የቡና ደጋፊዎች የፊታችን እሁድ በ4 ኪሎ ወወክማ ይሰባሰባሉ

የኢትዮጵያ ቡና ደጋፊዎች ማህበር ጠቅላላ ጉባኤውን የፊታችን እሑድ ሀምሌ 26/11/2018 ከጠዋቱ 2:30 ጀምሮ በ4ኪሎ የአዲስ አበባ ወጣቶች ማህከል የቀድሞው 4ኪሎ ወወክማ አዳራሽ ጉባኤያቸውን ይካሄዳል።

ስለሆነም የኢትዮጵያ ቡና ደጋፊዎች ማህበር መታወቂያ ያለው ሁሉም የክለቡ ደጋፊዎች ያደሰም ያላደሰም ደጋፊ ማሊያ በመልበስ መገኘት እንደሚችል የኢትዮጵያ ቡና ደጋፊዎች ማህበር አስታውቋል። በነገራችን ላይ የመሰብሰቢያውን አዳራሽ ስለማውቀው በጣም ጠባብ ነው ፤አደራሹ እንኳን ለክለብ ደጋፊዎች ለተለያዩ ኮርሶችና ለሴሚናር ተሳታፊዎች የማይበቃ ነው፤የክለቡ ደጋፊዎች ማህበር በርካታ ደጋፊዎች ያሉት በመሆኑ የህጻናት ቲያትር ማሳያ የነበረውን አዳራሽ ወይንም ጅምናዚየሙ ውስጥ ስብሰባውን ለማካሄድ እንዲችል ከወዲሁ የስብሰባውን ማካሄጃ ቦታ ሊያመቻች ይገባል ባዮች ነን ።
