የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ማክሰኞ ከሴኔጋል ይጋጠማል፤የሴኔጋል ቡድን ትናት ምሽት ገብቷል

0
IMG_20260928_124126_730

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በብሉ ናይል ሪዞርት ሆቴል ማረፊያውን ያደረገ ሲሆን በዛሬው ዕለት የመጀመርያ ልምምዱን በባህር ዳር ስታዲየም አከናውኗል።

ከኢትዮጽያ ብሔራዊ ቡድን በኩል መስፍን ታፈሰ ከሱዳን ጋር በተደረገው ጨዋታ የማስጠንቀቂያ ካርድ በመመልከቱ በሁለት ቢጫ ካርድ ቅጣት ምክንያት ከሴኔጋል ጋር ከሚደረገው ጨዋታ ውጪ ሆኗል።

በሌላ በኩል የሴኔጋል ብሔራዊ ቡድን ምሽቱን ባህር ዳር ደርሷል። የልዑክ ቡድኑ ደጃዝማች በላይ ዘለቀ አየር ማረፍያ ሲደርስም አቀባበል ተደርጓላቸዋል።ዛሬ ቀለል ያለ ልምምድ መስራታቸው ከስፍራው የደረሰን ዘገባ ይጠቁማል፤ጨዋታው ነገ በቀኑ 10 ሰዓት በኢትዮጵያ የሰዓት አቆጣጠር ይደረጋል

– ኢትዮጵያ ከ ሴኔጋል የሚያደርጉትን ጨዋታ የስታዲየም መግቢያ ቲኬት በኦንላይን እየተሸጠ ይገኛል።

በዚሁ ማክሰኞ መስከረም 19 ከቀኑ 10፡00 የሚካሄደው ጨዋታ የስታዲየም መግቢያ ቲኬት  eff-tickets.com ላይ በመሸጥ ላይ ይገኛል። ቲኬቱን ለመቁረጥ ይበልጥ አመቺ እንዲሆን ከኢሜይል ማረጋገጫ በተጨማሪ ስልክ ቁጥርዎን የሚጠቀሙበት አማራጭ ተመቻችቷል።

ከኦንላይን ሽያጭ በተጨማሪ በአካል ቲኬት መግዛት ለሚፈልጉ የመሸጫ ቦታዎች የተመቻቹ ሲሆን የመሸጫ ቦታዎቹን በነገው ዕለት እንገልፃለን።

የቲኬት ዋጋ
ፕሪምየም ደረጃ 500 ብር
ካቴጎሪ 2 ደረጃ 200 ብር
ካቴጎሪ 3 ደረጃ 100 ብር

https://eff-tickets.com

የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ከሲሸልስ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ጋር ያደርግአል

በ2028 ኦሊምፒክ ሴቶች እግር ኳስ ማጣርያ ከሩዋንዳ ጋር ለሚያደርጉት ጨዋታ በዝግጅት ላይ የሚገኙት የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ከሲሸልስ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ጋር ሁለት ዓለምአቀፍ የወዳጅነት ጨዋታዎች ያደርጋሉ።

የመጀመርያው ጨዋታ ረቡዕ መስከረም 20 ከቀኑ 9፡00 ላይ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ሲደረግ ሁለተኛው ጨዋታ ቅዳሜ መስከረም 23 በተመሳሳይ ሰዓት እና ቦታ የሚጫወቱ ይሆናል።

Facebooktwitterlinkedinyoutubetumblrinstagramflickrfoursquaremail
Facebooktwitterredditpinterestlinkedintumblrmail