የአፍሪካ ዋንጫ የማዘጋጀት ሰነድ ማዘገባትና የመጀመሪያ የማጣሪያ ጨዋታ

ኢትዮጵያ የ2028ቱን የአፍሪካ ዋንጫ ለማስተናገድ ጥያቄዋን ያቀረበችበት ሰነድ (Bid Document) ለአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) አስገባች
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከኢፌዴሪ መንግሥት ጋር በጋራ አስፈላጊ ዶክመንቶችን ያካተተ ሰነድ (BID HAND BOOK) ለካፍ በማስገባት ይህንን ታላቅ አህጉራዊ የእግር ኳስ ድግስ ለአራተኛ ጊዜ በስኬት ለማስተናገድና በአፍሪካ እግር ኳስ ያላትን ጉልህ ታሪክ ዳግም ለማደስ ዝግጁነቷን አረጋግጣለች።

በሌላ በኩል የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ የምድብ 10 የመጀመርያ ጨዋታ ሱዳንን የሚገጥምበት ቀን እና ቦታ ታውቋል።
የሱዳን እግር ኳስ ማኅበር የሜዳውን ጨዋታ ለማድረግ የደቡብ ሱዳኑ ጁባ ናሽናል ስታዲየምን መምረጡን አሳውቋል። በዚህም መሠረት ጨዋታው ዓርብ መስከረም 15 ቀን 2019 ዓ/ም ምሽት 1:00 ላይ ይካሄዳል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ከ23 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ድልድል ይፋ ሲሆን ኢትዮጵያ በመጀመርያው ዙር ከዩጋንዳ ጋር ተደልድላለች። ጨዋታዎቹ ከመስከረም 10-26 ሲደረጉ ወደ ተከታዩ ዙር የሚያልፈው ሀገር በሁለተኛው ዙር ሞሮኮን የሚገጥም ይሆናል።
