አቶ ኢሳያስ ጅራ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንታዊ ተወዳዳሪነት የቀረቡ ብቸኛ ዕጩ መሆናቸው ተገለጸ

0
IMG_20260820_080108_041

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የምርጫ አስፈፃሚ ኮሚቴ ሐምሌ 22 ቀን 2018 ዓ.ም ለፌዴሬሽኑ የጠቅላላ ጉባኤ አባላት በላከው ደብዳቤ መስከረም 5 ቀን 2019 ዓ.ም ለሚደረገው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንታዊ እና በፕሬዝዳንቱ አቅራቢነት የሚመረጡ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ከነተጠባባቂያቸው በፌዴሬሽኑ መተዳደሪያ ደንብ መሰረት እስከ ነሐሴ 4 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ለፌዴሬሽኑ ጽ/ቤት እንዲልኩ ማሳወቁ ይታወሳል፡፡

ኮሚቴው ነሐሴ 5 ፣ ነሐሴ 11 እንዲሁም ነሐሴ 13 ባደረጋቸው ስብሰባዎች የቀረቡ እጩዎችን ሰነድ የምርመራ እና የማጣራት ተግባር አከናውኗል፡፡ በዚህም መሠረት ለዕጩ ፕሬዝዳንታዊ ተወዳዳሪነት የቀረቡት ብቸኛ ተወዳዳሪ አቶ ኢሳያስ ጅራ ቦሾ መሆናቸውን አሳውቋል።

Facebooktwitterlinkedinyoutubetumblrinstagramflickrfoursquaremail
Facebooktwitterredditpinterestlinkedintumblrmail