
ከጨዋታ ማጭበርበር ጋር በተገናኘ ፌድሬሽኑ ያለውን እውቀትና የቀረበ ፎርማል ቅሬታ ያለ እንደሆነ በሚል ለፌድሬሽኑ ዋና ፀሃፊ አቶ ባህሩ ጥላሁን ገለጹ ፤
«በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 37ኛ ሳምንት ውድድሮች ላይ ሊኖር ይችላል ተብሎ ስለሚነሳው የጨዋታ ማጭበርበር (match-fixing) ስጋትና ውንጀላ እናውቃለን። ጉዳዩንም በከፍተኛ ትኩረትና ጥንቃቄ እየተከታተልነው ነው።
ሊግ ካምፓኒው ውድድሩን በበላይነት ሚያስተዳድረው አካል እሱ መሆኑን ልብ ማለት ያስፈልጋል። በዚህ ኃላፊነቱ መሰረትም ከጨዋታ ኮሚሽነሮች፣ ከዳኞች እንዲሁም ሁኔታውን ለመመርመር ቀድሞውኑ ከተቋቋመው ገለልተኛ ኮሚቴ በሚቀርቡ ሪፖርቶች መሰረት ሙሉ ምርመራ የማካሄድ ሃላፊነት አለበት።
እስካሁን ድረስ ወደ እኛ(ፌድሬሽን) በይፋ የቀረበ ምንም አይነት አቤቱታ የለም። እስካሁን ያየነው በማህበራዊ ሚዲያ ሚዘዋወሩ ነገሮችን ነው።
ሆኖም የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ይህን ጉዳይ በሚገባው ክብደት ልክ እየተመለከተው ነው።
በይፋ ሚቀርቡ ሪፖርቶችን ወይም አቤቱታዎችን በጥንቃቄ እንመረምራለን፤ በሕግና በተቀመጡ ሥነ-ሥርዓቶች መሰረትም ተገቢውን እርምጃ እንወስዳለን።
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ታማኝነትንና ግልጽነትን መጠበቅ ከሁሉም በላይ ቅድሚያ ምንሰጠው ጉዳያችን ነው። እናመሰግናለን”
