መድን በወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ እግር ኳስ ክለብ ላይ ክስ አቀረበ

ኢትዮጵያ መድን በወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ እግር ኳስ ክለብ የስም ማጥፋት ወንጀል ተፈፅሞብኛል በሚል ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌድሬሽን የአራት ገፅ የቅሬታ ደብዳቤን ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌድሬሽን አስገብቷል።

ኢትዮጵያ መድን በ37ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ
ጨዋታ 3ለ0 በሆነ ውጤት በምድረገነት ሽረ መሸነፉን ተከትሎ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ በጨዋታው መላቀቆች ነበሩበት ይመርመርልኝ መድኖች ሆን ብለው ለቀዋል በማለት የክስ ደብዳቤን ማስገባታቸው ከቀናት በፊት ይታወሳል።
