ቅዱስ ጊዮርጊስ የመጨረሻውን ጨዋታ ያለ ደጋፊ እንዲጫወት አወዳዳሪው አካል ወስነ።

0

ቅዱስ ጊዮርጊስ የመጨረሻውን ጨዋታ ያለ ደጋፊ እንዲጫወት አወዳዳሪው አካል ወስነ።

ይሄ ውሳኔ ወይም ቅጣት ለቅዱስ ጊዮርጊስ ምንም የሚፈይደው ነገር የለም ። ምክንያቱም ከዚህ ጨዋታ ቅዱስ ጊዮርጊስ ምንም አይነት ኪሳራም ሆነ ትርፍ የሚያገኝበት ጨዋታ አይደለም ። ስለዚህ ሳንጃው ይህን ጨዋታ የሚያደርገው መርሃግብርን በክብር ለመጨረስ ነው። በዚህ የመጨረሻ ጨዋታ መርሃግብር ላይ ጥንቃቄ ከሚያስፈልጋቸው ጨዋታዎች አንዱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ወልዋሎ አዲግራት ነው። ይህ ቅጣት ለወልዋሎ የምስራች ሲሆን በተቃራኒው ለአዳማ እና ለሽሬ ግን የመርዶ ያህል ነው ተብሏል ። ለቅዱስ ጊዮርጊስ መርሃግብር ከማሟላት ውጭ ጥቅምም ጉዳትም የለውም ። ነገር ግን ለአዳማ ፣ ለሽሬ እና ለወልዋሎ ብዙ ትርጉም ያለው ነው። ቅዱስ ጊዮርጊስ ካሳለፈው አስከፊ ጊዜ እና ካለው የተጫዋች ጥራት አንፃር ብዙ ውጤቶችን ማግኘት የቻለው ታማኝ ደጋፊውዎቹ በሜዳ ውስጥ አብረው መሆናቸው የማይካድ ሐቅ ነው። ይህ ደጋፊ ወደ ሜዳ እንዳይገባ የተወሰደው ቅጣት ለአወዳዳሪው አካል ግን ጥያቄን የሚያስነሳ መዘዝ ይዞበት ሊመጣ ይችላል ስለሆነም ቢረፍድም ቆም ብሎ እንዲያስብበት ምክር ለመለገስ ያህል ነው ። አዳማ እና ሽሬ ላለመውረድ እየተጫወቱ ወልዋሎ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር የሚያደርገው ጨዋታ የወልዋሎ ደጋፊዎች ብቻ እንዲገቡ መፍቀዱን በዝምታ ማየታቸው በገዛ ፈቃዳቸው መውረዳቸውን አርጋግጠዋል ለማለት እደፍራለሁ። በመጨረሻም ቅጣቱ ሳይነሳ ማልያ ሳንለብስ ገብተን እናያለን የምትሉ የቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊዎች ሌላ ቅጣት እና መዘዝ እንዳታመጡብን አደብ ግዙ። ከሚመለከታቸ የስራ ሃላፊዎች ውጭ ሁላችን ስብስብ ብለን

ባለንበት አካባቢ በ OBN ቀጥታ ስርጭት እያየን የማይረሳ ጊዜ ማሳለፍ እንችላለን። ድል ለታላቁ ቅዱስ ጊዮርጊስ።

ያያ መላኩ የቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊ ነው የዘገበው

Facebooktwitterlinkedinyoutubetumblrinstagramflickrfoursquaremail
Facebooktwitterredditpinterestlinkedintumblrmail