ፍፁም ጥላሁን ከቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ መውጫ በር ላይ ቆሟል

የኢትዮጵያ ብ/ቡድን እና የቅዱስ ጊዮርጊስ ድንቁ የፊት መስመር ተጫዋች የሆነው ፍፁም ጥላሁን ውሉ ማለቁን ተከትሎ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር እስከ አሁኗ ሰዓት ድረስ ንግግር ያላደረገ ሲሆን ምን አልባት ነገሩ በዝህ ከቀጠለ ከፈረሰኞቹ ጋር ሊለያይ ይችላል ተብሏል ።
የቀድሞ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድንና የቡና ተጨዋች የሆነው አንዳርጋቸው በፌስቡክ ላይ እንደገለጸው ፍፁም ጥላሁን የዘንድሮ አመት የፕሪሚየር ሊጉ ድንቅ ተጫዋች ከመሆን አልፎ በብ/ቡድን ከማላዊ ጋር በነበረው ጨዋታ አንድ ጎል በማግባት እና አንድ አሲስት በማድረግ ምርጥ ኳሊቲ እንዳለሁ ገልጿል ።
ፍፁም ጥላሁን ቅዱስ ጊዮርጊስ ችግር ውስጥ በነበረበት ወቅት ከሁለት ወር በላይ ደሞዝ ስላልተከፈላቸው ክለቡን መልቀቅ እየቻለ እሱ ግን በዛን ወቅን ክለቡን እና ደጋፊውን አክብሮ ክለቡን በሚገባ ከጓደኞቹሁ ጋር እንደጠቀመ ገልጾ ውሉን ማለቁን ተከትሎ ክለቡ ውሉን ካላደሰለት ክለቡን እንደሚለቅ ተናግሯል ።
