የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አዲስ መረጃዎች

0
IMG_20260915_130335_389

የወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ተጫዋቾች በረከት ሳሙኤል እና ካርሎስ ዳምጠው ለ2027 የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ዝግጅቱን እያደረገ የሚገኘው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን እንዲቀላቀሉ ጥሪ ቀርቦላቸዋል። ተጫዋቾቹ ነገ ከሰዓት ብሔራዊ ቡድኑ የሚገኝበት ሀዋሳ እንዲገኙም ጥሪ ተላልፏል።

እንዲሁም የሲዳማ ቡናዎቹ ያሬድ ባየህ፣ አቤል ያለው፣ ቢንያም በላይ፣ መስፍን ታፈሰ እና ብርሃኑ በቀለ ማክሰኞ ከሰዓት ብሔራዊ ቡድኑን እንዲቀላቀሉ ጥሪ ቀርቧል።

በሌላ በኩል ጋቶች ፓኖም እና ከነዓን ማርክነህ የቡድኑን ስብስብ ተቀላቅለው በዛሬው ዕለት የመጀመርያ ልምምድ አከናውነዋል።

Facebooktwitterlinkedinyoutubetumblrinstagramflickrfoursquaremail
Facebooktwitterredditpinterestlinkedintumblrmail