ሉሲዎቹ በኦሊምፒክ የሴቶች እግር ኳስ ማጣሪያ የመጀመሪያ ዙር ጨዋታ ሩዋንዳን አሸነፉ

የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን (ሉሲዎቹ) በኦሊምፒክ የሴቶች እግር ኳስ ማጣሪያ የመጀመሪያ ዙር ጨዋታ ሩዋንዳን 1 ለ 0 በሆነ ጠባብ ውጤት አሸንፈዋል።
🇷🇼 ሩዋንዳ 0 🇪🇹 ኢትዮጵያ 1 ኡዛዬ ሴንጋ ሊድያ (በራሷ ላይ ግቡን አስቆጥራለች – 45+3′)

ሁለቱ ቡድኖች የመልስ ጨዋታቸውን በጥቅምት 3 ቀን ያደርጋሉ።
ጨዋታው በድሬዳዋ ስታዲየም ላይ የሚካሄድ ይሆናል።
ጨዋታው ለ2028ቱ የሎስ አንጀለስ ኦሊምፒክ ጨዋታዎች ለማለፍ የሚደረገው የካፍ (CAF) የሴቶች ማጣሪያ ሁለተኛ ዙር የመጀመሪያ ጨዋታ አካል ነው።

ጨዋታው እጅግ ብርቱ ፉክክር የታየበት ሲሆን፥ ኢትዮጵያ ብቸኛዋንና የማሸነፊያ ጎል ያገኘችው በመጀመሪያው አጋማሽ ማጠናቀቂያ ተጨማሪ ሰዓት ላይ (45+3′) የሩዋንዳዋ ተከላካይ ኡዛዬሴንጋ ሊድያ ራሷ ላይ ባስቆጠረችው (Own Goal) ሳቢያ ነው ሉሲዎቹ አሸንፈው የወጡት።

የሉሲዎቹ የምንግዜም ምርጥ ግብ አስቆጣሪ የሆነችው ሎዛ አበራ ከቡድኑ ጋር ወደ ኪጋሊ ስላልተጓዘች በዚህ ጨዋታ ላይ አልተሰለፈችም።
የሉሲዎቹ ዋና አሰልጣኝ ሻለው ለሜቻ ከጨዋታው በፊት በሰጡት መግለጫ የሴካፋ (CECAFA) ቀጠና ሀገራት እርስ በርስ የሚያደርጓቸው ጨዋታዎች ሁሌም ከባድ መሆናቸውን ጠቅሰው፣ ቡድናቸው በመጀመሪያው ጨዋታ የነበረውን የሜዳ ላይ የበላይነት ይዞ መውጣት መቻሉ ለቀጣዩ ጨዋታ ትልቅ መተማመንን ፈጥሯል።
የሁለቱ ሀገራት አሸናፊ ቡድን በቀጣዩ ዙር የቦትስዋና እና ታንዛኒያ አሸናፊ ከሚሆነው ቡድን ጋር እንደሚገናኝ ታውቋል።
