
የሰውነት ቢሻው ከ17 ዓመት በታች አካዳሚ ከትውልደ ኢትዮጵያዊው አሸናፊ ግርማ የካናዳ የእግር ኳስ አካዳሚ ጋር የወዳጅነት ውድድር አደረገ።
የእግር ኳስ ልምድ ልውውጥን ዓላማ ያደረገው ይህ ውድድር የአካዳሚው ታዳጊዎች በስልጠና ያዳበሩትን ክህሎት በተግባር እንዲያሳዩ አግዟቸዋል።

በአሰልጣኝ ሰውነት ቢሻው የሚመራው እና ታዳጊ ተጫዋቾችን አያፈራ የሚገኘው በአሸናፊ ግርማ ከሚመራው ትውልደ ኢትዮጵያዊ የካናዳ የእግር ኳስ አካዳሚ ጋር ያደረገው የወዳጅነት ጨዋታ ከፍተኛ ትኩረት የሳበና እጅግ አስተማሪ የሆነ ጨዋታ ሆኗል።
ይህ የወዳጅነት ጨዋታ ከሀገር ውጪ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ስፖርተኞች ከትውልድ ሀገራቸው ጋር ያላቸውን ቁርኝትና ለወጣቱ ትውልድ እድገት የሚያደርጉትን አስተዋጽኦ በግልጽ ያሳያል።

እንደዚህ ያሉ የፉክክር መድረኮች የታዳጊዎችን የአዕምሮ ዝግጁነት፣ የሜዳ ላይ ልምድ እና የውድድር መንፈስ ከፍ ከማድረግ አንፃር ያለው ፋይዳ እጅግ የላቀ ነው።
በቀጣይነትም የኢትዮጵያን እግር ኳስ ከስር መሰረቱ በመገንባት ረገድ የአካዳሚዎች ትብብር ምን ያህል ወሳኝ እንደሆነ ይህ ውድድር ማሳያ ሆኗል።
በሁለቱ አካዳሚዎች በተካሄደው የወዳጅነት ጨዋታ የሰውነት ቢሻው የእግር ኳስ አካዳሚ የአሸናፊ ግርማን የእግር ኳስ አካዳሚ 2ለ0 አሸንፏል።
