ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድናችን የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የሴካፋ ዞን ማጣሪያ የምድብ ተጋጣሚዎቹን አወቀ

ዘጠኝ ብሔራዊ ቡድኖች በሚሳተፉበት ውድድርም በምድብ ሁለት ከደቡብ ሱዳን እና ሩዋንዳ ተደልድሏል።
ውድድሩ ከመስከረም 6 እስከ መስከረም 20 ድረስ በታንዛኒያ አስተናጋጅነት ይደጋል።

ለፍፃሜ የሚደርሱ ብሔራዊ ቡድኖች ወደ የ20 ዓመት በታች አፍሪካ ተሳታፊ መሆናቸውን ያረጋግጣሉ።
25 ተጫዋቾች የያዘው ቡድኑ በሀዋሳ ከተማ በትናንትናው ዕለት ዝግጅቱን ጀምሯል።
ኢትዮጵያ በአፍሪካ ከ20 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ የተሳተፈችው ከ25 ዓመታት በፊት አዘጋጅ በነበረችበት ውድድር ነበር።
