ሀላባ ከነማ የወሳኝ ተጨዋቾችን ውል እያራዘመ ነው

0
IMG_20260731_192625_724

በትላንትናው ዕለት ወደ ተጫዋቾች ዝውውር ገበያ በስፋት በመግባት የአምስት አዳዲስ ፈራሚዎችን ዝውውር ማጠናቀቃቸውን ያበሰሩት በአሰልጣኝ በሽር አብደላ የሚመሩት «በርበሬዎቹ»፣ በዛሬው ዕለት ደግሞ የወሳኙን የመስመር አጥቂ የዮናታን ሐይሉን ውል ማራዘማቸውን ይፋ አድርገዋል።

​በዝውውር መስኮቱ ከተለያዩ የሀገራችን ክለቦች ጋር ስሙ በተደጋጋሚ ሲያያዝ የቆየው የቀድሞው የደደቢት መስመር አጥቂ፤ በ2018 በከፍተኛ ሊጉ ወደ አዲሱ ምዕራፍ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ባሳደገው ምርጥ የሚባል ግዜ ባሳለፈው ክለቡ ሀላባ ከነማጋር ለመቀጠል በመስማማት አዲሱን ውሉን አራዝሟል።

በሌላ በኩል​ የነባር ተጫዋቾችን ውል እያራዘመ እና አዳዲስ ተጨዋቾችን ወደ ቡድኑ እየቀላቀለ የሚገኘው ሀላባ ከነማ የአማካይ ስፍራ ተጫዋቹን ብሩክ ቦጋለን ውል አራዝሟል።

​የቀድሞው የደሴ እና የአዳማ የመሀል ሜዳ ተጫዋች ባሳለፍነው የውድድር አመት ከክለቡ ጋር የማይረሳ ጊዜን ያሳለፈው ብሩክ ቦጋለ፣ ከሀላባ ከነማ ጋር ለተጨማሪ አመት ለመቆየት ተስማምቷል።

Facebooktwitterlinkedinyoutubetumblrinstagramflickrfoursquaremail
Facebooktwitterredditpinterestlinkedintumblrmail