ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ ተጫዋቾች የ20 ሚሊዮን ብር ሽልማት አበረከተ።

ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ ተጫዋቾች የ20 ሚሊዮን ብር ሽልማት አበረከተ።
የሽልማት መርሐ ግብሩ በሸራተን አዲስ ሌግዠሪ ኮሌክሽን ሆቴል በመካሄድ ላይ ይገኛል።

በሥነ ሥርዓቱ ላይ የክለቡ ተጫዋቾች፣ አሰልጣኞችና አመራሮች፣ ደጋፊዎች እንዲሁም የቀድሞ ተጫዋቾች ተገኝተዋል።

ለእያንዳንዱ የክለቡ ተጨዋቾች፣ የአሰልጣኝ ቡድን አባላት፣ ኳስ አቀባይ እና ትጥቅ ያዥ እንደየተሳትፎ መጠን እና አስተዋጽዎአቸው ከ50 ሺህ እስከ 600 ሺህ ብር የሚደርስ የገንዘብ ስጦታ ተበርክቶላቸዋል።
