
የሴኔጋል አሰልጣኝ ፓትሪክ ቪየራን ጨምሮ 12 ዲያስፓራ ተጨዋቾችን ይዛ ወደ ኢትዮጵያ ልትመጣ ነው
ኤርትራ በሚያስገርም ሁኔታ 27 ዲያስፓራ ተጨዋቾችን ለደቡብ አፍሪካ ጨዋታ ጠራች
የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ኮከብ ግብ አግቢም ተመርጡዋል
ከነዓን እና ጋቶች ብቸኛ ተጨዋቾች ናቸው

የ2027 የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ ከሃያ አራት ቀናት በሃላ ይጀመራል።ይህንን ተከትሎ በማጣሪያው የሚካፈሉ ሃገራት ስብስባቸውን ይፋ እያደረጉ ይገኛሉ።
የዋሊያዎቹ አሰልጣኝ ዬሃንስ ሳህሌ ሁለት ኢንተርናሽናል ተጨዋቾችን ጨምሮ ለአርባ ተጨዋቾች ጥሪ በማድረግ ዝግጅት ከጀመሩ 15 ቀናት ሊሞላቸው ተቃርበዋል።
ከኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ጋር የመጀመሪያዎቹን ሁለት ጨዋታዎች የሚያደርጉት ሱዳንና ሴኔጋል በቀጣዩ አስር ቀናት ስብስባቸውን ይፋ እንደሚያደርጉ ተሰምታል።
መስከረም 19/2019 ዓ.ም የኢትዮጵያን ብሄራዊ ቡድን የምትፋለመው ሴኔጋል ወደ 12 የሚደርሱ ዲያስፓራ ተጨዋቾችን በማካተት ወደ ኢትዮጵያ እንደምትመጣ ከዳካር የሚወጡ መረጃዎች ያመላክታሉ።

ሴኔጋል በ2026ቱ የዓለም ዋንጫ 10 ዲያስፓራ ተጨዋቾችን አካታ የነበረ ሲሆን የወቅቱ የብሄራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ ፓትሪክ ቪየራም የፈረንሳይ ዜግነት ያለው ዲያስፓራ አሰልጣኝ መሆኑ ርግጥ ነው።
ይህም የካራንጋ አንበሶች በዲያስፓራ ተጨዋቾች ላይ የተገነባ መሆኑን ያመላክታል።በ2026ቱ የዓለም ዋንጫ 98 ዲያስፓራ ተጨዋቾች ለተለያዩ ሃገራት ብሄራዊ ቡድን ተጫውተዋል።
ከሶስት ሳምንት በሃላ በሚጀመረው የ2027 የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ በምድብ 4 የተደለደለችው ኤርትራ መስከረም 13 ከኬንያ መስከረም 19 ደግሞ ከደቡብ አፍሪካ ለምታደርገው የማጣሪያ ጨዋታ ዛሬ ለ30 ተጨዋቾች ጥሪ አደርጋለች።
በሚያስገርም ሁኔታ ግብፃዊው አሰልጣኝ የቀይ ባህር ግመሎች በሚል ቅፅል ስም ለሚታወቀው የኤርትራ ብሄራዊ ቡድን 27 ዲያስፓራ ተጨዋቾችን በስብስባቸው አካተዋል።ከሃገር ውስጥ ሶስት ተጨዋች ብቻ መርጠዋል።

አብዛኞቹ ተጨዋቾች በተለያዩ የአውሮፓ ሃገራት እንደ ጀርመን ፡እንግሊዝ፡ስዊዲን፡ካናዳ፡ኦስትሪያ፡ሆላንድ፡ኖርዌይ፡ጣሊያን፡ዩጋንዳ ግብፅ እና የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ የሚጫወቱ ናቸው።
በሁለት ተከታታይ ዓመታት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ኮከብ ግብ አግቢ የነበረው እና አሁን ላይ ለግብፁ አል ናስሪ የሚጫወተው ዓሊ ሱሊማን የቡድኑ ቁልፍ ተጨዋች በመሆን በስብስቡ ተካታል።
ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ተጨዋቾች ዋሊያዎቹን ቢቀላቀሉ ፋይዳቸው እስከምን ድረስ ይሆናል ትላላችሁ?
ወርልድ ስፓርት ከ1986 ዓ.ም ጀምሮ (በጋዜጠኛ ጥሩነህ ካሳ)
