አትሌት ትዕግሥት አሰፋ የዓለም አትሌቲክስ የዓመቱ ምርጥ አትሌት ሽልማት እጩ ሆነች

0
IMG_20261008_082014_497

የኢትዮጵያ የማራቶን ኮከብ አትሌት ትዕግሥት አሰፋ ለ2026 የዓለም አትሌቲክስ የዓመቱ ምርጥ አትሌት ሽልማት እጩ ሆናለች።

የዓለም አትሌቲክስ ዛሬ የእጩዎች ዝርዝር ይፋ አድርጓል ።

አትሌት ትዕግሥት በ2026 የለንደን ማራቶን 2:15:41 በሆነ ሰዓት በሴቶች ብቻ በሚደረግ የማራቶን ውድድር የዓለም ክብረወሰን በማሻሻል አሸንፋለች።

በቅርቡ በበርሊን ማራቶን 2:11:04 በማስመዝገብ የሴቶች ማራቶን ታሪክ ሦስተኛውን ፈጣን ሰዓት በማስመዝገብ የበርሊን ማራቶን ለሦስተኛ ጊዜ ውድድሩን በበላይነት ፈፅማለች ።

የ2023 የዓለም አትሌቲክስ ከስታዲየም ውጭ የዓመቱ ምርጥ አትሌት በመሆን የተሸለመችው አትሌት ትዕግሥት አሰፋ፣ በዚህ ዓመትም በማራቶን ያሳየችው ድንቅ ብቃት ለሽልማቱ ከታጩ አትሌቶች መካከል እንድትካተት አድርጓታል።

የ2026 የዓለም አትሌቲክስ የዓመቱ ምርጥ አትሌት ለመምረጥ የመጨረሻው ዙር የደጋፊዎች ድምፅ አሰጣጥ ከዛሬ መስከረም 26 እስከ ጥቅምት 7 ቀን 2019 ድረስ ይካሄዳል።

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቤተሰብ በዚህ ዓመት በዓለም መድረክ ኢትዮጵያን በላቀ ደረጃ ያስጠራችውን ትዕግሥት አሰፋን በመደገፍ ድምፁን እንዲሰጥ ጥሪ እናቀርባለን።

ድምፅዎን ለትዕግሥት አሰፋ ለመስጠት ከታች ያለውን ሊንክ ይጠቀሙ።

Who has your vote? 👉 https://bit.ly/4y66IHT

በተያያዘ ዜና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ለአዲዳስ የምስጋና  መልዕክት ልኳል ፌዴሬሽኑ እንዳለው፣ በዚህ ወሳኝ ወቅት ለብሔራዊ ጀግናችን እና ለተከበረችው አትሌት ትግስት አሰፋ ለተደረገላት ልዩ ድጋፍ እና እንክብካቤ ለአዲዳስ ያለንን ጥልቅ አድናቆት እና ከልብ የመነጨ ምስጋናችንን መግለጽ እንፈልጋን ብሏል


በተለይ አዲዳስ ከበርሊን ወደ ሙኒክ እንድትዛወር የግል ጄት በማዘጋጀትና  ከሁሉም በላይ ደግሞ አስፈላጊውን የህክምና እና የቀዶ ጥገና እንክብካቤ እንድታገኝ በሙኒክ የህክምና ድጋፍ እና እርዳታ ላደረገችበት ሁኔታ ምስጋናችንን ማቅረብ እንልጋለን ሲል ገልጿል።
ለአዲዳስ ዋና ስራ አስፈፃሚ፣ ለመላው የአስተዳደር ቡድን፣ ለሰራተኞች እና ለሚመለከታቸው አካላት ላሳዩት የላቀ ቁርጠኝነት እና ድጋፍ ልባዊ ምስጋናችንን እናቀርባን። እንዲሁም በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ላሳዩት ቁርጠኝነት፣ ትብብር እና ቀጣይ ድጋፍ ለትዕግስት አሰፋ የአስተዳደር ቡድን እና ለአመራሩ ልዩ ምስጋናናችንን ማቅረብ እንወዳለን በማለት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ለአዲዳስ ምስጋናውን አቅርቧል ።

Facebooktwitterlinkedinyoutubetumblrinstagramflickrfoursquaremail
Facebooktwitterredditpinterestlinkedintumblrmail