ብሩኖ ጊማሬሽ (Bruno Guimarães) ወደ አርሰናል የሚያደርገው ዝውውር የመጨረሻ ምዕራፍ ላይ ደርሷል። አብዛኞቹ ታማኝ ዓለም አቀፍ የስፖርት መገናኛ ብዙኃን ዝውውሩ በዚህ ቅዳሜና እሁድ ሙሉ በሙሉ እንደሚጠናቀቅ እየዘገቡ ይገኛሉ።

የስምምነቱ ዝርዝር ሁኔታ

አርሰናል ለኒውካስል ዩናይትድ 70 ሚሊዮን ፓውንድ ቋሚ ክፍያ (ከ90 ሚሊዮን ዩሮ በላይ) እና በተጨማሪ 10 ሚሊዮን ፓውንድ ማበረታቻ (Performance-related bonuses) በድምሩ 80 ሚሊዮን ፓውንድ ለመክፈል ሙሉ ስምምነት ላይ ደርሷል።

የ28 ዓመቱ ብራዚላዊ አማካኝ ከአርሰናል ጋር እስከ ሰኔ 2031 ዓ.ም (ለአምስት ዓመታት) የሚቆይ ውል ለመፈረም የግል ጥቅማጥቅሞችን ሙሉ በሙሉ ተስማምቷል።

ጊማሬሽ በኒውካስል የቅድመ-ውድድር ዝግጅት ስብስብ ውስጥ ያልተካተተ ሲሆን፣ በዚህ ሳምንት መጨረሻ ለሕክምና ምርመራ እና ፊርማውን ለማኖር ወደ ለንደን እንደሚያቀና ESPN ዘግቧል

ከኒውካስል በኩል ያለው መረጃ

ኒውካስል አካባቢ የሚወጡ አንዳንድ የአገር ውስጥ ጋዜጠኞች (እንደ ሊ ራይደር ያሉ) ክለቡ አዲስ ለሚሾመው አሰልጣኝ ማትያስ ጃይስሌ (Matthias Jaissle) ዕድል ለመስጠት ዝውውሩ ገና በይፋ አልተቋጨም ቢሉም፣ የዴቪድ ኦርንስታይን (The Athletic) እና የቢቢሲ (BBC Sport) መረጃዎች ግን ዝውውሩ ወደኋላ እንደማይመለስና መጠናቀቁ አይቀሬ መሆኑን እያረጋገጡ ነው።

ሩኖ ጊማሬሽ ዛሬ የሕክምና ምርመራውን ያደርጋል ተብሎ የነበረ ቢሆንም ሕክምናውን ግን አላደረገም፤ ነገር ግን የመጨረሻ ስምምነት ላይ ስለተደረሰ የሕክምና ምርመራው በሚቀጥለው ሰኞ (ነሐሴ 3 ቀን 2026 እ.አ.አ) እንዲያደርግ ቀጠሮ ተይዞለታል።

ስለ ዝውውሩ የመጨረሻ ምዕራፍ የወጡት ትኩስ ዝርዝር መረጃዎች የሚከተሉት ናቸው፦

አርሰናል በለንደን ኮልኒ (London Colney) የሥልጠና ማዕከሉ ለተጫዋቹ የሕክምና ምርመራ ለማድረግ የሰኞውን ዕለት በይፋ  ቀጠሮ ይዟል።

እንደ የቫን ቃሳግራንዴ (Venê Casagrande) መረጃ አርሰናል ለኒውካስል ዩናይትድ 75 ሚሊዮን ፓውንድ ቋሚ ክፍያ ለመክፈል የተስማማ ሲሆን፣ ከሌሎች ማበረታቻዎች ጋር በአጠቃላይ ሂሳቡ 80 ሚሊዮን ፓውንድ ይደርሳል።

ተጫዋቹ መጀመሪያ ከተባለው አምስት ዓመት ይልቅ እስከ ሰኔ 2030 ዓ.ም ድረስ (ለ4 ዓመታት) በለንደን ለመቆየት በግል ጥቅማጥቅሞች ላይ ሙሉ ስምምነት ላይ ደርሷል።

Facebooktwitterlinkedinyoutubetumblrinstagramflickrfoursquaremail
Facebooktwitterredditpinterestlinkedintumblrmail

By admin

Hello, dear. I am Wosenseged Mersha Demissie. Author, Journalist, and Sociological Criticism. He has worked in several media in Ethiopia and foreign media also. I have come to my country, Ethiopia, from abroad, and for the past eight years, I have been giving political analysis and writing in magazines, newspapers, and televisions on all the free press in Ethiopia. I have six books that I wrote and published during my stay abroad and after I came back to my country and are on the market. Above all, I feel spiritual satisfaction for coming from a developed country and working in a country where there is no freedom of the press. I have sacrificed a lot in this profession. Imprisonment, abuse—I was crushed economically. I have been living separately from my family for many years, but I am happy and proud of my career to be a voice for the voiceless people of Ethiopia, whom I love and respect by working in the press without payment. After leaving my country and returning to my country, Growing up in Arat Kilo, YMCA, I was exposed to various sports. I know many sports. I have worked as a referee, player, and tournament organizer. As a result, I have worked as a sports editor on radio, television, and newspapers for many years. I have worked alongside other media outlets for more than 20 years by preparing and publishing my own sports newspaper called San George.I have traveled to many countries, including Europe, the Far East, Asia, Oceania, and Africa, and have been present at many competitions, including athletics.This is because I have this love for sports. I have reopened this media outlet for sports. In addition to this, I have worked for the past 30 years. May God protect Ethiopia and its people and give peace and love to our world. Thank you anyway. Wosenseged Mersha Demissie Author, Journalist, Sociological Criticism

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *