ለአፍሪካ ዋንጫ ለሴካፋ ዞን የታዳጊዎች የማጣርያ ውድድር ብሔራዊ ቡድኑን የሚወክሉትን ተጨዋቾች ለመመልመል ሥራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ገለጸ ።

ፌዴሬሽኑ እንዳለው በቀጣይ ዓመት መጀመርያ ለሚካሄዱት ከ17 እና ከ20 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ ሴካፋ ዞን የማጣርያ ውድድሮች ለሁለቱም የዕድሜ እርከን ብሔራዊ ቡድኖቻችን ብቁ የሚሆኑ ተጫዋቾችን ለመለየት እንዲያስችል የናሽናል ካምፒንግ የመጀመርያ ምዕራፍ ዛሬ ተጀምሯል ብሏል።

በሁለቱ የዕድሜ እርከኖች በጠቅላላው 81 ተጫዋቾች ትናንት ሐምሌ 18 የተሰባሰቡ ሲሆን የናሽናል ካምፒንጉ የመጀመርያ ምዕራፍ እስከ ዓርብ ሐምሌ 24 ድረስ የሚቆይ ይሆናል ሲልም ገልጿል።

በመስከረም ወር ታንዛንያ ላይ እንደሚካሄድ በሚጠበቀው ከ20 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ የሴካፋ ዞን ማጣርያ ውድድር ላይ ለሚሳተፈው የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ብቁ የሚሆኑ ተጫዋችን ለመመልመል በዚህ ምዕራፍ 41 ተጫዋቾችን በማሰባሰብ የምልመላ ሒደት የተጀመረ ሲሆን በናሽናል ካምፒንጉ ላይ ከ2 ወራት በፊት በሞሮኮ በተካሄደው ከ17 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ ላይ ድንቅ ጉዞ አድርጎ ከነበረው ቡድን፣ በአፍሪካው ዋንጫ ስብስብ ውስጥ መካተት ያልቻሉ እና በባለፈው ዓመት ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ካምፒንግ ተከታታይ ስልጠና ሲያገኙ የነበሩ  እንዲሁም ከኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ፕሪምየር ሊግ ውድድር ላይ የተመለመሉ ተጫዋቾች መካተታቸውን ገልጿል።

ከዚህ ሌላ ከ17 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ የሴካፋ ዞን የማጣርያ ውድድር በሩዋንዳ አስተናጋጅነት ጥቅምት ወር ላይ እንደሚካሄድ ሲጠበቅ በዚህ ውድድር ላይ ተሳታፊ ለሚሆነው የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ቡድን ተጫዋቾችን የመመልመል ሒደት ለማከናወን 40 ተጫዋችችን በማሰባሰብ የናሽናል ካምፒንጉ ተጀምሯል። ከሁለት ሳምንት በፊት በአዲስ አበባ እና አዳማ ከተማ የውስጥ ውድድሮች ላይ ተመልምለው የሪጅናል ካምፒንግ በማከናወን ስልጠና የተሰጣቸው 40 ታዳጊዎች የዚህ ካምፒንግ አካል ሆነዋል በማለትም ተናግሯል።

የናሽናል ካምፒንግ የመጀመርያ ምዕራፍ ዛሬ ሲጀመር በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ስድስት ኪሎ ካምፓስ ሜዳ በሁለቱም የዕድሜ እርከን የተመረጡት ሁሉም ተጫዋቾች የአካል ብቃት ምዘና ተከናውነው በማስከተል ቡድኖቹ በተናጠል የእርስ በርስ ጨዋታ በማከናወን የተጫዋቾች ብቃት ምዘና መካሄዱን ፌዴሬሽኑ አሳውቋል።

Facebooktwitterlinkedinyoutubetumblrinstagramflickrfoursquaremail
Facebooktwitterredditpinterestlinkedintumblrmail

By admin

Hello, dear. I am Wosenseged Mersha Demissie. Author, Journalist, and Sociological Criticism. He has worked in several media in Ethiopia and foreign media also. I have come to my country, Ethiopia, from abroad, and for the past eight years, I have been giving political analysis and writing in magazines, newspapers, and televisions on all the free press in Ethiopia. I have six books that I wrote and published during my stay abroad and after I came back to my country and are on the market. Above all, I feel spiritual satisfaction for coming from a developed country and working in a country where there is no freedom of the press. I have sacrificed a lot in this profession. Imprisonment, abuse—I was crushed economically. I have been living separately from my family for many years, but I am happy and proud of my career to be a voice for the voiceless people of Ethiopia, whom I love and respect by working in the press without payment. After leaving my country and returning to my country, Growing up in Arat Kilo, YMCA, I was exposed to various sports. I know many sports. I have worked as a referee, player, and tournament organizer. As a result, I have worked as a sports editor on radio, television, and newspapers for many years. I have worked alongside other media outlets for more than 20 years by preparing and publishing my own sports newspaper called San George.I have traveled to many countries, including Europe, the Far East, Asia, Oceania, and Africa, and have been present at many competitions, including athletics.This is because I have this love for sports. I have reopened this media outlet for sports. In addition to this, I have worked for the past 30 years. May God protect Ethiopia and its people and give peace and love to our world. Thank you anyway. Wosenseged Mersha Demissie Author, Journalist, Sociological Criticism

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *