የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ እጣ ፕሮግራም ማውጣት መስከረም 7/2019 ዓ.ም ይደረጋል!

መስከረም 30 የሚጀምረው የ2019 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር በተመረጡ 7 ሜዳዎች እና በተዘጋጁ 6 ቋቶች በሚወጣው እጣ መሰረት የውድድር አመቱ መርሃ ግብር ይዘጋጃል።
ለሊጉ የተመረጡ ሜዳዎችም:-
⚽️ አዲስ አበባ ስታዲየም
⚽️ አዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ ስታዲየም
⚽️ ሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ስታዲየም
⚽️ ባህርዳር አለም አቀፍ ስታዲየም
⚽️ ሀላባ ስታዲየም
⚽️ ሆሳዕና አብዩ ኤርሳሞ ስታዲየም እና
⚽️ አርባምንጭ ዩንቨርሲቲ አባያ ካምፓስ ስታዲየም ናቸው።
በዚህ መሰረት የ2019 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የእጣ ማውጣት ስነ ስርዓት መስከረም 7/2019 ይደረጋል።
