ሲዳማ ቡና የ2018 ሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮን በመሆነናችሁ እንኳን ደስ አላችሁ እንላለን

በ36ኛው ሳምንት የሊጉ መርሀ ግብር በአዲስ አበባ ስታዲየም 2ኛ ደረጃ ላይ የሚገኘውን ነጌሌ አርሲን የገጠመው ሲዳማ ቡና 1 ለ 1 አቻ ተለያይቶ የዋንጫ በለቤት ሆኗል።
የሲዳማ ቡናን ግብ ያስቆጠረው ብርሀኑ በቀለ ሲሆን፤ በረከት ወልዴ ነጌሌ አርሲን በፍፁም ቅጣት ምት አቻ አድርጓል።
በዚህም ነጥቡን 65 ያደረሰው ሲዳማ ቡና ሳምንታት እየቀረው ከወዲሁ የ2018 ሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮን መሆኑን አረጋግጧል። ቡድኑ በ1999 ዓመተ ምህረት ተመስርቶ የፕሪምየር ሊግ ከተመሰረቱ አንጋፋ ክለቦችን ጭምር በማሸነፉ የክለቡን አባላት በሙሉ እንኳን ደስ አላችሁ እንላለን!
