
የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን አጥቂ የሆነችው ንግስት በቀለ በአውሮፓ የሙከራ ዕድል ተሰጧት በፈረንሳዩ የሴቶች ሁለተኛ ሊግ ክለብ ኤፍ ሲ ሜትዝ (FC Metz) የሙከራ ዕድል ተሰጥቷት ፈረንሣይ እንደምትገኝ ተገልጿል ።
ለተጫዋቿ የሙከራ ዕድል የሰጣት ክለብ ሜትዝ በአሁኑ ወቅት በ2ተኛው የሊግ እርከን በመሳተፍ ላይ የሚገኝ እና በ1974 የተመሰረተ ሲሆን ባለፈው የውድድር ዓመት 12ኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቋል ፤ የሴቶች እግር ኳስ ከፍተኛ ትኩረት በሚሰጥበት ፈረንሳይ ውስጥ የሚገኝ አንጋፋ ክለብ ነው።
በኢትዮጵያ የሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ውስጥ ለኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ፣ ለቦሌ ክፍለ ከተማ፣ ለመቻል (መከላከያ) እና ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ክለቦች በአጥቂነት ተጫውታለች።
በኢትዮጵያ የሴቶች ብሔራዊ ቡድን ውስጥ በሁሉም የዕድሜ ክልሎች (በታችኛው የዕድሜ እርከን እና በዋናው ቡድን) ሀገሯን አገልግላለች።
መስከረም 16 ቀን 1997 ዓ.ም (ሴፕቴምበር 26, 2004 እ.ኤ.አ) አዲስ አበባ ውስጥ ተወለደች።
የመስመር አጥቂ (Winger) እና አጥቂ (Forward) ሆና ትጫወታለች። ፈጣንና የግብ ዕድሎችን በመፍጠር ረገድ የተዋጣላት ተጫዋች ናት።
በክለብ እና ብሔራዊ ቡድን ደረጃ
ለኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ፣ ለቦሌ ክፍለ ከተማ፣ ለመቻል እና ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ (CBE) ተጫውታለች። በቅርቡ ደግሞ ከነገሌ አርሲ ክለብ ጋር ጥሩ የውድድር ዘመን አሳልፋለች።
ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ (CBE) የሴቶች ቡድን ጋር በካፍ የሴቶች ሻምፒዮንስ ሊግ (CAF Women’s Champions League) ላይ ተሳትፋለች ።
በኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች (U-20) እና በዋናው የሴቶች ብሔራዊ ቡድን (ሉሲዎቹ) ውስጥ በመስመር አጥቂነት በቋሚነት በመሰለፍ ሀገሯን እያገለገለች ትገኛለች።
