታይ እያከሙ መሄድ ስለሚያስፈልግ፣ ሳሊባ ለረጅም ጊዜ” (Extended Period) ከጨዋታ ውጭ ሆኖ እንደሚቆይ ክለቡ በይፋ አረጋግጧል።

ይህንን ይፋዊ መግለጫ ተከትሎ አርሰናል በመከላከል መስመሩ ላይ የገጠመውን ትልቅ ክፍተት ለመሙላት የጆን ስቶንስን ዝውውር በከፍተኛ ሁኔታ ለማፋጠን እየሞከረ ይገኛል።

ምንም እንኳን ቀዶ ጥገና ባያስፈልገውም፣ ጉዳቱ ሙሉ በሙሉ እስኪድን ድረስ ለረጅም ጊዜ (Extended Period) ከሜዳ እንደሚርቅና ልዩ የማገገሚያ ፕሮግራም (Rehabilitation) እንደሚጀምር ክለቡ ገልጿል።

አርሰናል የኢንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዋንጫ ጨዋታውን ነሐሴ 15 (August 21) ከኮቨንትሪ ሲቲ ጋር ሲጀምር ሳሊባን የመጠቀም ዕድል አይኖረውም።

የአርሰናል አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ዊሊያም ሳሊባን ለመተካትና ክፍተቱን ለመሙላት ዋና ዋና ታክቲካዊ አማራጮችና የዝውውር እቅዶች አሉት የመጀመሪያው የጋብርኤልና የቤን ኋይት ጥምረት፤ ቤን ኋይት ወደ ቀድሞ ቦታው በመመለስ ከጋብርኤል ማጋሌሽ ጋር በመሀል ተከላካይነት ይሰለፋል።

በቀኝ ተከላካይ መስመር ዩሪየን ቲምበር ይጫወታል።ሪካርዶ ካላፊዮሪ የመሀል ተከላካይ አማራጭ ሊሆን ይችላል ጣሊያናዊው ተከላካይ ሪካርዶ ካላፊዮሪ በግራ መስመር ብቻ ሳይሆን በመሀል ተከላካይነት የመጫወት ከፍተኛ ብቃት አለው። ካላፊዮሪ ከመሀል ወደ መስመር እየወጣ የማጥቃት ክፍሉን እንዲያግዝ (Inverted Full-back) በማድረጉ በኩል አርቴታ አዲስ የጨዋታ ስልት ሊጠቀም ይችላል።

በአካዳሚው የሚገኙ ወጣት ተከላካዮች በቅድመ-ውድድር ዝግጅት ጨዋታዎች ላይ የመሰለፍ ዕድል ያገኛሉ።

የአርሰናል አዲስ የዝውውር እቅድ

ሳሊባ ረጅም ጊዜ የሚርቅ በመሆኑ አርሰናል በአስቸኳይ ሌላ የቀኝ መሀል ተከላካይ (Right-sided Center-back) ለማስፈረም ገበያ ውስጥ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል።

እንግሊዛዊው ተከላካይ ጆን ስቶንስ (John Stones) ከማንቸስተር ሲቲ ጋር በይፋ መለያየቱ ይታወሳል፤በነፃ ዝውውር(Free Agent) ወደ ቡድኑ ሊመጣ ይችላል፤ጆን ስቶንስ ለ10 ዓመታት በስኬት ያገለገለበትን የማንቸስተር ሲቲ ክለብ ኮንትራቱ በሰኔ ወር መጨረሻ በማብቃቱ በነፃ ዝውውር ነው ክለቡን የለቀቀው። በሲቲ ቆይታው 6 የፕሪሚየር ሊግ፣ 1 የሻምፒዮንስ ሊግና በርካታ የዋንጫ ስኬቶችን ማሳካቱ ይታወሳል።

ይሁንና አርሰናል ከቼልሲ ጋር የዝውውር ፍልሚያ ይጠብቀዋል፤

የአርሰናል ፈላጊነት የመነጨው ከዊሊያም ሰሊባ በጀርባ ጉዳት ምክንያት ለረጅም ጊዜ ከሜዳ እንደሚርቅ መረጋገጡን ተከትሎ ነው፣ አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ልምድ ያለውን ጆን ስቶንስን በነፃ ዝውውር ወደ አርሰናል ለማምጣት በከፍተኛ ሁኔታ እየገፋበት ይገኛል። አርቴታ ተጫዋቹን በማንቸስተር ሲቲ በረዳት አሰልጣኝነት በነበረበት ወቅት በቅርብ ያውቀዋል።

አዲስ አሰልጣኝ የቀጠረው ቼልሲ የጆን ስቶንስን ዝውውር ለመጥለፍና ወደ ስታምፎርድ ብሪጅ ለማምጣት ንግግር መጀመሩ ትልቅ አነጋጋሪ ዜና ሆኗል። አዲሱ የቼልሲ አሰልጣኝ ዣቢ አሎንሶ በቡድኑ ውስጥ ልምድ ያለው ተከላካይ ስለሚፈልግ ክለቡ ለስቶንስ ጥያቄ አቅርቧል።

ስቶንስ በዓለም ዋንጫው ያሳየው ብቃት አስገራሚ ነበር፤ምንም እንኳን ባለፈው የውድድር ዘመን በማንቸስተር ሲቲ በጉዳት ምክንያት የጨዋታ ዕድል ቢያጣም፣ በ2026ቱ የዓለም ዋንጫ ላይ ለእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን እጅግ ድንቅ ብቃት ማሳየቱ በገበያ ላይ ያለውን ዋጋ መልሶ ከፍ አድርጎታል።

Facebooktwitterlinkedinyoutubetumblrinstagramflickrfoursquaremail
Facebooktwitterredditpinterestlinkedintumblrmail

By admin

Hello, dear. I am Wosenseged Mersha Demissie. Author, Journalist, and Sociological Criticism. He has worked in several media in Ethiopia and foreign media also. I have come to my country, Ethiopia, from abroad, and for the past eight years, I have been giving political analysis and writing in magazines, newspapers, and televisions on all the free press in Ethiopia. I have six books that I wrote and published during my stay abroad and after I came back to my country and are on the market. Above all, I feel spiritual satisfaction for coming from a developed country and working in a country where there is no freedom of the press. I have sacrificed a lot in this profession. Imprisonment, abuse—I was crushed economically. I have been living separately from my family for many years, but I am happy and proud of my career to be a voice for the voiceless people of Ethiopia, whom I love and respect by working in the press without payment. After leaving my country and returning to my country, Growing up in Arat Kilo, YMCA, I was exposed to various sports. I know many sports. I have worked as a referee, player, and tournament organizer. As a result, I have worked as a sports editor on radio, television, and newspapers for many years. I have worked alongside other media outlets for more than 20 years by preparing and publishing my own sports newspaper called San George.I have traveled to many countries, including Europe, the Far East, Asia, Oceania, and Africa, and have been present at many competitions, including athletics.This is because I have this love for sports. I have reopened this media outlet for sports. In addition to this, I have worked for the past 30 years. May God protect Ethiopia and its people and give peace and love to our world. Thank you anyway. Wosenseged Mersha Demissie Author, Journalist, Sociological Criticism

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *