የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን 18ኛ መደበኛ እና የምርጫ ጠቅላላ ጉባዔ በአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን /ECA/ እየተካሄደ ይገኛል

0
IMG_20260915_130930_268

በ2018 የውድድር ዓመት በህይወት ያጣናቸው የእግር ኳስ ቤተሰቦችን በማሰብ በሕሊና ጸሎት በማድረግ የተጀመረው ጉባዔው በማስከተል የባህል እና ስፖርት ሚኒስቴርን በመወከል አቶ ከበደ እጅጉ ፣ የኦሊምፒክ ኮሚቴን በመወከል አቶ ገዛኸኝ ወልዴ ንግግር ያደረጉ ሲሆን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ  የኢትዮጵያን ብሔራዊ ቡድንን በተመለከተ ለጉባዔው ተሳታፊዎች ንግግር አድርገዋል።

በመቀጠል የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት፣ የካፍ የሥራ አስፈጻሚ እና የፊፋ ቋሚ ኮሚቴ አባል አቶ ኢሳያስ ጅራ ንግግር አድርገው የ2018 የበጀት ዓመት አፈጻጸም ሪፖርት፣ የሂሳብ ሪፖርት እና የፋይናንስ ኦዲት ሪፖርት ለጉባዔው ቀርቦ በሙሉ ድምጽ ፀድቋል።

በአሁኑ ሰዓት ጉባዔው የሻይ እረፍት ላይ የሚገኝ ሲሆን በመቀጠል የምርጫ ሂደት የሚከናወን ይሆናል።አቶ ኢሳያስ ጅራ ብቻቸውን ከመንትያቸው  ጋር ተወዳድረው በድጋሚ ስልጣኑን ይቅናጠጣሉ፡፡በጉባሄውና በምርጫው ዙሪያ የታዘብኩትን መጣጥፌን ነገ ይዤ ብቅ እላለው።በተለይም የትኩረትና የትዝብት ሂላማዬ የሚሆነው

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን 18ኛ መደበኛ እና የምርጫ ጠቅላላ ጉባዔን ሂደት በቅርበት እንደታዘብኩት፣ በዋናነት ሦስት ትልልቅ ነጥቦች በነገው መጣጥፌ አተኩራለው ።

ለተቃዋሚ ዕጩዎች በር መዘጋት (ብቸኛ ዕጩነት)፦ የፌዴሬሽኑ የወቅቱ ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ ያለ ምንም ተፎካካሪ ብቸኛ የፕሬዝዳንትነት ዕጩ ሆነው መቅረባቸው የሚታወስ ነው። ይህ ሁኔታ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ዙሪያ አዳዲስ ሐሳቦች እና አማራጭ አመራሮች ወደ ፊት እንዳይመጡ የምርጫ መስፈርቱ ወይም ሂደቱ ተፅዕኖ እያሳደረ መሆኑን በግልጽ ያሳያል።

የፋይናንስ ዕድገት እና የስፖርታዊ ውጤት መራራቅ፦ ፌዴሬሽኑ በበጀት ዓመቱ 370 ሚሊዮን ብር አቅዶ ከ557 ሚሊዮን ብር በላይ (ከዕቅዱ 150%) ገቢ ማሰባሰቡ ትልቅ የፋይናንስ ስኬት ነው። ነገር ግን ይህ ከፍተኛ ገቢ ከሀገሪቱ እግር ኳስ የወረደ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ፣ ከስታዲየሞች ጥራት ማነስ እና ከብሔራዊ ቡድኑ ደካማ ውጤት ጋር ሲነፃፀር በገንዘብና በሜዳ ላይ ውጤት መካከል ትልቅ ክፍተት እንዳለ ያሳያል።

የክልልና የክለቦች ተሳትፎ ሚዛን፦ በጉባዔው ላይ የሚነሱ የድምፅ አሰጣጥ እና ውሳኔዎች አሁንም በክልል እግር ኳስ ማህበራት እና በዋና ዋና ክለቦች ፍላጎት ዙሪያ የሚያጠነጥኑ በመሆናቸው፣ ፌዴሬሽኑ ከግለሰቦች ስምምነት ይልቅ ወደ ጠንካራ ተቋማዊ አሰራር መሸጋገር እንዳለበት አመላካች ነው።

በዚህና በሌሎች ዙሪያ የምለው ይኖረኛል፡፡

Facebooktwitterlinkedinyoutubetumblrinstagramflickrfoursquaremail
Facebooktwitterredditpinterestlinkedintumblrmail